በመጪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ እየተባሉ የሚጠበቁት ሒላሪ ክሊንተን ንግግር በሚያደርጉበት ጊዜ ጫማ ተወረወረባቸው፡፡ ጉዳት ባይደርስባቸውም ዜናው ግን የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ ስቧል፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሒላሪ ክሊንተን በላስ ቬጋስ በተጠራ የመልሶ መጠቀም ኢንዱስትሪዎች (Scrap Recycling Industries) ስብሰባ ላይ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ሁኔታ ከአዳራሹ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡ ጫማው ሳይመታቸው ቢቀርም ወርዋሪዋ ግለሰብ አስተካክላ ብትወረውር ግን ክፉኛ ጉዳት ልታደርስባቸው ትችል እንደነበር የቪዲዮው ምስል ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ አዳራሹ ጨለምለም ያለ በመሆኑ ክሊንተን ጫማው ከተወረወረ በኋላ ነው ያስተዋሉትና ደበቅ ለማለት … [Read more...] about ሒላሪ ክሊንተን ጫማ ተወረወረባቸው
ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው
ኢህአዴግ በሙስና ስም የ"ማጥራት ዘመቻ" ማካሄዱን ተከትሎ የተከሰተው አለመተማመንና እርስ በርስ በጥርጥር የመተያየት ችግር ካድሬውን ማስጨነቁ ተጠቆመ። ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች "ለምን" በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመፍራት የግድ ፓርቲውን መስለው እንደሚኖሩ ተገለጸ። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ቀደም ሲል ኢህአዴግን ተሰናብተው የወጡና በተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ ካሉ ያገኘውን መረጃ በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የቀድሞ የትግል ጓደኞቻቸው "በደህና ጊዜ ተገላገልክ" በሚል በፓርቲው ውስጥ ችግር ስለመኖሩ እየነገሯቸው ነው። አብዛኞቹ ኢህአዴግን ተለይተው በሰላም ስለመኖር እንደሚያስቡ ነው የተሰማው። የቤተሰቦቻቸው የወደፊት እድልና የነሱ በፍርሃትና በጭንቀት መኖር አሳዛኝ እንደሆነ የነገሩት የቀድሞ የኢህአዴግ ሰዎች "አሁን ያለው … [Read more...] about ከአገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣናት በጭንቀት ውስጥ ናቸው
“አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ።”
ወንድሜ ህይ! በመጀመሪያ አነሳስህ ታሪክ መሰረተ አድርገህ ነው የተንቀሰቀስከው። አሁን ግን ሰበካውን፣ ፖላቲካውን፣ ታሪኩን (ተረት-ተረት)፣ የትምክህትና የንቀት ቀለቶችህ ተበውዘው ሊክ እንደካርታ ጨዋታ አኬር (ጆከር) ፍለጋ የሚባዝን ሰው መሰልከኝ። አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንድ ያኔው 19ኛ ክፍለ ዘመን ብዙ የተናገራ እንድሚያሸንፍ አይደለም። አማሪኛችሁን ስለ ከሸንክና በጥሩ ቃላቶች ነገሮችን ስለ ሸፋፈንክ (ቅኔም) እንበለው፣ ሃቁ ተደብቆ አይቀርም። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) አቶ ቃሉ ኩሣ ይህንን ምላሽ የጻፉት አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን “መልሳቹህ” በማለት ለሰጡት ምላሽ ነው። … [Read more...] about “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ።”
“ኅብረ ሐመልሚል”
“የአረንጓዴ፤የቢጫ፤ የቀይ፤ የነጭና የጥቁር ነጠብጣብ፤ የብዙ አይነት ቀለማት ህብር፤ በማይዝግ በብር ሰሌዳ ላይ በባለሙያ የተሰሩ የወርቅ፡ ያልማዝና የዕንቁ ፈርጦች እና ጉብጉባቶች” የአቶ መላኩ አሰፋን የህይወት ታሪክ ለመግለጽ “ኅብረ ሐመልሚል ቀይህ ወጸዓድዒድ አርአያ ኮሰኮስ ዘብሩር”ብለን ውበት የምንገልጽበትን የግዕዝ ቋንቋ ሐረግ መነሻ ማድረጉ ተስማሚ ይመስለኛል። ይሁን እንጅ ያቶ መላኩን ሁለንተና ለመግለጽ ወደዚህ ውበት ገላጭ ሀረግ ከመግባቴ በፊት፤ በሩቅና በቅርብ ላሉት ዘመዶቹና ወዳጆቹ ህልፈቱን ለማርዳት ስለሚረዳ፤ ተወልዶ እትብቱ ከተቀበረባት መንደር ጀምሬ የረገጣቸውንና የቆየባቸውን ቦታወች ማስቀደሙ ተገቢ እንደሆነ እገምታለሁ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ኅብረ ሐመልሚል”
ዲና ሙፍቲ ይመችዎት – “በነጻው ፕሬስ” ስም
ለምሳሌ አንድ አናጢና ግንበኛ የነበረ ሰው ጊዜ ረድቶት ወይም ተምሮ ወይም እድገት አግኝቶ ወይም …. በቃ በሆነ ነገር የጦር ጄኔራል ቢሆንና ተመልሶ ግንበኛ ቢሆን ምን ተብሎ ሊሰየም ነው? ግራ ያጋባል። ግን ደግሞ ላያጋባም ይችላል። የዛሬዎቹ ጄኔራሎች ኢንቨስተር ስለሆኑ ነዋ!! ለምሳሌ አንድ አምባሳደር ተብሎ የ"ተመደበ" ሰው፣ በግምገማ በሉት በገገማ "በቃህ" ቢባልና ቀድሞ ወደነበረው ሙያ ወደ ነርስነቱ ቢመለስ ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? “አምባሳደር፣ ነርስ፣ እገሌ …”? ቀጭኑ ዘ-ቄራ ነኝ። በውል በማይገባችሁ ምክንያት ተሰውሬ ነበር። ዛሬ እግር ጣለኝና "ላሸብር" መጣሁ። ሰላምታዬ መሆኑ ነው። መለስ ድንጋዩ ይቅለላቸው፣ አርማታው ስፖንጅ ይሁንላቸውና ብዙ አይነት የሰላምታ ቋንቋና ስታይል "አውርሰውን" አልፈዋል። ታላቁና አርቆ አስተዋዩ መሪያችን!! ህወሃቶች በዚህም ይቀኑ ይሆናል … [Read more...] about ዲና ሙፍቲ ይመችዎት – “በነጻው ፕሬስ” ስም
ትግል እምቢታ እንጅ አቤቱታ አይደለም
ምንም እንኳን ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ ተቃዋሚ ሃይሎች በመባል በአንድ ጎራ ተጠቃለው ይታወቁ እንጅ በውስጣቸው የተሰሉፉት ሃይሎች አንድ አይነት የትግል ስልትም ሆነ ብሄራዊ ራዕይ ያላቸው እንድልሆኑ ግልፅ ነው። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በጥገና ለውጥ ስርዓቱ እንዲሻሻል ማስገደድ ይቻላል የሚሉ፣ ሌሎች ደግሞ ስርዓቱ መቀየር አለበት የሚሉ፣ ነገር ግን የሃገሪቱን ሉአላዊነት ግምት ውስጥ የማያስገቡና የባዕዳንን የቆየ ተፅዕኖ በአዲስ ቀለም ለማስቀጠል የሚፈልጉና ዴሞክራሲን ከይስሙላ ምርጫ ጋር ቀላቅለው የሚያዩ፤ ጥቂቶች ደግሞ መገንጠልን በግልፅ እሚያራምዱ ወይም ይህንኑ ዓላማ በአዲስ ቋንቋ አለዝበው ሁኔታው እስኪመቻች የሚጠብቁና ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ነን ቢሉም እነዚህኑ ክፍሎች የሚያግዙና የሚያበረታቱትንም ያጠቃልላል። ከነዚህ ሁሉ ተለይተው የቆሙት ሃይሎች ደግሞ፣ ያለው … [Read more...] about ትግል እምቢታ እንጅ አቤቱታ አይደለም
የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት
ኢትዮጵያ የ5 እና የ 6ሺ ዘመን ታሪክ ያለት ሀገር ነች። የመንግስት ስርዐትም ፈጥረው ከኖሩ ሀገሮች መካከል በቅድሚያ የምትጠራ ሀገር ናት። ሆኖም ግን አንዳንዶቹ የአሁኑ ድህነታችን፣ በቴክኒኦሎጂ ወደሁዋላ መቅረታችን፣ የቀደመ የኢትዮጵያንና የህዝቡዋን ትልቅነት ለማየት ይቸግራቸዋል። ”ቤት ሲያረጅ ትሁዋን ይፈጥራል” እንደሚባለው ካልሆነ በቀር ከታሪክ እንደምንረዳው፣ አንድ ሀገር ይወድቃል ይነሳል፡ ይደኸያል ይበለጽጋል፡ ይዋረዳል ይከበራል። ሆኖም በህዝቡ የመንፈስ ጽናትና ቆራጥነት፣ የገጠመውን ድህነት፣ ውድቀትና ፈተና ሁሉ ታግሎ አሸንፎ ወደ ነበረበት የክብር ቦታው ይመለሳል። ዛሬ እኛ ደህይተናል፣ ወድቀናል፣ ተዋርደን ህዝባችን በየሀገሩ ተበትኖ የስቃይ ህይወት መኖሩ አልበቃው ብሎ በሀገሩም በሰላም እንዳይኖር በኢትዮጵያ የቅርብና የሩቅ ጠላቶች በሚደጎሙና አለኝታን ባገኙ ከሀዲዎች … [Read more...] about የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት
ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው
የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል። ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል። ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር … [Read more...] about ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው
በፓኪስታን የ9 ወር ህጻን በመግደል ሙከራ ተከሰሰ
ባለፈው ሳምንት በፓኪስታን ላሆር ከሌሎች ቤተሰቦቹ ጋር የ9 ወር ህጻን በመግደል ሙከራ ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ህጻኑ ከነጡጦው በፍርድ ቤት መዝገብ ላይ በአያቱ እርዳታ ጣቱን በቀለም አጥቅሶ ከፈረመ በኋላ ዳኛው ጊዜያዊ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ በማድረግ ለሚያዚያ 4 ቀጠሮ ሰጥተውታል፡፡ ህጻኑና ወደ25 የሚጠጉት ቤተሰቦቹ የተከሰሱት በፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወርና የፖሊስ ኃይሎችን ለመግደል ሞክረዋል በሚል ነው፡፡ በላሆር የሚገኙ ነዋሪዎች የጋዝና የኤሌክትሪክ ክፍያ ባለመፈጸማቸው ውዝፍ ዕዳ ስለተጠራቀመባቸው የጋዝና የኤሌክትሪክ መስመሮቹን ለመቁረጥ የፖሊስ ኃይል ወደሥፍራው የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ ተንቀሳቅሶ ነበር፡፡ በሁኔታው የተናደዱ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊስ ቡድኑ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጥቃት ከማድረስ አልፎ የተወሰኑት ላይ ጉዳት አድርሰው ነበር፡፡ ክስተቱን … [Read more...] about በፓኪስታን የ9 ወር ህጻን በመግደል ሙከራ ተከሰሰ
በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት Vs ህገ-መንግስታዊ ቀናዒነት
መግቢያ በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ constitutional patriotism ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የConventional Cultural Unity ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል ኣሳብ ለማፍራት ነው። በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ ፍልስፍና ወይም ቲየሪ በኣንድ ሃገር ፖለቲካ ውስጥ መሰረታዊ የመጫወቻ ወለል ኣድርገን ከማንጠፋችን በፊት ቲየሪው ወይም ኣሳቡ በጣም መጠናትና ግልጽ መሆን ኣለበት። ግልጽነት ሳይኖረውና ሳንረዳው በስሜት ከተከተልነው ሁዋላ ላይ ጉምን እንደ መጨበጥ ይሆንና እናርፋለን። ለዚህ ምሳሌ ኣምጣ ብትሉኝ … [Read more...] about በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት Vs ህገ-መንግስታዊ ቀናዒነት









