የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤ አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤ ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ … [Read more...] about ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ
ኢህአዴግ – ሌባ ወይስ አገር አስተዳዳሪ?
ከላይ የጠየቅነው ጥያቄ ዛሬ የተነሳ አዲስ ነገር አይደለም። ኢህአዴግ መሰረቱን ዝርፊያ ላይ ያደረገ አገር አስተዳዳሪ መሆኑ ግብሩ ራሱ ምስክር ነውና "ሌባ አገር አስተዳዳሪ" ስለመሆኑ ማስተባበያ ሊያቀርብም አይቻለውም፤ አያስፈልገውም። ሌብነቱ አገርንና ህዝብን ወደ ገደል እየሰደደ መሆኑ ግን ሁሌም የሚያስጨንቅ ነውና ዛሬ እንደ አዲስ አነሳነው እንጂ!! ኢህአዴግ ግዙፍ፣ ሃብቱ በዶላር ካልሆነ በብር የማይቆጠር፣ በህገወጥ ንግድ ሰላማዊ ነጋዴዎችን የሚውጥ፣ ለብቻው መግቢያና መውጪያ የተዘጋጀለት፣ የተለየ ጨረታና የነጻ ቀረጥ እድል የሚበጅለት፣ በየትኛውም ተቋም እንደፈለገ መጋለብ የሚችል ልጓም አልባ የሆነ፣ በፈለገው ቦታና ማህበረሰብ ጥቅም ላይ እንዳሻው ከበሮ እየደለቀ የሚጨፍር፣ ጡሩምባ ይዞ የሚያንጠራባ፣ የፈለገውን ማስወገድ፣ ማሳገድ፣ ማስከፈት፣ ማዘጋት የሚችል፣ ድንበርና ኬላ … [Read more...] about ኢህአዴግ – ሌባ ወይስ አገር አስተዳዳሪ?
ጃፓን + ኢህአዴግ – ቻይና = መንበርከክ
ከቻይና ጋር የጀመሩት መወዳጀት ሥር ሰድዶ በሁለት እግሩ ከመቆሙ በፊት አቶ መለስ በሞት ከተለዩ በኋላ የኢህአዴግና የቻይና ግንኙነት በርካታ መንታ መንገዶች እየገጠሙት መጥተዋል፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ገንዘብ በበጀት ድጎማም ሆነ በዕርዳታ የሚሠጠው ኢህአዴግ ምዕራባውያን ከቻይና ጋር ካላቸው ፍጥጫ አንጻር እየገባበት ያለው አጣብቂኝ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል፡፡ “ምርጫው በምርጫ” እየተወሳሰበበት የመጣው ኢህአዴግ በአንድ በኩል የአሜሪካንን ፍላጎትና ጥያቄ መፈጸምና ማስፈጸም፤ በሌላ በኩል ደግሞ አፈናውን ለማጠናከርና የግዛት ዘመኑን ለማርዘም ከቻይና የሚያገኘው በቅድመ ሁኔታ ያልታሰረ “ጥቅም” በሁለት ጽንፍ ወጥረውታል፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ “ወጣሪ” ብቅ ብሎ በመንታው መንገድ ላይ ሌላ መንታ ፈጥሮበታል - ጃፓን! ቻይና በተለይ በአፍሪካ እያደረገች ያለችው የንግድ እንቅስቃሴና … [Read more...] about ጃፓን + ኢህአዴግ – ቻይና = መንበርከክ
በክርስትና ላይ ጥናታዊ ምርምር ሲያደርግ የነበረው ሰው በራሱ ሕይወት ላይ ምርመራ ተደርጎበት እጁን ሰጠ!!!
ወንድ ልጅ ሲወለድ አባት ለተወለደው ልጁ ጠብ - መንጃ (ጠመንጃ) ለመግዛት ደፋ ቀና ከሚባልበት አካባቢ ነው ተወልጄ ያደኩት፡፡ ይህ የሚደረገው ደግሞ በቂ ሃብት ስላለ ሳይሆን “ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ እንዝርት አቅርቡለት ይፍተል እንደ እናቱ” የሚለው የንቀት አባባል በልጁ ላይ ሲያድግ እንዳይደርስበት ከወዲሁ ለማዘጋጀት ነው፡፡ እንዲያውም ልጅ በልጅ ተሸንፎና ተመትቶ እያለቀሰ ወደ ወላጆቹ ለእርዳታ ሲቀርብ አልቃሻ ልጅ አልወድም/የለኝም ተብሎ በጥፊ ወይም በአለንጋ ይደገማል፡፡ በለው! ትሸነፍና ወዮለህ! እንዳታሳፍረኝ! የሴት ልጅ! (ከወንድ ብቻ የተወለደ ያለ ይመስል)፣ ሊጥ አትሁን!፣ አስለቅስ እንጂ አታልቅስ!፤ አትበለጥ! ኩራት እራቱ! ከአረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂ . . . ይሻላል! ከማን አንሼ!. . . ወዘተ እየተባልንና እያልን ነው እኛ ኢትዮጵያውያን … [Read more...] about በክርስትና ላይ ጥናታዊ ምርምር ሲያደርግ የነበረው ሰው በራሱ ሕይወት ላይ ምርመራ ተደርጎበት እጁን ሰጠ!!!
የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ፤ መሪዉን በማስተካከል ከማያውቁት መጨረሻ ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤ የተከተላቸውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ መዝገባቸው ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፊት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር፤ ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ … [Read more...] about የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
በመሠረቱ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ስለ አብዮቱ “ እኛና አብዮቱ “ የሚል መጸሐፍ ጻፉ የሚል ዜና ስሰማ ፣ መጸሐፋቸው እንደ ሌ/ኮ መንግሥቱ ኃይለማርያም መጸሐፍ በቅጥፈት የተሞላ አይሆንም ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ በነገራችን ላይ የሻምበሉን መጸሐፍ ገና አላገኘሁትም፣ ነገር ግን አንድ ወዳጄ ከምዕራፍ 13–16 ያሉትን ገጾች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ስለሠጠኝ አየተገረምኩኝ አነበብኳቸው፡፡ ሻምበሉን ምን ነካቸው ብዬም እራሴን ጠየኩኝ፡፡ ደራሲው በትምህርታቸው እንዳልገፉ ይገባኛል ፡፡ ሆኖም ግን በትምህርት ያለመግፋት ትንታኔ ላይ ችግር ይፈጥር እንደሆን እንጂ ፤ “ በእጅ የገባን መረጃ ” አሳስቶ ማቅረብ ከምን ሊመነጭ እንደሚችል ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም፡፡ ፍቅረሥላሴ መረጃው በእጃቸው ከሌላቸው አርፈው መቀመጥ አለባቸው እንጂ ባልሆነ ማስረጃ አንባቢን ማሳሳት … [Read more...] about የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ አሳሳች መረጃዎችና የተምታታ አስተያየት
እኔና አንቺ… ፫
በሕዝብ ተጋርደን ባ’ገር ተከልለን ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን። እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ እኔም ያን አይደለሁ አንቺም ያቺ አይደለሽ። እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ ጭራሽ ከሚለየን ኑሮአችንን ገፎ ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ። ****************** እኔና አንቺ … ፩ - ፖለቲካና ስደት እኔና አንቺ…፪ - ሀገርና ክህደት … [Read more...] about እኔና አንቺ… ፫
በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ … [Read more...] about በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ
አድዋ ለኔ
እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው። በአሜሪካ ሆኜ የአድዋን በዓል አከበርኩ። የኢትዮጵያዊያን ድረገፆችን እየተመላለስኩ ቃኘኋቸው። ሬዲዮኖችን አዳመጥኳቸው። የስልከ ልውውጦችንና የእንግዶችን ሃሳቦች ተከታተልኩ። ስደሰት፣ ሳዝን፣ በጣም ስደሰትና በጣም ሳዝን ዋልኩ። ሲመሽና የምኝታ ሰዓቴ ቀርቦ ባልጋዬ ላይ ስጋደም፤ እንቅልፍ ቶሎ አልወስድህ አለኝ። መገለባበጡ ለውጥ አላመጣ ሲል በሃሳብ መዋተቱን ተያያዝኩት። አድዋ ለኔ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከዕለቱ ወደላይና ወደታች መዋዠቅ ጋር ተዛምዶ አፋጠጠኝ። እውነት አድዋ ለኔ ምንድን ነው? አድዋ ከመቶ ዓመት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ነው። በዚያ ጊዜ የተካፈሉትና የነበሩት አሁን የሉም። አድዋ በአንድ የሀገራችን አካባቢ የተፈፀመ ጉዳይ ነው። ታዲያ ለኔ ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ ላለሁት ምኔ ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ ስመላለስበት እኩለ ሌሊት ሆነ። ለካስ … [Read more...] about አድዋ ለኔ
የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ
በእርግጠኝነት ኢትዮጵያዊ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻም አይደለም በየትኛውም ዓለም ያለ በቅኝ ግዛት ቀንበር ፍዳ ያየ የትኛውም የሰው ዘር ጭምርም እንጅ፡፡ ይህን አንጸባራቂ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ካስመዘገበ እነሆ ነገ የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም 118 ዓመቱን ይይዛል፡፡ ይህንን ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ ? የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡ ዐፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከነበረበት አልፎ … [Read more...] about የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ









