ሰላም ወገኖቼ!! ተጠፋፋን። ግን አንለያይም። ድሮ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜ ነበር። እሁድ እሁድ ወታደሮች ከደጀን፣ እናትና አባት፣ ቤተሰብ ከቤት ሆነው ይኮሞክሙት ነበር። አሁን ግን ለምን ተከለከለ? ባድመ፣ ሽራሮ፣ ዛላምበሳ፣ ገመሃሎ፣ ላከ ኤርትራም አሉ፤ ዘላበድኩ መሰለኝ … ብቻ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜው ትዝ ብሎኝ ነው። ቀጭኑ ዘ-ቄራ ነኝ!! “የለቅሶ ማስተላለፊያ የአየር ሰዓት/ክፍለ ጊዜ ቢጀመር ጥሩ ነው። ምርጫውን ያደምቀዋል” የሚል አስተያየት ሟርተኞች ያቀርባሉ። ግን ምን አለበት የከፋቸው ቢያለቅሱ። በየጓዳው እያለቀሱ ነው። አደባባይ ወጥተው ቢያለቅሱ ምን ነውር አለው? ለመለስ ደረት እየተመታ ሲለቀስ የአየር ሰዓት ተፈቅዶ የለ? ለሞተ ሰው ከተፈቀደ በህይወት ላለው፣ ግብር ለማያጓድለው ለምን ይከለካል? ወይስ ነዋሪው በሟች ተበልጧል? ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲባል … [Read more...] about መለሰ ዜናዊ ናፈቁኝ – የለቅሶ አየር ሰዓት አማረኝ
ሰማያዊ ቀን!
የሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መጋቢት 20 ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡ በትዕይንቱ የወጣው ሕዝብ ነጻነት እንደሚፈልግ፤ ስቃይ፣ አፈናና ስደት እንደበቃው ባሰማው መፈክር አሰምቷል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ ከፎቶዎች ጋር በማጀብ ከሰልፉ ዝግጅት ጀምሮ በየሰዓቱ በፌስቡክ በለቀቀው መረጃ መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በጅማ፣ በአዲስ አበባ፣ በሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በጭሮ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልቂጤና ሌሎችም ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ እንደተለመደው የኢህአዴግ ፖሊስ ሰልፉን በማጨናገፍ፣ ተሰላፊው ሰልፉን ጀምሮ ለማብቃት የወሰነበት ቦታ እንዳይደርስ በመከላከል ድርጅታዊና ወገናዊ ሥራውን አከናውኗል፡፡ በየከተማው በተካሄደው ትዕይንተ ሕዝብ ሰልፈኞቹ የሚከተሉትን መፈክሮች አሰምተው እንደ ነበር ከዜናው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል፡ ነፃነት እንፈልጋለን፣ ነፃነት፣ … [Read more...] about ሰማያዊ ቀን!
ቆራጥ ጀግና ማነው?
አንድነት ይፈጠር - ሀገር ነጻ ትውጣ ንብረትም ይቅርብኝ - ምንም ነገር ልጣ ዳሩ መሀል ሳይሆን - ድንበሩ ተደፍሮ ርቱዕ አንደበት - እንዳይቀር ተቀብሮ ጋዜጠኝነትም - እንዲኖር ተከብሮ ቸነፈር ረሀብ - ሙቀቱን ሳይፈራ ውሎ የከረመ - ከታጋዮች ጋራ ጽናቱ ጠንካራ - ወገኑን የሚወድ ጌትነት የጠላ - ጭቆናን ለመናድ ነጻነት ናፋቂ - በደል የመረረው ውነተኛ ታጋይ - ቆራጥ ጀግና ማነው? … [Read more...] about ቆራጥ ጀግና ማነው?
“የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ። የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው። አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች … [Read more...] about “የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
ኦነግ ሲከተል የነበረው መንገድ ስህተት እንደነበር በይፋ በመናገር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የተሰኘውን አዲስ ድርጅትና ወኪሎች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት አቶ ሌንጮ ለታ ተቀባይ በማጣታቸው ወደመጡበት የተመለሱት ኦህዴድ ባቀረበው ተቃውሞ መሆኑ ታወቀ። የኢህአዴግ አፈ ቀላጤ የስላቅ መልስ ሰጡ። ኦዴግ (ኦዲኤፍ) በ2012 ምርጫ ሊጋበዝ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታል። የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በመነጠል ከኢትዮጵያ (“አቢሲኒያ አገዛዝ”) መገንጠልን አማራጭ አድርጎ ለግማሽ ምዕተ አመት ሲወድቅ ሲነሳ የኖረውን ኦነግ ሲመሩ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ተቃውሞ ደርሶባቸው ነበር። የቀድሞው የትግል ጉዞ ስህተት እንደነበር በይፋ አስታውቀው ለድርድር ኢህአዴግ ደጅ የዘለቁት አቶ ሌንጮ ከጉዟቸው በፊት የተነሳባቸውን ተቃውሞ … [Read more...] about ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
Yemen in our prayers
Poor Yemen is fast becoming the new playground of every wanabe strong Arab regime in the Middle East. Yemen is a safe location where they could test their acquired toys and pretend to act like a real army fighting real battles. Yemen never have it good. It was not blessed with oil, the only commodity that sustains the Arab monarchs’. Yemen came out from the womb staggering and never seem to have acquired this thing called stability, freedom and democracy. It is said long time ago the Axumite … [Read more...] about Yemen in our prayers
የህፃናት አምባ ልጆች ትዝታና ቁጭት
ወቅቱ 1973 ዓ.ም ነበር፡፡ አገሪቱ ከተለያዩ የውስጥና የውጪ ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችበት ጊዜ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ልጆቻቸውን ያለ አሳዳጊ ጥለው በየጦር ሜዳው ወድቀዋል፡፡ አሳዳጊና ተንከባካቢ ያጡት ህፃናት በየጎዳናው መውደቃቸው ያሳሰበው የደርግ መንግስት፤ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበሩት መንግስቱ ኃይለማርያም ልዩ ትዕዛዝ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ህፃናት አምባ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጅራ አውራጃ፣ በአላባ ቁሊቶ ወረዳ፣ አላጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወላጆቻቸውን በጦርነትና በሌሎችም ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ያጡ ህፃናትን ተቀብሎ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት፣ በትምህርትና በሥነ ምግባር ኮትኩቶ የማሳደግን ዓላማ አንግቦ የተቋቋመው አምባው፤ “ሰብለ አብዮት”፣ “መስከረም ሁለት ኦጋዴን”፣ … [Read more...] about የህፃናት አምባ ልጆች ትዝታና ቁጭት
“የልማታዊ” እና “ሁለገብ” ጋዜጠኞች አንድም – ሁለትነትም
ጋዜጠኝነት ትልቅ ክብር የሚሰጠው፣ የራሱ የሆነ መርህና ስነ-ምግባር ያለው፣ ጠያቂነትን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትንም በውስጡ የያዘ የሙያ መስክ ነው። ለዛም ነው ጋዜጠኛ የሕዝብ አንደበት፣ አይንና ጆሮ ነው የሚባለው። ሕዝብ በሚከበርበት ቦታ ሁሉ ጋዜጠኛም ይከበራል። ሕዝብ በሚዋረድበት፣ በሚታፈንበትና በሚዋከብበት ስፍራም ጋዜጠኛ ይዋረዳል፣ ይሳደዳል፣ ይታፈናል፣ ይዋከባል፣ ይታሰራል፣ ሲከፋም ይገደላል። ይህም በሕዝብ፣ በመንግሥትና በጋዜጠኛ መካከል ያለውን ቁርኝት በደንብ ያሳያል። ሕዝብና መንግሥት ልብ ለልብ ሊገናኙ የሚችሉት ጋዜጠኛ ሲኖር ነው። የሁለቱን የልብ ትርታ እያደመጠና ያንዱን ላንዱ እያስደመጠ በመካከላቸው ገደል እንዳይኖር ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። ጋዜጠኞች ይህን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት ከሚጠበቅባችው ነገሮች ዋነኛውና መሰረታዊው ነገር የሙያውን ሥነ-ምግባርና መርሆዎች ጠንቅቆ … [Read more...] about “የልማታዊ” እና “ሁለገብ” ጋዜጠኞች አንድም – ሁለትነትም
Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD): Update
In our April 30 2014 commentary which appeared on several media outlets, we outlined the fallacies of the Egyptian policy towards GERD. It appears that the last few months have witnessed breath-taking diplomatic developments. For one, Egypt has returned to the African Union. It also has been reported that there were several rounds of side and formal meetings between Ministers and the Heads of States and Governments of Egypt, Ethiopia and Sudan. Egypt has also shown a renewed interest on … [Read more...] about Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD): Update
በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል”
ኢህአዴግ በሥልጣን በቆየባቸው 25 ያህል ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ መቶ ዝሆኖች ውስጥ ከዘጠና በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፣ ወደ ጎረቤት አገር ተሰድደዋል፣ የደረሱበት አይታወቅም፣ . . . ሲሉ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ዛሬ (አርብ) ዘግበዋል፡፡ የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ ኢህአዴግ ከቻይና ጋር ከተፋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የዝሆን ቀንድ ንግድ እየተጧጧፈ እንደሄደ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በዚህም “ጮማ” ንግድ ውስጥ ቢጂንግን፣ ሲንጋፖርን፣ ታይላንድን፣ … መመላለሻቸው ያደረጉ ቱባ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ይጠረጠራሉ፡፡ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል”










