በኦህዴድ አባላት ዘንድ “ጃርሳው” የሚል መጠሪያ ያላቸው አባዱላ ገመዳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰለቻቸው ከፍተኛ አመራሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው። "ንፍሮ እየበላሁ ከተራው ህዝብ ጋር መኖር ናፈቀኝ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን በነጻነት የምሄድበት ቀን መቼ ነው?" በማለት ለሚቀርቧቸው ሲናገሩ መቆየታቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ምስክርነት ይሰጣሉ። የጦር ሰራዊት መለዮ አውልቀው መከላከያ ሚኒስትር፣ ከዛም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙት አባዱላ፣ በኢህአዴግ አመራሮች የማይደፈሩ ቦታዎች ድረስ ዘልቀው በመግባት ከህዝብ ጋር በተደጋጋሚ የመከሩ፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ኦሮሚያ ላይየተሻለ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው። በአቶ ደራራ ሞት እጃቸው አለበት በሚል የሚከሷቸው ያሉትን ያህል፣ በባህሪያቸው ሩህሩህ እንደሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አርሲና ባሌን … [Read more...] about “እስከማውቀው አባዱላ በዚህ መልኩ አይዳፈሩም”፤ አባዱላ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነት
ሽሽት እና አባዱላ ገመዳ
ከሰሜን እና ከበስተ-ምስራቅ አቅጣጫ እየነፈሰ ያለው አውሎንፋስ መርከብዋን እያናጋት ይገኛል። ጫፍ ላይ ጉብ ያሉትን አስተናጋጆች እያንጠባጠበ የሚገፋው ሃይል እየበረታ መጥቶ፣ አሁን ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ይህ ሁላችንንም የሚያስማማን መራራ ሃቅ ነው። ችግሩ እዚህ ላይ አይደለም። ግን ... እየሰመጠ ካለው ከዚህ መርከብ ለማምለጥ የተገኘችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ የሚሾልኩትን ሁሉ "ጀግና" ብለን ለመጥራት እንደምን ይዳዳን? ራስን ማዳን እና ሃገርን ማዳን፤ በሰማይና በምድር መሃከል ያለ ርቀትን ያህል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ዘንግተነው ከሆነ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ይህ ስራዓት "በስብሷል" ብሎ ከተናገረ 10 አመታት አልፈውታል። ከ 26 ዓመታት በኋላ ደግሞ እነሆ ህወሃት ከርፍቶ መርገፍ ጀመረ። ችግሮቹ ግን እጅግ እየተባባሱ እንጂ እየተሻሻሉ አልመጡም። ይህ ስርዓት ዛሬ … [Read more...] about ሽሽት እና አባዱላ ገመዳ
Chinese Investments in Africa: “Chopsticks Mercantilism”
In the early parts of the 21st century, China became an important source of finance for African development. The continent’s infrastructure was in disrepair; it had crumpled after decades of abject neglect and destruction from senseless civil wars. A substantial investment was – and still – needed to rebuild this infrastructure. According to a World Bank Report (2009), “the poor state of infrastructure in Sub-Saharan Africa—its electricity, water, roads and information and communications … [Read more...] about Chinese Investments in Africa: “Chopsticks Mercantilism”
አገርን ከጥፋት ህዝብን ከፍጅት ለማዳን ዛሬውኑ በጋራ እንነሳ
በአገራችን ውሰጥ የሰፈነው ከፋፋይ ሥርዓት እነሆ ህዝባችንን እርስ በርስ የሚያጋጭና የአገሪቱንም አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ሕዝባችን በየዕለቱ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ይገኛል። የቀውሱ አድማስም በአንድ ቦታ የተወሰነ ሳይሆን በየጊዜው እየሰፋ ትላንት ሰላም ነው ይባል የነበረን ቦታ ዛሬ የቀውስ ማዕከል እያደረገው ሁሉንም የኅብረተሰባችንን ክፍል፣ ሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ እየነካ ይገኛል። በቀላል አነጋገር አገሪቱ ከዳር አስከ ዳር በቀውስ አየተናጠች መሆኗ በገሃድ አየታየ ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ላለፉት 26 ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን አመቃ፣ ምዝበራና ንቅዘት በመቃወም የተነሳው ህዝባዊ አንቅስቃሴ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን፣ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ የተከሰተው የሥርዓቱ ውስጣዊ መፈራረስ ያስከተለው መዘዝ መሆኑን መታዘብ ይቻላል። የዚህ ሁሉ … [Read more...] about አገርን ከጥፋት ህዝብን ከፍጅት ለማዳን ዛሬውኑ በጋራ እንነሳ
የኢትዮጵያ ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ፣ ተግዳሮቶቹና የመፍትሄ ኣሳብ
የሰው ልጅ ማህበራዊና ግላዊ ተፈጥሮ ስላለው ለማህበራዊ ኑሮውና ለግላዊ ኑሮው የተለያዩ ጠገጎችን እያበጀ ይኖራል። እነዚህ የሚሰራቸው ጠገጎች ለግል ህይወቱም ሆነ ለማህበራዊ ህይወቱ ወሳኝ ናቸው። ሰው የዚህን ዓለም ኑሮውን ለመግፋት ከሚያስችሉት መሳሪያዎች ኣንዱ እነዚህ ጠገጎቹ ናቸው። የሰው ልጅ በህይወቱ የሚፈጥራቸው እነዚህ ጠገጎች ሃይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ወይም ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትርፍ ያስገኙለታል። ታዲያ ይህ የሰው ልጅ በዓለም ላይ ከሚፈጥራቸው ጠገጎች መሃል ከፍተኛውና ጠንካራው ሃገር የሚባለው ጠገጉ ነው። በርግጥ ከዚህ ኣልፎ ዛሬ ጊዜ ሌላ ከፍ ያለ የጋራ የዓለም ጠገግ ህዝቦች ኣበጅተው ስያሜውን ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ብለውታል። ነገር ግን የሰው ልጅ ከቀን ተቀን ህይወቱ ጋር በጣም የተሳሰረው ጠገግ አገር ሲሆን ለዚህ ጠገግ የተለያዩ ስምምነቶችን ኣስፍሮ በዚህ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሶሺዮ ፖለቲካ ጉዞ፣ ተግዳሮቶቹና የመፍትሄ ኣሳብ
H.Res 128 ከጸደቀ በሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር አልተባበርም ማለት ምን እንድምታ አለው?
የተከበሩና የዘወትር የኢትዮጵያ ህዝብ ነገር የሚቆጫቸው እንደራሴ ስሚዝ ክሪስ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ትግል ለመደገፍ ሲሉ H.Res 128 ህግን ኣርቅቀዋል። ይህ ህግ በውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ወደ ዋናው ምክርቤት ለድምጽ ውሳኔ በመሄድ ላይ ነው። ባለፈው ኦክቶበር ሁለት ለህዝብ ተወካዮች ለድምጽ ይቀርባል ተብሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይሁን እንጂ እንደተራዘመ ተገልጻል። የተራዘመበት ምክንያት በትክክል ባይገለጽም ነገር ግን በመሃል የኢትዮጵያ መንግስት በአምባሳደሩ አማካኝነት ለአሜሪካ እንደራሴዎች ይህን ህግ ካሳለፋችሁ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋራ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አትተባበርም በማለት የማባበል ይሁን የማስፈራራት ስራ አየሰራ እንደሆነ የተከበሩ እንደራሴ ማይክ ኮፍማን ተናግረዋል። ይህ የኢትዮጵያ መንግስት አባባል ምን ማለት ነው? የዚህ አባባል አንድምታው … [Read more...] about H.Res 128 ከጸደቀ በሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር አልተባበርም ማለት ምን እንድምታ አለው?
የአምባሳደር ኸርማን ኮኸን ምክርና የኢትዮጵያ ጥቅም
የኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል በተደረገበት ጊዜ ታላቅ ሚና ከነበራቸው ባለስልጣኖች አንዱ አምባሳደር ኸርማን ኮኸን እንደነበሩ ይታወቃል። በምእራቡ አለም ደግሞ የቀድሞ ባለስልጣኖች ከጡረታ በዄላም ቢሆን ቁልፍ ሚና ሲጫዎቱ ይስተዋላል። በመሆኑም፤ አርሳቸው በዚሀ ጉዳይ ላይ ህሳበ ሲስንዘሩ ትኩርት መሰጠቱ አስፈላጊነቱን የጎላ ያደርገዋል።ከዚህ በመነሳት ስሞኑን አምባሳደር ኮኸን ይዘውልን ብቅ ያሉትን ጉዳይ አንዳንድ ገጽታዎች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ እመረምራለሁ። አምባሳደር ኸርማን ኮኸን በኤርትራ (ሻቢያ) ላይ የተባበሩት መንግስታት የጣለው ማእቀብ ሊነሳ ይገባዋል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ አሁን በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ያላትን ቦታ ተጠቅማ እንዲያውም ስለማእቀቡ መነሳት በግንባር ቀደምትነት ዋናዋ ጠያቂ መሆን አለባት ሲሉ እንደተናገሩ አፍሪካን ኒውስ የተሰኘው ድረ ገጽ ላይ … [Read more...] about የአምባሳደር ኸርማን ኮኸን ምክርና የኢትዮጵያ ጥቅም
HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
ለኢትዮጵውያን ታላቅ ተስፋ ይዞ የተነሳው HR 128/SR 168 በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኘ ተነገረ። የህወሃት/ኢህአዴግን ህልውና በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ብዙ የተባለለት ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ ከማግኘቱ በፊት ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት የማቀዛቀዝ ተግባር እየተፈጸመበት ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረው በመታገል ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጠ። ሐምሌ 20፤ 2009ዓም (7/27/2017) የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳደርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት ማለፉ ይታወሳል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን … [Read more...] about HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!
Interview with Obang Metho on Soft Skills
Following the publication of 'Soft Skills That Make or Break Your Success' book, the author has been interviewing successful professionals to share their take on soft skills. In this interview, Obang Metho, Executive Director of Solidarity Movement for New Ethiopia (www.solidaritymovement.org) shared which soft skills helped him the most, which soft skill he is working on, and the soft skills that are very vital to Ethiopians in the Diaspora. You can get the book, Soft Skills That Make or Break … [Read more...] about Interview with Obang Metho on Soft Skills
የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ
ህወሐት በትግል ፕሮግራሙ የአማራን ያክል የሚጠላው ሌላ ህዝብም ሆነ አካል እንደሌለ በግልጽ ያስቀመጠ ድርጅት ነው። የአማራ ህዝብ መሬት እያረሰ የሚኖር ደሀ ህዝብ ቢሆንም በህወሐት የምስረታ ሰነዶች እንደ ገዥ ብሄር ተፈርጆአል። አስገራሚው ነገር አማራ ንጉሱንም ሆነ ደርግን በማስወገድ ትግል ከሌሎች ህዝቦች እኩል ድርሻ የነበረው ህዝብ ነው። እንደ ህዝብ በህወሐት የሚጠላው በተጨበጠ ምክንያት አይደለም። ህወሐት የአማራን በሌሎች እንዲጠላ ካደረገባቸው የተደራጁ ስብከቶች በተጨማሪ የብሄረሰቡን ማንነት የሚያዳክምባቸው ልዩ ልዩ እርምጃዎችንም ወስዶአል። አንዱ ሴቶች ፍላጎታቸው ሳይጠየቅ የረጅም ግዜ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ማድረጉ ነው። በዚህም እኤአ 2007 የህዝብ ቆጠራ የህዝብ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በ3 ሚሊዮን የቀነሰ ብቸኛ ህዝብ ሆኖአል። ሌላው በትግራይ ክልል የልዩ … [Read more...] about የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ









