የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው "ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም" ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው "ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ" በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች "አገር በማተራመስ" ወንጀል ክስ መሰረተባቸው። የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። … [Read more...] about ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?
“I can’t eat GDP!”– Why Numbers don’t Matter!
On 25th February 2014 a one-day seminar was conducted by Heinrich Böll Stiftung, a foundation which is founded after the name of one of the legendary figures of peace movements during the 1970s and 80s, famous for his many critical works as a writer. The foundation intimately linked to the Green party, actively participating in ecological, democratic and peaceful movements is contributor to civil society organizations in Germany and civil society organizations worldwide. In this spirit, it … [Read more...] about “I can’t eat GDP!”– Why Numbers don’t Matter!
ዜጎች በጎጃም መሬቸውን እየተነጠቁ፤ በወለጋ ደግሞ እየተፈናቀሉ ነው!
አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለካሳ እየተነጠቁ ነው መራዊ፡- በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ያለ ፈቃዳችን መሬታቸውን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ አርሶ አደሮች እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በመራዊ አካባቢ ሜጫ ወረዳ እናሸንፋለን ቀበሌ መንግስት የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ እናካሂዳለን በሚል ከ400 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ከመሬታቸው እንዲለቁ የተደረገውን እርምጃ አርሶ አደሮቹ በመቃወማቸው እስርና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ከአሁን ቀደም ተመሳሳይ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን የአርሶ አደሮቹ መሬት በአበባ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ይህም በአሁኑ ወቅት መንግስት ውሃ ለመቆፈር በሚል አርሶ አደሮቹ ከመሬታቸው እንዲለቁ የሚወስደው እርምጃ በተመሳሳይ ለአበባ … [Read more...] about ዜጎች በጎጃም መሬቸውን እየተነጠቁ፤ በወለጋ ደግሞ እየተፈናቀሉ ነው!
የወያኔ የሚፈራው ምርጫ ወይስ ሕዝባዊ እምቢተኝነት (አመጽ)
በዚች አለም በሕዝቦቻቸው ላይ የሚፈነጩ አምባገነኖችን ለማስወገድ የሚደረጉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወያኔ ዘረኛችን ለምን ሲያስደነብራቸውና በፍርሃት ሲያሸማቅቃቸው እንደሚኖር የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ የህውሃት ዘረኛ ቡድን በሕዝብና በሃገር ላይ የሚያደርሰው መጠነ ሰፊ ጥቃት ወይም ውድመት በተለያየ መንገድ ሕዝቡ ቅሬታውን ቢያሰማም እራሱ ለፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ የሕዝቡን ብሶት ለማዳፈን ሀላፊነት የጎደለው ተግባራትን እየፈፀመ ሃገርን የመበተን ስራውን ቀጥሎበታል፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የወያኔ የሚፈራው ምርጫ ወይስ ሕዝባዊ እምቢተኝነት (አመጽ)
የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል
ሃያ አምስት በመቶ እንደተጠናቀቀ የሚነገርለት የ“ህዳሴው” ግድብ በኢትዮያና በግብጽ መካከል ከፈጠረው የፖለቲካ ቁርቋሶ በተጨማሪ ወደ ሃይማኖት መንደርም እየዘለቀ ነው፡፡ ዛሬ (አርብ) ግብጽን ለመጎብኘት ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አቡነ ማቲያስ ከግብጽ በኩል እንዳይመጡ በተላለፈላቸው መልዕክት መሠረት ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡ በግብጽና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የተለያዩ የዜና ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ መልዕክቱ ያስተላለፉት የግብጹ ፓትሪያርክ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ ናቸው፡፡ ፓትሪያርኩ ለአቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት መልዕክት በበርካታ ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የአባይ ግድብ የፈጠረው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ይህንን ጉብኝት ማካሄድ የግብጽን ቤ/ክ “የሚያሳፍር” ይሆናል በሚል ነው ምክራቸውን ለአቡነ ማቲያስ የለገሱት፡፡ ስማቸውን ሳይጠቅሱ መረጃውን ለግብጽ የሚዲያ … [Read more...] about የ“ህዳሴው” ግድብ ተጽዕኖ ሌላ አቅጣጫ መያዙ አሳሳቢ ሆኗል
“የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ላይ ያለው እምነት ተሟጥጧል”
የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ወደ አፍሪካ የሰብዓዊ መብቶችና ህዝቦች ኮሚሽን ሂደው በመንግስት ላይ ክስ መመስረታቸው ይታወቃል። ይህንን በማስመልከትም በድር ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ቢቢኤን) የኮሚቴውን የክስ ሂደት በቅርበት ከሚከታተለው ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ ጋር በዚሁ ጉዳይ ቆይታ አድርጓል። ዶ/ር አወል የአለም ዓቀፍ ህግ ምሁር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በLondon School of Economics የሰብዓዊ መብት Fellow ነው። ቢቢኤን፡- የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጉዳያቸውን ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ለመውሰድና ለመክሰስ ያሰቡት ለምንድን ነው? ጉዳያቸውን በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች መጨረስ አይችሉም ነበር? ዶክተር አወል፡- አመሰግናለሁ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት በኢትዮጵያ … [Read more...] about “የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ላይ ያለው እምነት ተሟጥጧል”
ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
አንድ በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ። አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን … [Read more...] about ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?
ምን ይባላል!
ከዚህ በፊት ስናደርግ የነበረውን የግጥም ጫወታ በበርካታ ምክንያቶችና ለመቀጠል ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለn:: በተቻለን ሁሉ እንደገና ለመጀር እየሞከርን በመሆኑ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በአጫጭር ግጥሞች ታላላቅ መልክቶችን የምታስተላልፈውን የብሌን ከበደን ግጥም ለዛሬው አቅርበናል - ግጥሙን ያገኘነው ከብሌን ፌስቡክ ገጽ ላይ ነው:: እስቲ እናንተም የፌስቡክ ውሎዋችሁን ስንኝ ቁዋጥሩበት:: ምን ይባላል! ውሎና አዳሬን እዚህ ተወዝቼ ሰፈሬን መንደሬን ቀዬዬን ዘንግቼ ከጠለቀው ባህር `ከፌስ ቡክ `ገብቼ ጥቂት ሞጫጭሬ ብዙ እውቀት አጊኝቼ ሀሳብን ደግፌ ካልመሰለኝ ትቼ አሁንም እዛው ነኝ መስኮቴን ከፍቼ ። አንድ ጊዜ በላኘ ቶኘ አንድ ጊዜ በስልኬ አይኖቼን ተክዬ እዛው ተላክኬ ቀንና ሌት ሳልመርጥ ስገባ ስወጣ ያ ደሞ ምን አለ ይሄ ምን አመጣ ያቺ ምን … [Read more...] about ምን ይባላል!
ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና … [Read more...] about ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!
አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ
የሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት አንፃር ተመዝኖ አስፈላጊ የሚባሉ የፖሊሲና የመንግስታዊ አወቃቀር ለውጦችን መተግበር ሲሆን ይህም በሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ጥሩ ሊባል የሚችል ለውጥ ሲያስገኝ ተስተውሏል። ነገር ግን ወደ ሃገራችን መንግስት ስንመጣ ከበድ ያሉ የማስተካከያ መፍትሄዎችን ቀርቶ እጅግ አነስተኛ የሚባሉ የማህበረሰብ የመብት ጥያቄዎችን እንኳን በሃይል በመጨፍለቅ … [Read more...] about አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ









