ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ አለበለዚያ ድንጋይ ብለው ይጥሉሻል ይባላል! ለራስህ እውቅበት፣ ትርጉም እንዳታጣ ለማለት ነው፣ መቼም ይህን ታውቁታላችሁ! ነገሩን ወደ ዘመናችን ዓለም አቀፍ ፖለቲካ ስናዞረውና ልንማርበት፣ ተመክሮ ልናገኝበት ከፈለግን እንደሚከተለው ነው። ሰው ህዝብ ሀገር ለራሱ ሲል፣ ወዳጅ ረዳትና ነገረፈጅ በዓለም መድረክ ላይ አለኝ በሎ፣ በራሱ ሳይሆን በነርሱ ተማምኖ ነገር ዓለሙን ከተወው፣ ለራሱ ሲል ካላወቀበት የኋላ ኋላ ጉድ ጉድ ተብሎ፣ መቼም ምን ይደረግ ተብሎ ይተዋል፤ ይወድቃል፤ ለወሬውም ይረሳል ማለት ነው። ጉድ አንድ ሰሞን ነውና ሊቢያ ጉድ ጉድ ሲባል ከርሞ ዛሬ ተረስቷል! ኢራክማ የት የሌለ፤ ስለ አፍጋኒስታንም ለማለገጫ ከልሆነ በስተቀር ብዙም ልብ አይባል! ግብጽም ከሰሞኑ ትንሽ ሰንበት ብሎ ይረሳል፤ የመን ተረስቷል፣ ሲሪያም ጨዎቹ(ፖለቲከኞቹ) … [Read more...] about ጨው ለራስሽ ስትይ ጣፍጪ!? ኡክሬይን
ሙሰኞችና “ሙሰኛው” ፀረ ሙስና
“ . . .የኢትዮጵያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የህዝብንና የመንግስትን ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል ክስ የመሰረተባቸውን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን . . . . . . “ የኢቲቪ ዜና “. . . ጉድ ፈላ በቃ ቀጥሎ ሴትዮዋ ነች . . . " የዋህ ኢትዮጵያውያን “. . . እባካችሁ በጥቂት ሺህ ብሮች የወር ደሞዝ የህዝብ አገልጋይ ነን እያላችሁ የሰባት ሚሊዮን ብር መኪና አትንዱ . . .” አፈጉባኤው “. . . የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስናን በማጋለጥ ጋር በተያያዘ በታሸገ ውሃ ተመርዘው ነው የሞቱት መባሉን ባናረጋግጥም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በኦሮሚያ ክልል መንግስታዊ ስብሰባዎች የታሸገ ውሃ መቅረብ መቆሙን አውቀናል . . . “ ለስርዓቱ እጅግ የቀረቡ የመንግስት ጋዜጠኞች ባለፈው ሰሞን ጥቂት የመንግስት … [Read more...] about ሙሰኞችና “ሙሰኛው” ፀረ ሙስና
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ዘገባ በግድብ ሥራ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ታላላቅ ግድቦችን በመሥራት ላይ የሚገኙ ታዳጊ አገራት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተነገረ፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረገው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው ዘገባ መሠረት አገራቱ ለከፍተኛ ዕዳ እና ከዚያ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ችግሮች የሚጋለጡ መሆናቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ “ለሕዝባችሁ የምታስቡ ከሆነ ገንዘቡን ለሌላ ተግባር አውሉት” በማለት ምክርም ሰጥቶዋል፡፡ እኤአ ከ1934ዓም ጀምሮ በ65 አገራት የተገነቡ 245 ግድቦችን በማካተት የተደረገው በዓይነቱ ለየት ያለው አጠቃላይ ጥናት በቅርቡ እየተገነቡ ያሉትን ታላቅ ግድቦችንም ያካተተ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ካለው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጀምሮ እስከ ብራዚሉ የአማዞን ቤሎ ሞንቴ የግድብ ፕሮጀክቶችን የሚገነቡት ታዳሽ ኃይልን አጠቃቀም ለማጎልበት እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለመጨመር በሚል እንደሆነ የጠቀሰው ጥናታዊ … [Read more...] about የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ዘገባ በግድብ ሥራ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ
የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ። በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣ እንደገና መልሰን የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው። በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን ጠርቶ የህልም ፍቺ … [Read more...] about ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ
ኔልሰን ማንዴላና ህፀፆቹ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትና የገዢው የኤኤንሲ /የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ/ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩትን ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ ከሦስት ትውልድ ያላነሰ አፍሪካዊና የሌላው አህጉር ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። እኝህ ሰው ይበልጥ ከሚታወቁባቸው ጉዳያቸው ውስጥ በአገሪቱ በነበረው አፓርታይድና ዘረኛ ስርዓት ለ27 ዓመታት መታሰራቸው ብሎም ከእስር በኋላ ለአሳሪዎቻቸውና በብዙ ሚሊዮን ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንን አንገብግበው ለገዙ የዘር መድሎ ለፈፀሙ እንዲሁም የግርፋት የግድያና የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን ለሰሩ ነጭ በዝባዦቻቸው ይቅር ማለታቸው ዋነኛው ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ኔልሰን ማንዴላና ህፀፆቹ
“በዴሞክራሲ” ስም የሚደረግ የመሬት ነጠቃና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ
በአይነቱ የመጀመርያ የሆነ የውይይት መድረክ የካቲት 27 2006ዓም/March 6, 2014/ በኦስሎ፣ ኖርዌይ ከተማ ተደረገ። Frontline Club Oslo በተባለ ድርጅት አማካኝነት በኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ስም እየተካሄደ ያለውን የመሬት ነጠቃ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት በመጥራት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በስብሰባውም ላይም ከውጭ ጉዳይና ከሌሎች መስሪያ ቤቶች፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለጉዳዩ ቅርበት ያላችው አካላት ተገኝተዋል። ስብሰባውን የጠራው ድርጅት በመወከል ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ማርየስ ቮንዳርፈር እንደተናገሩት Fronline Club የተባለ ድርጅት በኦስሎ የተቋቋመው በያዝነው ዓመት ሲሆን አላማውም በዓለምአቀፍ ታዋቂ የፊልም እና የፎቶግራፍ ባለሙያዎችን፣ … [Read more...] about “በዴሞክራሲ” ስም የሚደረግ የመሬት ነጠቃና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ
አያስቅም! አጭር ወግ
በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው - ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ፣ ጾም በኩዳዴ» ይባል ነበር። ይህ አባባል አሁን መኖ በዘዴ በሚል ተቀይሯል። መቼም ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው። ጋዜጠኛ አቤል አለማየሁ በቅርቡ ባሳተመው "የአዲስ አበባ ጉዶች" የሚል መጽሃፉ ላይ ስለዚህች ታሪካዊ ምግብ ቤትም ትንሽ ብሏል። የምግብ ቤትዋ ባለቤት "ገሊላ ምግብ ቤት" የሚለው ጽሁፍ በከፊል አጥፍተውታል። አሁን ምግብ ቤት የሚለው ተነስቶ "ገሊላ" … [Read more...] about አያስቅም! አጭር ወግ
በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው?
"በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው “Who is in Charge?” የሚለው ጥያቄ ያሳሰባቸው ቧልተኞች የፈጠሩትን ቀልድ ላልሰማችሁ ላሰማችሁ፡፡ (ኮፒራይቱ የሰፊው ህዝብ እንደሆነ ይታወቅልኝ!) አንዱ ኤፍኤም ሬዲዮ ይደውላል - ዘፈን ለመምረጥ። ደዋይ - ዘፈን ለመምረጥ ነበረ፤ የእገሌን … ኤፍ ኤም- ማን እንበል? ከየት ነው? ደዋይ- የገዢው መደብ አባል ነኝ---- ከደቡብ! ኤፍ ኤም- (ደንገጥ ብሎ) ከደቡብ … እሺ ዘፈኑ ይቀጥላል … (የኤፍኤሙ ጋዜጠኛ ከድብልቅልቅ ስሜት ሳይወጣ ሌላ ዘፈን መራጭ ይደውላል) ኤፍ ኤም- ሄሎ … ማን እንበል? ከየት ነው? ደዋይ - ዘፈን ለመምረጥ ነበር ኤፍኤም- ራስህን አስተዋውቀን? ደዋይ - የገዢው መደብ አባል ነኝ - ከትግራይ! ኤፍኤም - እንዴትነው ነገሩ? አሁን ከደቡብ ደውሎ የገዢው መደብ አባል ነኝ … [Read more...] about በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው?
“የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ”
ይኽን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ዐርብ የካቲት 28 ቀን (March 7, 2014) አንድነቶች “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” የሚል ህዝባዊ ንቅናቄ (ህዝባዊ ሰላማዊ ዘመቻ) በ14 ከተሞች {አዲስ አበባ፣ ደሴ፣ አዋሳ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ መቀሌ፣ ደብረታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ ነቀምት፣ ለገጣፎ፣ እና በተጓዳኝ ከተሞች ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ)} እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ነው። መግለጫቸውን እንዳነበብኩ ዘመቻው ለታሪካችን፣ ለተያያዝነው የነፃነት ትግል እና አይናችን ለተከልነበት የዴሞክራሲ ሽግግር የሚሰጣቸው ጠቀሚታዎች አሉን? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስቼ ጥቂት ከራሴ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ ለዘመቻው ድጋፌን በመስጠት እና አንድነቶችን በማበረታት ተሳትፎዬን እንድገልጽ ህሊናዬ የግድ አለኝ። ስለዚህ የዚህ ጽሑፍ ግብ ዘመቻው … [Read more...] about “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ”
Sexual Violence and Rape against Ethiopian Women!
Sexual violence and rape are weapons used indiscriminately by TPLF/EPRDF cadres, soldiers and federal police in Ethiopia. They targeted innocent people living in villages and towns who are caught in the crossfire. Ethiopia is often described as being 'the most dangerous place in the world to be a woman'. The UN estimates that a staggering more than 200,000 women and girls have been victims of rape and/or sexual violence in Ethiopia during the last 15 years. The worst of the violence is … [Read more...] about Sexual Violence and Rape against Ethiopian Women!










