አርእስቴን በጥቂቱ ያልኩበት ምክንያት የተነሳሁበት ርእስ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ ስለማውቅ ነገር ግን ልንወያይበት እንደሚገባ በመረዳቴ ለውይይት መክፈቻ ይሆን ዘንድ እንጂ እኔ ባለኝ እውቀት ብቻ ሙሉ በሙሉ ልተነትነው እንደማልችል በማመኔ ነው። ይህም ቢሆን እንደዜግነቴ ሃገሬን ለዘመናት ለተቆራኛት የድህነት ችግር መንስኤና መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በመጠኑ ለመተንተን ለመሞከር ነው። በአንድ ሃገር ወይም አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ ለግላዊም ሆነ ማህበራዊ ፍላጎቶቹ በበቂ ሁኔታ መሟላት አጣጥሞና አስማምቶ በእኩልነት ሊያኖረው የሚችል ህግና ስርዓት በብዙሃኑ ፍላጎትና ስምምነት ላይ ተመስርቶ መቀረፅ አለበት። የሰውን ልጅ ከእንሰሳት የሚለየውና የተሻለ ያደረገውም አንዱ ሌላውን በእኩልነት ማየቱ እንዲሁም ሰው በጉልበቱ የበላይ መሆን የማይችልበት ሁናቴ መፈጠሩ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ”
ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች
በመጪው ምርጫ የግብጽ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ የሚባሉት የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ፊልድ ማርሻል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሩሲያ ጋር የ2ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ድርድር ላይ መሆናቸው በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ረቡዕ ሞስኮ የገቡት አል-ሲሲ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር የመሣሪ ውሉን በተመለከተ የሁለት ለሁለት ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ ከግብጽና ከሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የድርድር ውሉ ዋና አካላት ናቸው፡፡ “ጉብኝታችን በግብጽና ሩሲያ መካከል የወታደራዊና የቴክኖሎጂ ልማት ስምምነት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ መክፈት ይሆናል” ያሉት አል-ሲሲ ትብብሩን ለማፋጠን ተስፋ እንዳለቸው ጠቁመዋል፡፡ ይጸድቃል የተባለው ይህ ስምምነት ከሩሲያ በኩል ድጋፍ እንዳለው ፕሬዚዳንት ፑቲን አል-ሲሲን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡ “የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን … [Read more...] about ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች
የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ
ከራሳቸው አልፎ ባህር ውስጥ ቢደፉት የማይጎድል ሃብት አላቸው። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የነዳጅ ክምችት አግኝተው ጉድጓድ ለመቆፈር ተቃውሞ በመነሳቱ ሪፈረደም አካሂደዋል። ከነዳጅ ይልቅ ውሃ ውስጥ ያለው ህይወት አንደሚብስባቸው በማስታወቅ ድምጽ የሰጡ በመብዛታቸው ነዳጁ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል። ይህ ዜና በተሰማበት ሰሞን ያልተገረመ አልነበረም። ሃብት ካለ ምን ችግር አለ? አንግዲህ እንደዚህ "ብር ይብቃን፤ አሳና የባህር ውስጥ ፍጡራን እንቁራሪትን ጨምሮ ይበልጡብናል" የተባለባት አገር ኖርዌይ ናት። በተቃራኒው ደግሞ ብር ካየ የሚገባበትን ጉድጓድ፣ የሚፈጽመውን ጥፋት የማይለካው ኢህአዴግ የሚመራት ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ስደተኞች ኖርዌይን ተጠልለዋል። ከአራት ሺህ በላይ ወገኖች ኖርዌይ በጡረታ መልክ እየቆረሰችላቸው ወይም ስራ እየሰሩ ህይወታቸውን ይመራሉ። በኖርዌይ መወልወያና … [Read more...] about የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዮጵያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል፣ እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዮጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ … [Read more...] about የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት ... ዶናልድ ያማሞቶ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዴት እዚህ ተደረሰ? የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና … [Read more...] about መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?
የጅዳ ቆንስል ሃላፊ ዘነበ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!
