• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ

September 30, 2017 12:06 am by Editor Leave a Comment

ህወሐት በትግል ፕሮግራሙ የአማራን ያክል  የሚጠላው ሌላ  ህዝብም ሆነ አካል  እንደሌለ በግልጽ ያስቀመጠ ድርጅት ነው። የአማራ ህዝብ መሬት እያረሰ የሚኖር ደሀ ህዝብ ቢሆንም በህወሐት የምስረታ  ሰነዶች እንደ ገዥ ብሄር ተፈርጆአል።

አስገራሚው ነገር  አማራ ንጉሱንም ሆነ ደርግን በማስወገድ ትግል ከሌሎች ህዝቦች እኩል ድርሻ የነበረው ህዝብ ነው። እንደ ህዝብ በህወሐት የሚጠላው በተጨበጠ ምክንያት አይደለም። ህወሐት  የአማራን በሌሎች እንዲጠላ ካደረገባቸው የተደራጁ  ስብከቶች በተጨማሪ የብሄረሰቡን ማንነት የሚያዳክምባቸው ልዩ ልዩ እርምጃዎችንም ወስዶአል። አንዱ ሴቶች  ፍላጎታቸው ሳይጠየቅ የረጅም ግዜ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ማድረጉ ነው። በዚህም እኤአ 2007 የህዝብ ቆጠራ የህዝብ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በ3 ሚሊዮን የቀነሰ ብቸኛ ህዝብ ሆኖአል። ሌላው በትግራይ  ክልል የልዩ ወረዳ አስተዳደር ክብር የሚገባቸው ልዩ ልዩ ብሄረሰቦች እያሉ ህወሐት አማራ ክልል መጥቶ የልዩ ዞን ፍላጎት ቀስቀሰሽና አስፈጻሚ መሆኑም ከዚሁ  አማራን ለማዳከም ካለው ጽኑ ፍላጎት ጋር ይያያዛል።

የአማራን ክልል መሬት በጉልበት ወደራሱ የማካለል ስራም ሌላው ተግባሩ ነው። ራሳቸውን በአማራነት የሚገልጹ ሰዎችን በግፊት ወደ ትግሬነት የመቀየር ስራም ሰርቶአል። ህወሐት በፕሮግራሙ ውስጥ አማራን ግንባር ቀደም ጠላቴ ነው ብሎ ከመጻፍ ጀምሮ በተከታታይ በዚህ ህዝብ ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ግፎች መነሻቸው ምንድን ነው?

የመጀመሪያው መሰረታዊ ምክንያት ህወሐት ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ፈጽሞ ማየት አለመፈለጉ ነው። ይህ ጥላቻ  ምንጩ የወራሪው ኢጣልያ አገልጋይ ከነበሩ ጥቂት  ባንዳ  የትግራይ ልጆች ነው። እነዚህ በቀድሞው  የህወሐት አባል በአቶ ገብረመድን  አጠራር ሻምቡሽ  እየተባሉ የሚጠሩት የትግራይ ባንዳዎች በልጆቻቸው በኩል ስብከቱን በማጉላት  በአሁኑ ወቅት ብዙ ተከታይ አግኝተዋል። የአማራ ህዝብ ደግሞ ፖለቲከኛ ሆነ ደሀ ገበሬ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሀገሪቷን  ከወራሪ ሲከላከል የቆየ ህዝብ ነበር። በዚህም ቂም ተይዞበታል።

ብዙዎች የዋሆች ህወሐት ኢትዮጵያዊ መባል ካልፈለገ  ለምን ታዲያ  ሁሉን አድራጊ በሆነበት በአሁን ወቅት መገንጠልን አይፈጽመውም  የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ። መልሱ የትግራይ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የስነልቦና የበላይነቱ እስካልተነካበት የመገንጠል ፍላጎቱን ገሀድ አያወጣም የሚል ይሆናል። አዎ እንደ ነብር ደምህን እየመጠጠ ይቆያል። ደምህ ካለቀ ወይም አሻፈረኝ ካልክ ግን  ያኔ ይተገብረዋል።

ሁለተኛው ምክንያት የተለመደው የከፋፍለህ ግዛ ባህሪው ነው። ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን ኣስፈራርቶ ለመግዛት  የሚፈሩት ጠላት ሊፈጥርላቸው ይገባል። ለዚህም አማራን አስቀምጦላቸዋል። በሁለተኛነትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህብረት እንዳይፈጥሩ ማድረጊያ ስልቱም ነው። ይህ ስልቱም ከጠበቀው በላይ ሰርቶለታል። በዚህም  የአማራ ህዝብ ለትውልዶች ከኖረባቸው አካባቢዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች  ተፈጽሞበታል። በኦሮሚያ፣ ደቡብ  ብ/ብ/ህ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  ውስጥ የተፈጸሙትን ግድያዎችና ማፈናቀል መጥቀስ ይቻላል።

የአለም ህዝቦች መልቲ ካልራሊዝምን እንደ ሀብት በሚቆጥሩበት  በዚህ የስልጣኔ ዘመን አባቶቹ የጣልያን ሻምቡሽ ሆነው የተነገራቸው ስብከት ላይ ተቸንክሮ የቆመውን ህወሐት በተግባር በቃ ልንለው ይገባል። አለበለዚያ ግን የሰሞኑ የአለም ባንክ  ይፋ ያወጣው የኢትዮጵያ ክልሎች  የመንገድ ግንባታ ግስጋሴ የ 10 ዓመት ሪፖርት በግልጽ እንዳስቀመጠው (ትግራይ ክልል አንደኛ እንዲሁም አማራ መጨረሻ) ህወሀት የአማራንም ሆነ ሌሎች ህዝቦችን ደም መምጠጡን ይቀጥላል።

ያሬድ አውግቸው (yaredawgichew@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule