ዐባይ ቢሻው ይጉረፍ በጣና ላይ ነግሶ አሎሃ ይደፍርስ ተከዜም ደም ለብሶ ማሂንም አቋሽም ጓንግም በሙላቱ መሻገሪያ ይንሳ እስኪያልፍ ክረምቱ ይፎክር ያቅራራ ይኩራ በጉልበቱ ድሮም እንዳይፀዳ በጎርፍ ውኃ ታጥቦ የጀግና ሰው ሞቱ ያውቃሉ እናውቃለን ዛሬም እንደ ጥንቱ ደም በደም ይፀዳል ደም ነው ሥርየቱ። ለጀግና ዕምባ አይረጩም ፀጉርም አይላጩም ዋይታና ለቅሶ ሙሾ አይደረድሩም ወይም ፊት አይነጩም እንደ አባት አደሩ እንደ ጎንደር በሃል ደም ነው ሥርየቱ ደም በደም ይፀዳል። አለፋ ጣቁሳ ደንቢያና ፎገራ ጭልጋ ገለድባ ከሽንፋ እስከ ቋራ ጎዛምን በላያ ከመተክል ፓዌ ከሻግኔ ወንበራ ከፍኖተ ሰላም ማንኩሳ እንጅባራ መተማ ሰራቆ ጫቆና አዳኝ አገር ቆላ ደጋ ዳሞት ቋሪትና አቸፈር እነሴና ነብሴ ሞጣ ቀራኒዎ ጭስ ዐባይ ባህር ዳር ነፋስ መውጫ ጋይንት እስቴ ደብረ … [Read more...] about ደም ነው ሥርየቱ
“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!
“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡ “መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ … [Read more...] about “ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!
GREATER ACCOUNTABILITY FROM ETHIOPIA’S AUTOCRATIC REGIME SHOULD BE A CONDITION OF CONTINUED AID
ETHIOPIA CHARGES NON-VIOLENT OPPOSITION LEADER WITH TERRORISM AFTER HE MET WITH MEMBERS OF THE EUROPEAN PARLIAMENT SMNE Press Release. The EU, the US, the UK, Canada, Germany, Sweden, Norway and other Western democratic countries should not continue to give large amounts of aid to the increasingly authoritarian Ethiopian regime of the TPLF/EPRDF. In a time where global doors are closing to refugees, why should money from the West continue to prop up a dictatorship that leads to so much … [Read more...] about GREATER ACCOUNTABILITY FROM ETHIOPIA’S AUTOCRATIC REGIME SHOULD BE A CONDITION OF CONTINUED AID
ታጋይ ጎቤ መልኬ በአዴት ጦርነት ተሰዋ፤ “የህወሃት ወራሪ ሃይል ጉዳት ደርሶበታል”
“ጎቤ ሲሰዋ አዳዲስ ጎቤዎች ትግሉን ተቀላቅለዋል’’ “አርበኛ ጎቤ መልኬ ተሰዋ” ሲሉ በአካባቢው የሚገኙ የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ገለጹ። ህወሃት የሚመራው ሰራዊት ክፉኛ ጉዳት ደርሶበታል። ዜናው ኢህአዴግ በሚያስተዳድራቸውም ሆነ በሚደጉማቸው መገናኛዎች ይፋ አልሆነም። ለነጻነት ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ አካላትም ይህ ዜና እስከታተመበት ድረስ በግልጽ ያሉት ነገር የለም። አርበኛ ጎቤ እራሱን እንዳጠፋም የሚገልጹ አሉ። በሰሜን ምዕራብ ቆላማዉ ክፍል የደፈጣ ተዋጊዎችን የሚመራዉ ታዋቂዉ አርበኛ ታጋይ ጎቤ መልኬ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ዕዝ ስር ባለዉ “አንገረብ” እየተባለ በሚጠራዉ የስለላ ቡድንና በ“ጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል ቡድን” የጋራ ዘመቻ በጠገዴ ወረዳ ልዮ ስሙ “አዴት” በተባለ በርሃማ ቦታ ትላንት ማምሻዉን በተካሄደ ዉጊያ ነው “ጎቤ ተሰዋ” … [Read more...] about ታጋይ ጎቤ መልኬ በአዴት ጦርነት ተሰዋ፤ “የህወሃት ወራሪ ሃይል ጉዳት ደርሶበታል”
ትናገር አድዋ
አድዋ የኢትዮጵያ፣ አድዋ የአፍሪካ፣ አድዋ የጥቁር ህዝብ ታሪክ ነው። በዕለተ ጊዮርጊስ የካቲት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሀገር ወራሪ ጦር በምሥራቅ አፍሪካ አከርካሪው የተመታበት ዕለት። የዓለም ድሀ ሀገሮችን የናቀና ጦር መሣሪያውን የተማመነ ኃይል በጋሻ ጎራዴ የተንበረከከበት፣ የነፃነት ጮራ ከወደ ምሥራቅ አፍሪካ የፈነጠቀበት፣ ታሪካዊ የድል ቀን አድዋ። ትናገር አድዋ። ትመስክር አድዋ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ … [Read more...] about ትናገር አድዋ
የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤
የህወሓት-እስራኤል ቀጣይ የፖለቲካ ቁማር! አሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለህወሓት/ኢህአዴግ ቁልፍ የስጋት ምንጩ የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ጎራ ነዉ፡፡ የድህረ-ምርጫ 97 ዉርስ ዕዳ የሆነዉ የዲያስፖራዉ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንደ ሀገር ቤቱ ሁሉ በዘዉግ ፖለቲካ የሚታመስ ቢሆንም በጋራ ጠላት (ህወሓት/ኢህአዴግ) መዉደቅ ላይ ያለ አንዳች የልዩነት መስመር ይስማማል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሀገር ቤት ያሉት የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከሚያሰሙት ጩኅት በላይ ከባህር ማዶ የሚሰማዉ ሹክሹክታ እንቅልፍ ይነሳዋል፡፡ የህዝብ ድምጽና የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ መሳ ለመሳ መሄድ የቆላ ቁስል ሆኖበታል፡፡ እናም የዲፕሎማሲ ታርጋን እንደ ሴራ ፖለቲካና ድርጅታዊ ጠቀሜታነት አብዝቶ ለመጠቀም የጨዋታዉን ህግ ያሻሻለ ይመስላል፡፡ የዲያስፖራ ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማይካድ ደረጃ … [Read more...] about የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤
ዜግነትና የስደተኞች መብትና ግዴታ
ስደተኞች ወደኢትዮጵያ የሚልኩት ጠገራ ብር ብዙ እንደሆነ አውቃለሁ፤ አንዳንድ ስደተኞች ለእንደኔ ያለ ወገኖቻቸው በብዙ መንገድ እርዳታ እንደሚያበረክቱ አውቃለሁ፤ በአንጻሩም አንዳንድ ስደተኞች ትንሽ ጠገራ ብር ይዘው መጥተው የሀኪም ቤትና ሌላም ዓይነት የንግድ ድርጅት (ሀኪም ቤቱን ከንግድ ጋር ያገናኘሁት አውቄ ነው) እያቋቋሙ ደሀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየገፈፉ የሚከብሩም እንዳሉ አውቃለሁ፤ ስደተኞች በአጠቃላይ ለአገራቸውና ለወገናቸው መብት በፖሊቲካው መስክ የሚያደርጉትን ትልቅ አስተዋጽኦ አውቃለሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የሚከነክነኝ ነገር አለ፡፡ ለእኔ ዜግነት ማለት የአገር ባለቤትነት ነው፤ የአገር ባለቤትነት መብቶችንና ግዴታዎችን ያጎናጽፋል፤ አንድ ሰው ስደተኛ ሲሆን የተወለደበትን አገር ባለቤትነት ከነመብቶቹና ግዴታዎቹ በፈቃዱ ትቶ ለሌላ አገር የሚያስረክብ ይመስለኛል፤ እዚህ ላይ … [Read more...] about ዜግነትና የስደተኞች መብትና ግዴታ
ብአዴን አከርካሪው ላይ ተቆርጧል – ሕዝብ እነ ደመቀን “በቃችሁ” አላቸው!
በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎንደር አቅንተዉ ነበር፡፡ በደመቀ መኮንንና በገዱ አንዳርጋቸዉ የተመራዉ ከፍተኛ አመራር ቡድን ሦስት ዋናዋና ቁልፍ ተልዕዎኮችን ለማሳካት ከባህርዳር እንደተንቀሳቀሰ የጎልጉል ድረገጽ ጋዜጣ የብአዴን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ አንደኛ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመራዘሙን አስፈላጊነት ለህዝብ ለማሳመን፤ ሁለተኛ የነጻነት ኃይሎች በሀገር ሽማግሌዎች አደራዳሪነት ከአገዛዙ ጋር ዕርቅ እንዲያወርዱ ከሚያስችሉ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ለመምከር፤ በሦስተኛ ደረጃ የተያዘዉ ተልዕኮ አብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ በአማራና በትግራይ ህዝብ መካከል የተፈጠረዉን ቅራኔ በኃይማኖት አባቶች የምኩራብ ስብከት አማካይነት እንዲበርድ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አቅጣጫ በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ-ስብከት ሥር ላሉ አድባራት በአቡነ ኤልሳዕ በኩል መልዕክቱን ማድረስ የሚሉት … [Read more...] about ብአዴን አከርካሪው ላይ ተቆርጧል – ሕዝብ እነ ደመቀን “በቃችሁ” አላቸው!
የዐድዋ ድል “የታሪክ አጋጣሚ” ወይስ በዕቅድ የተከወነ?
ሰሞኑን የዐድዋ ድል መታሰቢያ 121ኛ ዐመት የሚዘከርበት ወቅት ነው። በፍቃዱ ዘ. ኀይሉ የተሰኘ ከታቢ (blogger) "Bilisummaa adda-ዋ!" በተሰኘ እና በድረ ገጽ እና በፌስ ቡክ በተሰራጨ አነጋጋሪ ጽሑፉ ስለ ዐድዋ ድል እና ስለ ምኒልክ አመራር ብዙ ቢልም በተለይ ኹለቱ ትርክቶች የሚጐረባብጡ፤ ፈራቸውን የሳቱ ኾነው ስላገኘኹዋቸው እነሱ ላይ ሀሳቤን ማካፈል ወደድኩ። ኹለቱ የበፍቃዱ ዘኀይሉ “Bilisummaa adda-ዋ!” ትርክቶች፤ 1) የዐድዋ ድል በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ነው እና 2) ዐድዋ የጨቋኝ ምርጫ የተሰኙት ናቸው። ኹለተኛው ትርክት ቃል በቃል ባይኾንም የዐድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነጭ ጨቋኝ የጥቁር ጨቋኝ መርጦ የተዋጋበት እንጂ የዐድዋ ጦርነት ሕዝቡ ለነጻነት የተዋጋበት ጦርነት አይደለም ነው። በትክክል ተረድቼው ከኾነ በፍቃዱ መነሻ ሀሳቡን ያገኘው … [Read more...] about የዐድዋ ድል “የታሪክ አጋጣሚ” ወይስ በዕቅድ የተከወነ?
ለማሳጠር መስራት፤ ስለመርዘምም ማሰብ
በፌብርዋሪ 11 እና 12, 2017 በሁለቱ ቀናት ውስጥ በአምስቱም ክፍለ ዓለማት በሚገኙ ከአርባ በላይ በሚሆኑ ከተሞች ለአርበኞች ግንቦት 7 የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተደረጉ በዓላዊ ዘመቻዎች መካሄዳቸውን የበረታ በየአካባቢ በተደረጉት ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ለዓይን ምስክርነት ሲበቃ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ደግሞ በሚዲያዎች የታደመው ይመስለኛል። በዝግጅቱ ላይ ከድጋፍ ማሰባሰቡ በተጓዳኝ ለአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስካይፔ ከየአካባቢው ጥያቄዎች እየቀረቡ መልስ ሲሰጥም ስለነበር፤ በዚህ አጋጣሚ ከቀረቡት ልዩ ልዩ ጥያቀዌዎች ውስጥ አንድ ሃሳቤን የሰረቀው ጥያቄ "የትጥቅ ትግሉ በተጠበቀው ፍጥነት አልሄደም" የሚለው ነበር። ጥያቄው ማንም የባርነት ቀንበር የከበደው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ሊያነሳው ጥያቄ እንደሆነ የሚያጠያይቅ አይመስለኝም። የመከራና የጭነቀት … [Read more...] about ለማሳጠር መስራት፤ ስለመርዘምም ማሰብ