* ትናንት ረፋዱ ላይ በገደምዳሜ "ጉልቻ ቢቀያየር ..." ብለን ያንሹካሾክነው መረጃ ተረጋገጠ! * ለጊዜው ቆንስል ጀኔራሉን ተክተው በጊዜያዊነት ቆንስል መስሪያ ቤቱን ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚያስተዳድሩት በቆራጥ አመራራር ብቃታቸው የማይመሰገኑት ቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ናቸውም ተብሏል። * ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ትናንት ምሽት ጉዳዩን ለማሳወቅ የኢህአዴግ ድርጅት አባላት ስብሰባ ጠርተው እንደነበርና አብዛኛው አለመገኘታቸው ታውቋል። ድርጅት አባላት በተለይም ከጎናቸው የማይጠፉ የነበሩት ተጽዕኖ ፈጣሪ የህወሃት አባላት እንኳ አልተገኙም ተብሏል። አቶ ዘነበ ከበደ በቆንስሉ ዙሪያ የህወሃት አባላትን አምባገነንነትን በማውረድና በማቀዝቀዝ፣ በሙስና፣ በድለላ፣ በማጭበርበር ስራ በቆንስሉ ዙሪያ የነበሩትን በማጥፋት እና በሌብነት አካባቢውን በማጽዳት ይታወቃሉ። ህግ አዋቂ ሆነው … [Read more...] about የጅዳ ቆንስል ሃላፊ ዘነበ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!
Foreign regimes use spyware against journalists, even in U.S.
Mesay Mekonnen was at his desk, at a news service based in Northern Virginia, when gibberish suddenly exploded across his computer screen one day in December. A sophisticated cyberattack was underway. But this wasn’t the Chinese army or the Russia mafia at work. Instead, a nonprofit research lab has fingered government hackers in a much less technically advanced nation, Ethiopia, as the likely culprits, saying they apparently bought commercial spyware, essentially off the shelf. This … [Read more...] about Foreign regimes use spyware against journalists, even in U.S.
The Secret (ሚስጢሩ…)
የጤንነት ሚስጢር ማንም ህመምተኛ የወሰደው ኪኒን ያድነኛል ብሎ ከቻለ ለማመን ስላስተላለፈ ለአዕምሮው መልዕክት በርግጥም ይችላል ጥሩ ፈውስ ማግኘት በሰውነትህ ውስጥ ህመም የሚኖረው በሽታውን ትኩረት ስትሰጠው ብቻ ነው የጤና መዛባት ስሜት ከተሰማህ ህመሙን አታስፋ ለሰዎች ተናግረህ ስዎች ስለህመም ሲያወሩ ማዳመጥ መንገዱን መክፈት ነው እንዲባባስ ይበልጥ ህመማቸው ጸንቶ ቢወተውቱ እንኳን በመልካም ነገሮች ለውጠህ ወሬውን ባነጋገር ብቃት ትችላለህ ማዳን የአዕምሮ ፈጠራን የእርጅቻለሁ እምነት ከራስህ መንጭቀህ ይገባሃል ማውጣት ወጣት ነኝ አሁንም ብለህ በማተኮር ደስታን ጤናን ይዘህ ትችላለህ መኖር ስለዚህ አረጀሁ ብለህ በመጨነቅ ህመም እያወራህ እድሜህን ከመሰቅ ራስህ ራስህን በዚህ ዘዴ ጠብቅ ****************************** The Secret … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ስደበኝ
ጉሮሮህን ጠራርገህ፤ ምላስህን ሳልና እንደ ሽንኩርት የምልጠው እንደ ኪኒን የምውጠው ጥሩ ቃላት ምረጥና እንደ እበት ሳትለድፍ እንደ ጭቃ ሳትለጥፍ ልክ ልኬን ንገረኝ ደስ ይበልህ…ስደበኝ ባንተ መለኪያ ተለክቸ ባንተ መነፀር ታይቸ ሙሉ እንደማልሆን አውቃለሁ ባልተገራ ምላስህ ባዶ በሆነው ራስህ ማንነቴን ስትናገር፤ ማንነትህን አያለሁ እና…አንተን ደስ እንዲልህ የተጫንከው እንዲቀልህ ……………..ስደበኝ ለአቶ ዓልምነው መኮነን የአማራ ክልል ም/ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ … [Read more...] about ስደበኝ
118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል
ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ያገኛሉ:: … [Read more...] about 118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል










