መጋቢት 20/ 2006 ዓ.ም ሶዶ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ለእስር የተዳረጉት የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ድብደባና ወከባ እንደተፈጸመባቸው የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ ገለጹ፡፡ በወቅቱ ታስረው ከነበሩት መካከል ወጨፎ ሳዳሞ የወላይታ ዞን ምክትል ሰብሳቢ፣ ታደመ ፍቃዱ የወላይታ ዞን አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ጻድቁ ወ/ስላሴ የወላይታ ዞን የፋይናንስ ኃላፊ፣ አቶ ቴዎድሮስ ጌታ የዞኑ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ እና አቶ ቦጋለ የፓርቲው አባል ይገኙበታል፡፡ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ የታሰሩት የዞኑ አመራሮች ምግብ፣ ውሃና ልብስ እንዳይገባላቸው ተከልክሎ እንደነበርም የአካባቢው አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ "ከዚህ በፊት ሁለት የፓርቲው አመራሮች በአራዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ለፓርቲው ስራ የሚገለገሉባቸውን ሰነዶች … [Read more...] about በወላይታ ዞን አፈናና ወከባው ቀጥሏል
“ዘላለማዊነት ለገንዳዎች!! ዘላለማዊ ክብር ለገንዳዎች”
የገንዳዎች የደራጃ መዳቢ ድርጅት ሊቋቋም ይገባል። ገንዳዎች የኑሮ መሰረት የሆኑላቸው እየበረከቱ ስለሆነ በደረጃ መከፋፈል አለባቸው። የአጠቃቀማቸውም መመሪያም በግልጽ ሊቀመጥ ይገባል። የደረጃዎች መዳቢ ድርጅት ቢያንስ በገንዳዎች ውስጥ ስለሚጣሉ ቆሻሻዎች መመሪያ በማውጣት የሚበሉ ነገሮች ከሌሎች አይነት ቆሻሻዎች ተለይተው እንዲጣሉ ማዘዝ አለበት። ከሸራተንና ከቤተ መንግስት የሚወጡ የምግብ ትራፊዎች ተጠቃሚ ጋር ሳይደርሱ ፓስተር እንዲመረመሩ የሚያዝ መመሪያ ቢወጣም መልካም ነው። ቀጭኑ ዘ-ቄራ ማሳሰቢያ አለው። ገንዳዎች የኢህአዴግን ስራና ሃላፊነት በመወጣት ለድህነት ሰለባዎች "የላቀ" አስተዋጽኦ እያበረከቱ ስለሆነ የሽልማት ኮሚቴ ይቋቋምላቸው። ገንዳዎች በሚወጣላቸው ደረጃ መሰረት ተለይተው ይሸለሙ። የጥሬ ስጋ ተጠቃሚዎችና አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሽልማቱን ለግል ውዳሴ … [Read more...] about “ዘላለማዊነት ለገንዳዎች!! ዘላለማዊ ክብር ለገንዳዎች”
የመምህራን ፍዳ
‹‹እኔ ጆርጅ ቡሽን (ፕሬዚዳንት) አላደንቅም፤ ጠፈር ላይ የወጡትንም አላደንቅም፡፡ የማደንቀው እነዚህን ሰዎች ለትልቅ ደረጃ ያደረሷቸው መምህራንን ነው፡፡›› መምህራን የሀገር ምሰሶዎች... መምህርነት የሙያዎች አባት... መምህር የእውቀት ብርሃን...ይህ እውነት ነው፡፡ እውነቱ ግን ዛሬ ላይ ተጋርዷል፡፡ መምህርነትም ሆነ መምህራን የነበራቸው ክብር ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ መሬት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየወረደ ይገኛል፡፡ መምህራን በሙያቸው እያፈሩ ነው፡፡ እውቀታቸውን እየሰሰቱ ነው፡፡ አዎ፣ መምህራን ጫንቃቸው ጎብጦ ነገን በደበዘዘ ተስፋ የሚጠባበቁ ‹ምስኪኖች› እየሆኑ ነው፡፡ ግን እንዴት? ካድሬነት Vs መምህርነት ወጣት ነው፤ ገና ለስራው ዓለም ብዙ አበርክቶት የሚጠበቅበት፡፡ ወጣቱ በአዲስ አበባ አብዮት ቅርስ መሰናዶ ት/ቤ የኬሚስትሪ መምህር ነው፡፡ በስራው ዓለም ለአራት ዓመታት … [Read more...] about የመምህራን ፍዳ
የደብተራው አምሳሉ ጡዘት!!!
ደብተራው አምሳሉ የቅድመ አያቶቹን ታሪክ ይዞ ፉከራና ቀረርቶውን ያስነካዋል፡፡ ነጻነትህ ጥሩ ሆኖ ሳለ፤ ደብተራነትህ ሳይጎዳህ የቀረ አልመሰለኝም፡፡ ግድ የለህም ጎድቶሃል፡፡ ምላሽ ይሁናችሁ ብለህ የደገምከው የመሰል አያቶችህን ተረት ነው፡፡ የዛን ዘመን ተረት ደግሞ ታሪክ እንዲሆን ትወዳለህ፡፡ በሌላ ወገን ያለውን ለማመን ግን አሻፈረኝ ባይነትህ ገርሞኛል፡፡ በመሠረቱ የወደዱትን ጽፈው ታሪክ አስብለው ያለፉት ያንተው ነገስታት እነሆ ዛሬ ላይ ታሪክ አልባ ሀገር ብትኖረን ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስባለሁ፡፡ የእራሳቸውን ማንነት ለማግዘፍ ሲሉ፤ ቅራቅንቦዋቸውን ሁሉ በመዝገብ ሲያኖሩ ከርመው፤ አንዳች እውነት ፍለጋ ምን ያህል እያደከሙን እንዳሉ ሳስብ አዝናለሁ፡፡ ነገስታቱ በረባ ባልረባው ሁሉ የእነርሱን ጀብድና መልካምነት አስፍረው አልፈዋል፡፡ አንዳንዴም ሳስበው በንግስናቸው ወራት ጦርነት … [Read more...] about የደብተራው አምሳሉ ጡዘት!!!
የሽብርተኝነት እንቆቅልሽ
መንግስታት በተለያየ መልኩ ትርጉመው ያቀረቡትን ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ህግ ያወጣሉ፡፡ በእርግጥ በአዲስ መልክ በሽብር ላይ የታወጀው ዘመቻ በአሜሪካ ግፊት የመጣ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 አሜሪካ ከደረሰባት የሽብር ጥቃት በኋላ "war on terror" እንዲሁም "counter terrorism" የተሰኙ ዘመቻዎችን ነድፋ ተንቀሳቅሳለች፡፡ አሜሪካ ወዳጅም ሆነ የቀዩ ባላንጣዎቿን ሳይቀር ደልላም ሆነ ተማጽና የጀመረችው ይህ "ጸረ ሽብር ዘመቻ" መንግስታት በየ አገራቸው የራሳቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁ አፋኝ "የጸረ ሽብር" ዘመቻ እንዲያወጡ እድል ሰጣቸው፡፡ አሜሪካ የሰብአዊ መብት ይጥሳሉ እያለች ስትወቅሳቸው የነበሩ ስርዓቶች ሳይቀሩ የተደላደለ የዴሞክራሲያዊ መሰረት ባልተጣለበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን የሚደፈጥጡ አዋጆች አጽድቀው ሲተገብሩ ከሀያሏ አገር የገጠማቸው ወቀሳና … [Read more...] about የሽብርተኝነት እንቆቅልሽ
ኢህአዴግ እንደ ናቡከደነፆር
በአንድ ወቅት የዓለም ገናና ንጉስ የነበረው የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር ለ43 ዓመታት ባቢሎንን ገዝቷል፤ በስተሰሜን ሶሪያ በምዕራብ በፍልስጤም እስከ ግብፅ ግዛቱን አስፋፍቷል፡፡ ይህ ንጉስ ህጎችን ከመቀፅበት ይደነግጋል፣ ይለውጣል፡፡ ለእሱ ስርዓት ተገዥ ያልሆኑትን ያስራል፣ ይገርፋል፡፡ ንጉስ ናቡከድነፆር በጣም የሚፈራ እና ኃይለኛ ንጉስ ቢሆንም ከመውደቅ ግን አልዳነም፡፡ ለማንኛውም የዚህ ንጉስ ታሪክና የሀገራችን መንግስት ስርዓት ብዙ የሚያመሳስላቸው ነገሮች ስላሉ እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡፡ ንጉስ ናቡከድነፆር በዘመኑ በጣም የሚፈራ እና የማይደፈር እንደመሆኑ መጠን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው፡፡ በዚህም መሰረት ነው የሌለባቸውንና መልክ መልከኞችን ጥበብና ዕውቀት የሞላባቸውን በብልሀት ዳኞችንና አስተዋዮች የሆኑትን በንጉሱም ቤት መቆም የሚችሉ ብላቴናዎችን በእስራኤል ልጆች … [Read more...] about ኢህአዴግ እንደ ናቡከደነፆር
የክልል እና የፌዴራል ምርጫ!
ምርጫ 2005 የአካባቢ (የክልል ቀበሌ፣ ወረዳ እና ከተሞች) እንዲሁም የእራስ ገዞቹ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ምክር ቤቶች ምርጫ ነበር። ብዙ የተወራለት የ33ቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ቢያንስ ቢያንስ በአዲስ አበባ ከተለመደው የተቃዋሚዎች ምርጫ ሽሽት የተሻለ ነገር ሊሰራ ነው ብለን በተስፋ ስንጠብቀው ምርጫው ሲቃረብ ስለ ህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነንነት የማናውቅ ይመስል እንደ አዲስ ዜና በህውሃት/ኢህአዴግ ስር ምርጫው ነፃ አይሆንም አለን። ወዲያው እራሱን ከምርጫ ማግለሉን ገለጸለን። በዚህ አይነት የአዲስ አበባን ምክር ቤት 138 መቀመጫ እና የከንቲባውን ቦታ ካለምንም ፉክክር ተቃዋሚው በነፃ ለህውሃት/ኢህአዴግ በማስረከቡ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና ለማግኘት ሳይቀር በዚህ ምክር ቤት ስር በመጉላላት ላይ ይገኛል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የክልል እና የፌዴራል ምርጫ!
ነገረ ኢትዮጵያ
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ነገረ ኢትዮጵያ
ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ፈጠረ ወይስ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን?
እንደሚታወቀው በሕወሓት የትጥቅ ትግል ዘመን የትግራይ ሕዝብ ከሞላ ጎደል ሊባል በሚችል ደረጃ ለሕወሓ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያደርግ ነበር፡፡ ይሄንን ዓይነት ገደብ የለሽ ድጋፍ የትግራይ ሕዝብ ለሕወሓት እንዲሰጥ ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ተብለው ሲጠቀሱ የምንሰማቸው፡- የሕወሓት ታጋዮች ልጆቹ የአብራኩ ክፋይ ስለሆኑ፡፡ ወያኔ የትግራይ ሕዝብ ለደርግጥላቻ እንዲኖረውና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለመድረግ ደርግ በሕዝቡ ላይ የፈጸመው አስመስሎ የፈጸማቸው የግፍ ሴራዎች ስለሰመሩለት ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ‹‹ወደፊት እንዲህ እንዲህ አደርጋለሁ›› ብሎ ቃል በመግባቱና በሕዝቡም በመታመኑ፡፡ እንደነሱ አገላለጽ “ኢትዮጵያ ውስጥ ለሺህዎች ዓመታት በነበረው አገዛዝ ተረግጠው፣ ተንቀው፣ በማንነታቸው እንዲያፍሩ፣ እንዲሸማቀቁ፣ የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው በመደረጉ እንደዜጋ ባለመታየታቸው … [Read more...] about ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ፈጠረ ወይስ የትግራይ ሕዝብ ወያኔን?
ሆሳዕና
ከቤተ ፋጌ እስከ እየሩሳሌም ማቴዎስ ም.፪፩፣ ፩-፩፯ ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተ ፋጌ ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር ሂዱ ቅደሙና አምጡልኝ ፈታችሁ ማንምደግሞበዚህ አንዳችም ቢላችሁ በሉና ንገሩት ጌታ አስፈልጎታል ይሄንን ሲሰማ ወዲያው ይሰዳታል። ፅዮን ሆይ ንጉስሽ ባህያ ጀርባ ላይ ይመጣለንዳለው አስቀድሞ ነብይ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው አመጡለት እንዳዘዘው ሆነ እንዲፈጸም ትንቢት። ባህያ ተቀምጦ እየሱስም ሲደርስ ከህዝቡ ብዙዎቸያነጠፉ ልብስ ሌሎችም እንዲሁ ከዛፉ ጫፍ ጫፉን ቆርጠው በመጎዝጎዝ ሸፈኑት መንገዱን ቀድመው የደረሱ የተከተሉትም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም የተባረከ ነው መጪ በጌታ ስም እያሉ በመጮህ … [Read more...] about ሆሳዕና









