ወደ ኋላ ሄዶ አበባ ሲፈካ፣ ጊዜ ሲተካካ፣ ልጅ ስልጣኔ መጥቶ በራችን ሲያንኳዋካ፤ ከባህል ጥል ገጥሞ ለመኖር ለብቻው፣ ማየት ማስተዋል ነው፣ ኧረ የሰላም ያለህ ተው አይሆንም ሲለው ባህል ሲማጠነው ደባል እንዲሆነው፤ (ቀሪውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ትዝታ በ60/በስድሳ
የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤ በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሃከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሃት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልጹ ጥቂቶች በብዙሃኑ ደም ዎኝተው … [Read more...] about የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ "ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?" ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር። ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው … [Read more...] about ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው
የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)
በድሉ ዋቅጅራ ‹የሌላቸው ባለቤቶች› የሚል ቅራኔ ውስጥ የገባው ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ተነሥቶ ነው፤ አንዳንዴ ሁኔታዎች እያስገደዱን ቅራኔዎችን እንቀበላለን፤ አንድ ጌታ አሽከራቸውን ይጠሩና ባላገር ወደሚኖሩ እናታቸው ዘንድ ይልኩታል፤ ነገር ግን ‹ሞተው ከሆነ እንዳትነግረኝ› ብለው አስጠንቅቀውት ይሄዳል፤ ሴትዮዋ ሞተው ይደርሳል፤ ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው፤ ሲያንሰላስል ብዙ ቀናት ከቆየ በኋላ ጎፈሬውን ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ይላጭና ግማሹን ብን አድርጎ ያበጥርና ጌታው ዘንድ ይቀርባል፤ አንዴ ጎፈሬውን እየነካካ፣ አንዴ የተላጨውን እየዳበሰ ጥያቄዎቻቸውን ሲመልስ፣ ጌታው ተቆጡና ‹ምንድን ነው የምታድበሰብሰው አርፈው እንደሁ በወጉ አትነግረኝም!› ብለው ሲጮሁበት ‹አዬ ጌታዬ አርስዎ መቼ በወጉ ላኩኝና!› ብሎ መለሰላቸው። የበድሉ ‹የሌላቸው› በግማሽ እንደተላጨው ጸጉር ነው፤ … [Read more...] about የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!
ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቅራኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒቲው ሊቀመንበር እና በማህበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 /2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል፡፤ በቅርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአግባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ በመሰንዘራቸው ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጭት ስብሰባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአምባሳደር መሃመድ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!
በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው?
ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል .... "ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል ... ሀበሻ የድሮዎቹ የሉም ... ውድ የሆነውን የሰውን ደም … [Read more...] about በጭካኔ እየተገዳደልን፣ ወዴት እየሔድን ነው?
Fair trial for Ethiopian co pilot Hailemedhen Abera
Copilot Hailemedhen Abera has requested political asylum in Switzerland. The copilot’s action represents the voices of the voiceless Ethiopians who have lived under tyranny for the last 23 years. The action taken by Hailemedhin was an absolute necessity as the world turns a blind eye to the plight of the Ethiopian people and gives full support to the repressive leaders of Ethiopia. Despite the egregious breach of human rights by the regime as exposed on different occasions by various Human Right … [Read more...] about Fair trial for Ethiopian co pilot Hailemedhen Abera
ጥላ መጽሔት 9ኛ ዕትም
ጀርመን አገር የምትታተመው ጥላ መጽሔት 9ኛ እትም ለንባብ በቅታለች። ለወቅታዊው ሁኔታም ልዩ ትኩረት ሰጥታለች። (ሙሉውን መጽሔት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጥላ መጽሔት 9ኛ ዕትም
ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?
ኢህአዴግ "አልመረመርም፣ አልበረበርም" በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች "የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ … [Read more...] about ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?
ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር። EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ … [Read more...] about ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ










