የኢሳት መዝሙር ተበረከተ ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ። በቦታው ላይ ዝግጅቱን ለመካፈል የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የተገኙት ደግሞ ታዋቂዎቹ የኢሳት ጋዤጠኞች መሳይ መኮንን እና አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ከተንገላቱት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ውስጥ ዮሀን ፐርሾን ናቸው። ዝግጅቱን በጸሎት የከፈቱ በክርስትና ኃይማኖት በኩል ቄስ ፍስሀ ተስፋዬ፣ ሙስሊሙን በመወከል ደግሞ የተናገሩት ሀጂ ሁሴን ሺፋ ሲሆኑ፤ የጸሎቱ ሥነሥርዓት … [Read more...] about በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
“ባንዲራ ጨርቅ አይደለም” የኢህአዴግ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን – ኢብኮ
• የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለአራተኛ ጊዜ በሚዲያ እንዳይተላለፍ ተከለከለ • ኢብኮ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት "አላስተላልፍም" ብሎ መልሷል • "ኢብኮ ከገዥው ፓርቲ ጋር ወግኗል" አቶ ዮናታን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት "አላስተላልፍም" ብሎ መመለሱን ዛሬ የካቲት 29/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኢብኮ በደብዳቤው "የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልዕክታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው ሰንደቅ አላማ ምስል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክልና ህገ መንግስቱን…. የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል" በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል "ይህ የኢብኮ ተግባር የሰማያዊን ፕሮግራም ላለማስተላለፍ … [Read more...] about “ባንዲራ ጨርቅ አይደለም” የኢህአዴግ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን – ኢብኮ
ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
ሰማያዊ ፓርቲ "ኢህአዴግ" የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹'ግንባር' ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ የሚደራጅ አካል ነው፡፡›› እንደሚል ገልፆ፣ ግንባር የሆነው ኢህአዴግ እንደ ውህድ ፓርቲ ተቆጥሮ በስሙ ዕጩዎች መመዝገባቸው ህገ ወጥ ነው ብሏል፡፡ ፓርቲው በላከው ደብዳቤ "በአዋጁ እንደተደነገገውም ኢህአዴግ አራት ህልውና ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ግንባር እንጂ ፓርቲ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አባል የለውም፡፡ በእርሱ ስም … [Read more...] about ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” በሚል ስም የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ጠየቀ
የአድዋ ድልና እኛ
1.መቅድም ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው። ጳውሎስ ኞኞ ኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በሚለው መጽሃፉ እኛ ስለራሳችን ስንጽፍ እናጋንናለን ስለዚህ የውጭ አገር ምእራባውያን የመሰከሩልንን ተጠቅሜያለሁ ይላል። የጳውሎስ አንደኛውን ምክር ከልብ ማድረግ ነው። ሁለተኛ ቢያሳዝንም እውነት ስለሆነ የሰዎች ስም በክፉ ይነሳል፤ አያት ቅድመ አያት ለሰራው ባንጠየቅም የአያቶቻችን ስም ሲነሳ አለመቀየም ነው። ከተቀየማችሁም ምን ይደረጋል ከመጻፍ አይቀርም። ራስ ደስታ ዳምጠው በሁለተኛው የጣሊያን ጦርነት የደቡቡን ውጊያ የመሩ ለጣሊያን … [Read more...] about የአድዋ ድልና እኛ
ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት። "ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!" አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል። "ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si … [Read more...] about ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!
በመጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ጓደኝነት ጥቂት የማልላቸው የኢትዮጵያዊነትን የሀገር የወገን የማንነት የቅርስ ተቆርቋሪነትን ስሜት የተላበሱ የሚያስቀናና የሚንቀለቀል ወኔ የተሞሉ እኅቶች ወንድሞች የመጽሐፈ ገጽ ጓደኝነት እየጠየቁኝ እየተቀበልኳቸው በተቻለኝ መጠንም እያበረታታሁ በጉድኝነታችንን እስከአሁን ቀጥለን ነበር፡፡ ለካ እነኝህ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱና ወኔ የተሞሉ ቁጭት የሚበላቸው እያልኩ የማወድሳቸውና የተቻለኝን ያህልም ሳበረታታቸው የነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ወያኔዎች ያሁሉ ስሜትና ተቆርቋሪነታቸውም ጭንብል ወይም ሽፋን ኖሯል ለካ ሰሞኑን እነኝህ ሰዎች በዘመቻ በየአቅጣጫው “ከአሁን በኋላ አማራ ስለ ራሱ ብቻ ማሰብ ይኖርበታል፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ስለራሱ ማሰብ ትቶ ለ80 ምናምን ብሔረሰብ ሁሉ ማሰብ ለድንበር መበላሸት አለመበላሸት ማሰብ የለበትም፣ አሁን 30 ምናምን ሚሊዬን … [Read more...] about አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!
የዘንድሮ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እኮ አለፈኝ!
"ዋ…!ድምፄ ባከነ" ብዬ አምርሬ ልበሳጭ ዳድቶኝ ነበር፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል" ብሎ የሚያውቀውን ይመርጣል፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ብሎ የብብቱን ይመርጣል፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች፤ በራሷ ላይ አሳጠረች" ብሎ አሳሪውን ይመርጣል፡፡ ወትሮስ፤ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን በሚሻልባት ሀገር፤ የብብት እንደተያዘ የቆጡ በማይወርድባት ሀገር፤ ማሰሪያዋን የበጠሰች በቅሎ ነፃ በመውጣት ፈንታ እስርዋን በምታጠብቅበት ሀገር፤ የኔ ድምፅ መጣ …ቀረ ልዩነቱ ምንድነው!? (ምንጭ: ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር - Hiwot … [Read more...] about የዘንድሮ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እኮ አለፈኝ!
በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ 52 አገራት ኢትዮጵያ 32ኛ!
* የናሚቢያው ፕሬዚዳንት የሞ ኢብራሂም ሽልማትን አሸነፉ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን በየዓመቱ በሚያወጣው የአፍሪካ መልካም አስተዳደር ጠቋሚ ኢትዮጵያ ከ52 አገሮች 32ኛ ወጣች፡፡ እ.ኤ.አ. የ2014 የሞ ኢብራሂም የመልካም አስተዳደር ጠቋሚ ከ30 ገለልተኛ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ታማኝ ምንጮች የተገኙ ከመቶ በላይ መለኪያዎችን በመገምገም ነው የአገሮች የመልካም አስተዳደር ደረጃን ማውጣቱን የገለጸው፡፡ ዋነኛ መለኪያዎቹ አራት ምሰሶዎች መሆናቸውን የሚገልጸው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፣ እነዚህም ሕዝቦች ከመንግሥታቸው የሚጠብቋቸውና መንግሥትም ማቅረብ የሚጠበቅበት ግዴታዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ ምሰሶዎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የመናገር ነፃነት፣ የንፅህናና የንብረት ባለቤትነት መብቶች ጥበቃን የሚዳስሱ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት ሞሪሺየስ፣ ኬፕ ቨርዴና ቦትስዋና ከአንድ እስከ … [Read more...] about በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ 52 አገራት ኢትዮጵያ 32ኛ!
ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
ምርጫ 2007ን ከሌሎች ምርጫዎች ሁሉ ልዩ የሚደርገው ምርጫ ቦርድ ከምርጫው በፊት ፓርቲዎችን (ተፎካካሪ) በማፍረስ ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎችን (ከ200 በላይ) አልመዘግብም ማለቱ እና በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል ደግሞ ወደ ምርጫው ለመግባት ተወዳዳሪው በዕጣ መለየት አለበት ማለቱ ነው፡፡ ዕጣው ደግሞ ለሁሉም ፓርቲዎች ሳይሆን ሰማያዊን ጨምሮ ጥቂቶች ላይ የተደረገ ነው፡፡ ይኸውም በማፍረስ እና በመከልከል ተጀምሮ ”ምርጫ በሎተሪ” መሆኑ ነው፡፡ በዓለም ላይ በታሪክ ዴሞክራሲ በዕጣ ይረጋገጣል ሲባል ኢትዮጵያ ብቸኛ እና የመጀመርያ አገር ስትሆን በኢትዮጵያም ለመጀመርያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ በመወዳደሩ እና እንደሚያሸንፍ ስለታመነ እንጅ በ2002 በአንድ የምርጫ ክልል ከ18 በላይ ፓርቲዎች መወዳደራቸው አይካድም፡፡ እርግጥ ነው ህግ ከተባለ አዋ/ቁ 532/99 አንቀጽ 49 እንደ … [Read more...] about ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!
የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት እንጅ የነበረውን አሮጌውንና ያላዋጣውን በመተው በአዲስና በተመከረ በተማረ ልብ አዲስ ሐሳብ አዲስ መንገድ ለመቀየስ አልተፈለገም፡፡ የሚጠበቀውና አስፈላጊው ግን ይሄኛው ነበር፡፡ ለነገሩ ከአንባገነን ሥርዓት ባለሥልጣናት ይሄ የሚጠበቅ አይደለም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንኳን በአንድ ሰው ዕድሜ ሽህ ዓመታት የመኖር ዕድል ቢሰጣቸው እንኳን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ሱሪያቸውን በአንገት ለማጥለቅ እንደታገሉ ያልፋሉ እንጅ አይ ሐሳቤ መንገዴ ይሄንን ያህል ዘመን ብታገልም ሊሠራ አልቻለም፡፡ ሊሠራ ያልቻለበትም የራሱ ምክንያት ችግር ስላለበት ሳይሆን … [Read more...] about አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!










