ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡ ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው … [Read more...] about በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት!
የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?
ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በመቶዎች ሚሊዮኖች (አእላፋት) የሚቆጠር የሀገሪቱን ሀብት በማፍሰስ በመጠናቸው በሀገሪቱ ታይተው በማይታወቁ መልኩ በተለያዩ ሥፍራዎች "የሠማዕታት" የመታሰቢያ ሐውልት በማለት አስገንብቷል እያስገነባም ይገኛል፡፡ በምሳሌነት መቀሌ፣ ባሕርዳር፣ ናዝሬት፣ የተገነቡ የመታሰቢያ ሐውልቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ሐውልቶች እንዲዘክሩ እንዲያስቡ የሚፈለገው ሕውሓት ኢሕአዴግ በትግል ላይ በነበረበት ወቅት "የተሠው" ታጋዮቻቸውን እንደሆነ ከየሐውልቶቹ ስር ያለው የማስገንዘብያ ጽሑፍ ይገልጻል፡፡ ለመሆኑ በእርግጥስ እነዚህ ጓዶች ሠማዕታት ናቸውን ከሆኑስ ሠማዕትነታቸው ለማንነው? በበኩሌ እነኝህን ታጋዮች ሠማዕታት ብዬ ልዘክራቸው ሳስባቸው ክብር ልሰጣቸው የምችለው ኢትዮጵያንና ጥቅሞቿን በተመለከተ አሁን በሕይወት ካሉት የሕወሓት ኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና … [Read more...] about የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?
በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል
* "የውኃ ምርት ችግር የለብንም የኤሌክትሪክና የማሰራጨት እንጂ" የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለሁለትና ሦስት ቀናት ይጠፋ የነበረው የውኃ ችግር እስከ 20 ቀናት እየጠፋ መሆኑንና ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ በተለይ ከሳሪስ እስከ ቃሊቲ፣ አየር ጤና፣ ወይራ ሠፈር፣ ለቡ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ፒያሳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ መርካቶ፣ የካ በተለያዩ ወረዳዎች አራት ኪሎ (አልፎ አልፎ) በአጠቃላይ በከተማው ከአምስት እስከ 20 ቀናት ውኃ ጠፍቶ እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ የተባሉ የሳሪስ አቦ ማዞሪያ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ የውኃ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ ያስገርማቸዋል፡፡ ቀን ቀን ይጠፋና እኩለ ሌሊት ይመጣላቸው በነበረው ውኃ ሲማረሩ፣ ይባስ ብሎ የመጥፋቱ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል
መርገምተ ወያኔ
“በረከተ መርገም” የሚያስፈልግ ቃሉ፣ ዛሬ ነው ተራገም ባለቅኔው ኃይሉ። ቅኔህን አፍሰው እንደድሮ እንደጥንት፣ ላሁን ዘመን ገዢ ያስፈልጋል መርገምት። አንተ በርግማንህ የጠበጠብካቸው እነዛ ሊቃውንት በፍልስፍናቸው ተወቃሽ በመሆን ቢያተርፉም ክፉ ስም ለውጥ አስገኝተዋል ላለንባት ዓለም ነገር ግን ያሁኑ ለስልጣን ለሀብቱ፣ ለስጋ ቁመናው ለሰፊው ቀፈቱ፣ አስሮ ሲያንገላታ ቆይቷል ሲገድል፣ አፍስበት በሱም ከርግማንህ ጠበል፣ ድሮ በሊቆቹ እርግማን ከጨረስክ፣ ምን ይሰራል ብለህ ወይም መርገም ከተውክ፣ እንዳሻህ በልና ፍቀድልኝ፣ ለኔ የርግማን በረከት አለኝ በወያኔ ካስፈለገም አምጣ ድርሻህን መዋጮ፣ የእኔን ግን ልጀምር ከወያኔው ቁንጮ ከኢትዮጵያ ምድር ከአብራኳ ወጥተህ፣ አንባሻዋን ገምጠህ ወተቷን ጠጥተህ፣ ፊደል ቆጥረህባት በሜዳዋ ሮጠህ፣ በፍቅር በደስታ … [Read more...] about መርገምተ ወያኔ
የኢህአዴግ ማመልክቻ ድጋሚ ውድቅ መደረግ አለበት!
የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ በድጋሚ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ውድቅ መደረግ እንዳለበት ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት (Human Rights Watch) ድርጅት አስታወቀ፡፡ ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ አስገብቶ ውድቅ ተደርጎበት የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ የታወጁት አፋኝ ሕጎች እስካልተወገዱ ድረስ ድጋሚ ማመልከቻው ውድቅ ሊደረግ እንደሚገባው ጨምሮ ተነግሯል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከሳምንታት በፊት “ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ” በሚል ርዕስ ባወጣው ዜና ጉዳዩን በስፋት ዘርዝሮ ነበር፡፡ “EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ … [Read more...] about የኢህአዴግ ማመልክቻ ድጋሚ ውድቅ መደረግ አለበት!
የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሕጋችን ቢከለስስ?
የዛሬው ጽሑፌ መነሻውና መድረሻው በዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ስለነበረው የኡጋንዳ የፀረ ግብረ ሰዶም ሕግና አገራችን በንፅፅር የምትወስደውን ልምድ መቃኘት ነው፡፡ ኡጋንዳ ይህንን ሕግ በማውጣቷ ዓለም ተደንቋል፡፡ አፍሪካን ግን የሚደንቅ አይደለም፡፡ አገራችንንማ ሕጓን እንድታጠነክር ካልሆነ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚታገስ ባህልም ሕግም ኖሯት አያውቅም፡፡ ዜናው እጅጉን የሳበው ምዕራባውያንን ነው፡፡ ኡጋንዳ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች በአንድ ወቅት ቅኝ ገዥ ስለነበራት የድሮው አስተሳሰብ የተፀናወታቸው ወገኖች ተቃውሞውን አድምቀውት ሰንብተዋል፡፡ አገራችን በማንም ቅኝ ተገዝታ ባለማወቋ፣ ባህሏ የራሷ በመሆኑ ተቃዋሚዎች የመተቸቱን ሞራል የኡጋንዳን ያህል አያገኙትም፡፡ ከዓለም ጋር አንድ በሚያደርገን በተባበሩት መንግሥታትም ቢሆን አንድ የሆነ አቋም ባለመኖሩ፤ ቢኖርም በተዓቅቦ … [Read more...] about የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሕጋችን ቢከለስስ?
Ethiopia Anew: A Call to Amhara Ethnic People REALLY?
In present day Ethiopia there are two political schools of thought. These schools lead to the political struggle and the actions taking place on our land today. They are diametrically opposed to each other. The first one states that all problems that existed and still exists in Ethiopia emanate from the rulers oppressing Ethiopians at large. This leads to the struggle of Ethiopians to have a say in the political sphere of the country. The oppression of the rulers of the country has many forms … [Read more...] about Ethiopia Anew: A Call to Amhara Ethnic People REALLY?
ልማታዊ መንግሥትና አዲሱ የአባ ወራ አስተዳደር ለአፍሪቃ
ኢህአዲግ ለሚቀጥሉት አርባ ዓመታት ለመግዛት በማለም፣ ላለፉት ዓመታት የሚከተለውን የአስተዳደርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ „በባለ ራዕዩ“ መሪያቸው የ ተነደፈውን ባደባባይ ለውይይት ለማቅረብ እየሸነጠው ነው። በመሰረቱ ወጣም ወረደ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ይህ ፖሊሲ በተግባር ይውል እንደነበረ ባለሙያዎች ሆኑ የውጭ ሀይሎች ደጋፊዎቻቸው የሚያውቁትና የአደባባይ ምስጢርም ነው። አሁን ግን ይበልጡን ጡሩንባ ተለቆለት፣ ባደባባይ እንዲወጣና አዲስ የሚነዳ የርዕዮተ ዓለም ፈረስ ሆኖ ብቅ ያለው፣ የቀድሞው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቲዎሪ ነዳጅ ስለ አለቀና የሚያሳምን ስም ስላላተረፈ፣ ለአገዛዝ ማሰንበቻ፣ በልማት ስም፣ ልማታዊ መንግሥት /developmental state/ የሚባለው የተወሰነና ከዛኛው የበለጠ ሌጂትሜሲ/ ተቀባይነት ያስገኛል በሚል ምኞት ነው። በተለይም በልማት ሰበብ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች … [Read more...] about ልማታዊ መንግሥትና አዲሱ የአባ ወራ አስተዳደር ለአፍሪቃ
“ኢህአዴጋዊ ምርጫ” በሰሜን ኮሪያ
ድምጽ የመስጫው ጊዜ ተጠናቅቆ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ መቁጠር በጀመሩ ጊዜ ኪም ጆንግ ኧን የማሸነፋቸው ጉዳይ አሳስቧቸው በስጋት ውስጥ ነበሩ፡፡ ቆጠራው ተጠናቀቀ፤ ውጤቱ ይፋ ሆነ፤ አሸናፊው ታወጀ፤ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን ከያዙ የመጀመሪያውን ምርጫ በ100% አሸነፉ፤ ከጭንቀታቸው አረፉ፤ ሕዝቡም በደስታ ፈነጠዘ፣ የክት ልብሱን ለበሰ፤ በአደባባይ ወጥቶም ዳንኪራ ረገጠ፡፡ እሁድ በተደረገው ምርጫ የተሰጠውን እያንዳንዱን ድምጽ ኪም ጆንግ ያለተቀናቃኝ የራሳቸው አድርገዋል፡፡ በየአምስት ዓመቱ በሚካሄደው ምርጫ የተሳተፈው ሕዝብ የምክርቤት አባላትንም መርጦዋል፡፡ በደንቡ መሠረት ምርጫው የሚካሄደው ለምክርቤት ምርጫ ሲሆን የተመራጮች ዝርዝር ውጤት ከመታወቁ በፊት የሰሜን ኮሪያ ዜና አገልግሎት ኪም ጆንግ ኧን ያለተቀናቃኝ በተወዳደሩበት ወረዳ አንድም ተቃዋሚ ድምጽ ሳይሰጥባቸው የሁሉንም መራጭ … [Read more...] about “ኢህአዴጋዊ ምርጫ” በሰሜን ኮሪያ
“ልጄ አካለ ስንኩል ነው እንጂ አእምሮ ስንኩል አይደለም”
አካለ ስንኩል የሆነውን ልጁን በትከሻው በመሸከም በየቀኑ 14.4ኪሜ (9ማይል) በእግሩ በመጓዝ ለሚያመላልሰው አባት መንግሥት በአቅራቢያው ቤት እንደሚሰጠው ተነገረ፡፡ በደቡብ ምዕራብ የቻይና ግዛት የሚኖረው የአርባ አመቱ አባት አካለ ስንኩል የሆነውን የ12ዓመት ልጁን ት/ቤት ለማስገባት ካለው የጸና እምነት የተነሳ ልጁ ራሱን ችሎ መራመድ የማችል በመሆኑ ለመጓጓዣ ባዘጋጀው ለየት ያለ ቅርጫት በመሸከም ከመስከረም ወር ጀምሮ እያመላለሰው መሆኑን የቻይናን ዜና ምንጮችን ጠቅሶ ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡ ልጁ የሦስት ዓመት ህጻን በነበረበት ወቅት ከወላጅ እናቱ ጋር የተለያየው አባት ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ልጁን ብቻውን ያሳደገው ሲሆን እናቱ ብትለይም ልጁን ብቻውን ለማሳደግ በመወሰን መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል የዚያኑ ጊዜ መወሰኑን ተናግሯል፡፡ ልጁ እያደገ ሲመጣ ት/ቤት … [Read more...] about “ልጄ አካለ ስንኩል ነው እንጂ አእምሮ ስንኩል አይደለም”









