• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

H.Res 128 ከጸደቀ በሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር አልተባበርም ማለት ምን እንድምታ አለው?

October 5, 2017 08:16 am by Editor Leave a Comment

የተከበሩና የዘወትር የኢትዮጵያ ህዝብ ነገር የሚቆጫቸው እንደራሴ ስሚዝ ክሪስ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ትግል ለመደገፍ ሲሉ  H.Res 128  ህግን ኣርቅቀዋል። ይህ ህግ በውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ወደ ዋናው ምክርቤት ለድምጽ ውሳኔ በመሄድ ላይ ነው። ባለፈው ኦክቶበር ሁለት ለህዝብ ተወካዮች ለድምጽ ይቀርባል ተብሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይሁን እንጂ እንደተራዘመ ተገልጻል። የተራዘመበት ምክንያት በትክክል ባይገለጽም ነገር ግን በመሃል የኢትዮጵያ መንግስት በአምባሳደሩ አማካኝነት ለአሜሪካ እንደራሴዎች ይህን ህግ ካሳለፋችሁ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋራ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አትተባበርም በማለት የማባበል ይሁን የማስፈራራት ስራ አየሰራ እንደሆነ የተከበሩ  እንደራሴ ማይክ ኮፍማን  ተናግረዋል። ይህ የኢትዮጵያ መንግስት አባባል ምን ማለት ነው? የዚህ አባባል አንድምታው ምንድን ነው?  የሚለውን ማጤን ተገቢ ነው። በቅድሚያ H.Res 128  ምን ይዘት እንዳለው እንመልከት።

በክቡር እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ የተዘጋጀውና  በሌላ በኩል በሰኔት የተዘጋጀው S.Res 168 ሰነድ ተመሳሳይነት አላቸው።  H.Res 128 አጠቃላይ  ዓላማው በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት እንዲከበርና ሁሉን አቀፍ የሆነ የተሻለ አስተዳደርን ለማጠናከር ነው። ዝርዝር ይዘቱ የሚጠይቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠያቂነት እንዲኖር፣ ነፍጥ ያነሱ ሃይላት ከዚህ ታቅበው ዲያሎግ እንዲያደርጉ፣ ከዚህ በፊት ሰው የፈጁ የሚዘርፉ በህግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያትት ሲሆን ጠበቅ ያለ ጉዳይም ይዟል። በተለይ ኢትዮጵያውያንን በግፍ የሚገድሉ የሚያሰቃዩ የሚዘርፍ ሁሉ ማእቀብ እንዲደረግባቸው ንብረታቸው እንዲያዝ ይጠይቃል። ይህን ህግ ነው የኢትዮጵያ መንግስት H.Res 128 ህግ ካሳለፋችሁ ከናንተ ጋር ሽብርተኛን አልዋጋም ያስባለው። በርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ካለ፣ በርግጥ ለህዝብ የቆመ መንግስትና ሙስናን  ለመዋጋት የተነሳ መንግስት ከሆነ ይህን ህግ ሊፈራው አይገባም ነበር። እንዲያውም ይህን ህግ ለለውጥ ሙስናን ለመዋጋት እንደ ደጋፊ ሃይል ሊጠቀምበት ባሰበ ነበር።

እንደ ጠቃሚ ሪሶርስ አይቶት በነፍጥ ለውጥ እናመጣለን ያሉ ሃይሎችን ወደ ድርድር ለማምጣት በተጠቀመበት ነበር። ሙስናን በተዋጋበት ነበር። ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት ይህን ህግ እንደ አንድ ደጋፊ ሪሶርስ ሊያየው ይችል ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት አልወደደውም። አልወደደውም ብቻ ሳይሆን ምላሹ አስገራሚ ነው። ይህ ህግ ለዋናው ቤት ቀርቦ ድምጽ እንዳይሰጥበት ወይም ድምጽ ሲሰጥ እንዲወድቅ የሚታገለው ለሽብር ስራ አልተባበርም በሚል ነው። ይህን ካርድ በኮንግረስ ፊት መዞ የሚያውለበልበው የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ድርጊቱ አያፍርም። ለመሆኑ ከናንተ ጋር ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አልተባበርም ማለት ምን ማለት ነው? የሚከተሉት ጥያቄዎች ሊነሱ ይገባል።

ለመሆኑ መንግስት በሌላ ጉዳይ በምን ጉዳይ ነው ትብብሩ የሚቀጥለው?  በምን በምን ጉዳይ ነው ከአሜሪካ ጋር የሚተባበረው? ለምን? ሌላው ጥያቄ ደግሞ ነገ የአውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ተመሳሳይ ሪዞሉሽን ቢያሳልፉ ከነዚህ አካላትም ጋር የኢትዮጵያ መንግስት መርህ ከናንተ ጋር በሽብር ጉዳይ አብሬ አልሰራም ከሆነ ምላሹ፣ የአፍሪካ ህብረት ሆኖለት ተመሳሳይ ህግ ቢያወጣ ከናንተ ጋር ሽብርተኛ አልዋጋም ከሆነ ነገሩ የዚህ የኢትዮጵያ መንግስት መርህ መጨረሻው  ምን አንድምታ አለው? ለምን ሌሎች ጉዳዮችን ኣላነሳም? በንግድ በመሳሰሉት ጉዳዮች አብሬ አልሰራም ሳይሆን ተለወጥ ተስተካከል ካላችሁኝ ሽብርተኛ አልዋጋም ማለት ሽብረተኝነት የእኔ ስጋት አይደለም እኔና ሽብርተኞች የግል ጸብ የለንም እንደማለት ነው። እስከዛሬም በጸረ ሽብር ስራው የነበረኝ ተሳትፎ ችግሩን እንደራሴ ችግር ኣይቼው ሳይሆን ከእናንተ ድጋፍ ለማግኘት ነው እንደማለት ነው። H.Res 128 ካለፈ ከአሜሪካ ጋር አልሸባብን ኣልዋጋም ማለት አሜሪካ ከእኔ ጋር የጸረ ሽብር ስራ ለመስራት ካሰብሽ መጀመሪያ እሴቶችሽን ሰብረሽ ነይ እንደማለት ነው። የውስጥ አሸባሪ ብሆንም፣ ሙስናና ህገወጥ ግድያ ባካሂድም ይህንን ስራ ተው የምትይ ከሆነ አልሸባብን ኣልዋጋም ማለት የአሜሪካንን እሴት መስበር ነው።

የአይሲስ (IS) ህልም

ለኮንግረስም የቀረበው ጥሪ ይሄ ነው። አሜሪካ እንደ ልእለ ሃያል ሃገር የነጻነት፣ የዴሞክራሲ እሴቶቿ የውጭ ፖሊሲዋን ይገዛዋል። ለዚያም ነው ይህ ህግ በውጭ ጉዳይ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ የጸደቀው። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ውትወታ ከአሜሪካ እሴቶች ጋር የሚጋጭ በመሆኑና ሙገታው ራሱ ኣሳፋሪ በመሆኑ ተቀባይነት ያገኛል ብየ አላምንም። በመሰረቱ አልሸባብን የምንዋጋው ለአሜሪካ ብለን አይደለም። እንዴውም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሽብር እንቅስቃሴ ከማንም በላይ የሚያሳስበን ሰዎች እንደመሆናችን የዓለም ኣቀፍ ትብብር መሪዎች አስተባባሪዎች ልንሆን ይገባል። ኣይሲስ የተባለው አለማቀፍ ኣሸባሪ ቡድን ከረጅም ጊዜ ህልሙ መሃል ኢትዮጵያን የእስልምና መንግስት አገር ማድረግ ነው። ዝቅ ሲል የሚታየውን ስእል መመልከት የበለጠ ገላጭ ነው።

አሸባሪነት በአፍሪካ ቀንድም ይሁን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የኛ የራሳችን ችግር ነውና ይህ ጉዳይ ዋና የጸጥታችን ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባል። በምንም ዓይነት ለድርድር የምናቀርበው እጀንዳ መሆን የለበትም። ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ብዝሃነት ያላት ሃገር ሆና በተለይ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ለረጅም ጊዜ በሰላም የኖረባት ኣገር መሆኗ ለዓለም ምሳሌ ያደርጋታል። ይህ ሰላም ተጠብቆ የሚቆየው ታዲያ ኣክራሪነትን ሳንታክት ከተዋጋን ብቻ ነው። በመሆኑም አክራሪነትን በየትኛውም ደረጃ የመከላከላችን ተግባር ለድርድር የሚቀርብ የደህነታችን ኣጀንዳ መሆን ኣይጠበቅበትም።

የአሜሪካ እንደራሴዎች ከዚህ ከኢትዮጵያ መንግስት ውትወታ የሚረዱት ነገር አለ። አንደኛው ይህን ማስፈራሪያ ወይም ማሳመኛ አድርጎ መምጣቱ የሚያሳፍር ሲሆን ሌላው ዋና ጉዳይ ደግሞ ይህ መንግስት በሃገሩ በዜጎቹ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽም በመሆኑና በውስጥ አለመረጋጋት የተመታ በመሆኑ ዘላቂና ታማኝ የአሜሪካ ጓድ ሊሆን እንደማይችል ነው። የዴሞክራሲ ምህዳሩን አጥብቦ ህዝቡን በብሄር ከፋፍሎ የሚያፋጅ መንግስት ጸረ ሽብር የሆነ ሃይል እንደማይሆን ይገመግሙታል። የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የቅቡልነት (legitimacy) ችግርና የመታመን (trust) ችግር እንዳለበት ስለሚረዱ ይህ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ቀርቶ በራሱ ሃገርም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ያመጣል ብለው አያምኑም።

በቀጣናው ሰላም መረጋጋትን ለማምጣት ቅቡልነት በጣም ዋና ጉዳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት በፍጹም የቆረጠና የገባው የጸረ ሽብር ሃይል ሊሆን አይችልም። ፕሬዚደንት ትራምፕም ይህንን አይደግፉም። በሽበርተኞች ላይ የጸና አቋም ያላቸው ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሃቀኛ ጓድ ያስፈልጋቸዋል። የጸረ ሽብርን ስራ መነገጃ ካደረገ መንግስት ጋር ግንኙነት አይሹም። በመሆኑም ይህ ሎቢው ይሳካል ብሎ ማመን ይከብዳል። ለማናቸውም ይህ ህግ ይጸድቅ ዘንድ የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ የአሜሪካንን እንደራሴዎች ማነጋገር ማስረዳት ያስፈልጋል። አሜሪካም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን መቆሟን ታሳያለች ብለን እናምናለን። ዛፍ ላይ ወጥቶ የተቀመጠበትን ዛፍ ለመቁረጥ አየገዘገገዘ ካለ መንግስት ጋር የሚተባበር የለም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ገለታው ዘለቀ (geletawzeleke@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule