"የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።..." የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ "የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።" የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ። "የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።" ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል … [Read more...] about ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም
ነጋ ደግሞ !
ላስታምም የሆዴን ጩርር ..... ርታ፤ ላዳምጥ የወስፋቶቼን ጩኸት ጫጫታ፤ የማያቋርጥ የረሃብ ሳል ልስል፤ እሹሩሩ እያልኩ ረሃብን ላባብል፤ ልደማ ልቆስሌ ልገዘገዝ በችጋር፤ በቁም ሞቼ - ላልኖር ስኖር፤ በብርሃኗ ላላጌጥ - ጮራዋ ለኔ ላይፈነጥቅ፤ ነጋ ደሞ ! ...... ሌላ ቀን - ፀሐይ ወ'ታ ልትጠልቅ :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ነጋ ደግሞ !
አይ አዜብ!
አዜብ ሲባል ማን በአዕምሮህ ሊመጣ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በውስጥህ ያሰብከው ‹የባለራዕዩን መሪ› ባለቤት አዜብ መስፍንን ከሆነ ለጊዜው ግምትህ አልሰራም፡፡ አሁን አዜብ የምልህ ሌላ ሴት ናቸው፡፡ አዜብ አስናቀን ነው፡፡ (አስናቀ ስልህም እንዳትደነግጥ...የሰው ለሰው ድራማው አስናቀ አይደለም፡፡) ለማነኛውም አዜብ አስናቀ የግልገል ጊቤ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ሴት ነው እየጠቀስኩልህ ያለሁት፡፡ እና አዜብን እንዴት አነሳኋቸው ካልክ ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ ሴትዮዋ ከግቤ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ‹ከፍ› ወዳለ ሹመት መጥተዋል፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚነት አድገዋል፡ ፡ ሹመታቸው በቀድሞው ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረት ደበበ ቦታ መሆኑ ነው፡፡ እኒህ ሴት ታዲያ ‹አይ› የሚያስብል ነገር … [Read more...] about አይ አዜብ!
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
የትምህርት ሚኒስትር በ2006 ዓ.ም በአገሪቱ በተፈጠረው የመምህራን እጥረት ምክንያት በተለ ያዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ኢትዮጵያውያንን ለአንድ አመት ሙሉ ወጫቸውን ችሎ የማስተማር ስነ ዘዴ (ፔዳጎጅ) በማስተማር ወደ መምህርነት እንዲገቡ ማስታ ወቂያ ያወጣል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረ ትም ለማጣሪያነት የቀረበውን ፈተና በመፈተን መልምሎ ለስልጠና እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረት በ10 ዩኒቨርሲቲዎች (መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ሀሮማያ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ) እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡ ይህ ስልጠና እየተካሄደ ባለበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት ሙሉ ወጫቸ ውን መንግስት እንደሚችል ተነግሯቸው ነበር የመጡት፡፡ በዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ የተደለ ደሉት 330 ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ተማሪዎቹ ቃል በተገባላቸው መሰረት … [Read more...] about የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ‘ሮሮና ስጋት
የከሸፉት የህወሓት የተስፋ ቃላት
የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ በእግሩ የተተካው ህወሓት ይኸው ሥልጣን ላይ ከወጣ 23 ዓመት ሊሆነው ነው። ህወሓት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዲሞክራሲን አሰፍናለው፣ ሰብአዊ መብት አክብሬ አስከብራለው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ይከበራል፣ ልማት ይመጣል የኢትዮዽያ ሕዝብ ስደት ያበቃል፣ በቀንም ሦስት ጊዜ ይበላል የሚሉት ዋንኞቹ ነበሩ። እስኪ አንድ በአንድ እንያቸው። 1. ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተመለከተ ህወሓት ከበረሃ ወጥቶ ከተማ እንደገባ ዋንኛ ጩኸቱ ይሄ ነበር። በመጀመሪያ አካባቢ ነፃ ጋዜጦችን ማሳተም፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በፖለቲካ ፓርቲ መደራጀት የመሳሰሉት ነገሮች ጥሩ ጅማሮ ያሳዩ ቢሞስሉም ብዙም ሳይቆይ ግን የህወሓት ትክክለኛ ባሕሪ መገለጥ ጀመረ። ጋዜጠኞችን ማሰርና ማንገላታት፣ ነጻ የሙያ ማኅበራትን ማፍረስ፣ ተቃዋሚዎችን ማሰር ብሎም በስውር ማስገደል፣ … [Read more...] about የከሸፉት የህወሓት የተስፋ ቃላት
ፋሲካን በመንገድ ዳር
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ፋሲካን በመንገድ ዳር
ሕወኃት/ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ጨካኝ አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ በደል ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ በጣም አስከፊና ሁዋላ ቀር የህዝብን ጥቅም የማያስጠብቅ ጭከናና ኢሰብኣዊ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም አገርን ማፈራረስና የኢትዮጵያዊነትን ታሪክና ባህልን የማጥፋት ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብን የሀገር ሀብት መዝረፍ በስፋት እየፈጸመ ይገኛል::(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሕወኃት/ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?
ይህንን ምን እንበለው? ኢህአዴግ እስካሁን ያለው ነገር የለም
"መኖሬን ጠላሁት። ራሴን እንዳልገድል ወንጀል ነው። ሰው እንዳልገድል ወንጀል ነው" በሚል ግራ መጋባት አንድ አዛውንት ይናገራሉ። ተበዳዮች ከእርሻ ስራ በኋላ የሚይዙትን በትር ፖሊስ ሰበሰበ። ከዚያም እገበያ ቦታ ላይ ገጀራና ጦር የያዙ ጎረምሶች እየጮሁ ጥቃት መፈጸም ጀመሩ። 16 ሰዎች፣ 26 ናቸው የሚሉ አሉ ጉዳት ደረሰባቸው። አንድ ሰው ተገደሉ። ይህ ዜና የተወሰደው ተበዳዮች ራሳቸው ባንደበታቸው ሲናገሩ ከሚታዩበት ቪዲዮ ነው። የተገደሉት አቶ ጌጡ ክብረት ይባላሉ። የሰባት ልጆች አባት ናቸው። የተገደሉት በገጀራ ነው። ከተገደሉ በሁዋላ አይናቸውን አውጥተዋቸዋል። አንደኛው ተናጋሪ አዛውንት እንደተናገሩት ደግሞ "ብልታቸውን ሸንሽነዋቸዋል"። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለህክምና ሲሄዱ "ሂድና አገርህ ታከም። ይህ የእኛ ሃኪም ቤት ነው" እንደተባሉ ምስክሮቹ ይናገራሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው … [Read more...] about ይህንን ምን እንበለው? ኢህአዴግ እስካሁን ያለው ነገር የለም
በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ
የኢህአዴግን የስለላ መዋቅርና አካሄድ አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ተበራክተዋል። ኢህአዴግ ራሱን እንደሚስለው ዓይነት ድርጅት ሳይሆን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉድለት ያለበት፣ በሚዲያ ነጻነት ኋላ ቀር፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በማሳደድ ግንባር ቀደም፣ አፋኝ ህግ በማውጣትና በማሸማቀቅ ወደር የማይገኝለት፣ ለሚያወጣው ህግና ደንብ የማይገዛ፣ የውስጥ ችግሩ ታይቶ በማይታወቅ መጠን ዜጎችን ለስደት እየዳረገ እንደሆነ እየተመሰከረበት ነው። ኢህአዴግን ሸሽተው አገር ለቀው የተሰደዱ በስደት ምድርም ኢህአዴግ እየተፈታተናቸው እንደሆነ መግለጽ ከሰነበቱ ቆይቷል። በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በጀርመን፣ በስዊድንና በእንግሊዝ አገር ስደተኞችን በመሰለል ተግባር ላይ የተሰማሩ “የስደተኛ ሰላዮች” በስፋት ስለመኖራቸው መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። የተለያዩ ድርጅቶች በዚህ … [Read more...] about በስደትም መሰለል – በኖርዌይ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ
ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስአበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ
አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ "የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!"› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስአበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ








