ተግባቢና በሳል ነው፤ ረጋ ባለ አንደበቱ የሚሰማውን በጥሞና መናገር ልዩ ያደርገዋል ፡፡ እምነቱን አጥበቆ ይወዳል፤ የእስልምና ሃይማኖት የሚያዛቸውን ተግባራት (ሶላት መስገድ፣ መጾም…) ፈጽሞ ሌሎች መሰሎቹ እንዲፈጽሙ ማድረግን ያውቅበታል፡፡ ከሌሎች የእምነት ተከታዮች ጋር የመግባባቱና ከሁሉም ጋር በአብሮነት መኖሩ ባጠቃላይ ማህበራዊ ኑሮ የሚጠይቀውን ግዴታ የመወጣት ልዩ ችሎታ አለው፡፡ ከማንም ሰው ጋር የመግባባት፣ ተጫውቶ የማጫወት ክህሎት አለው፡፡ ከቀለሙ በተጓዳኝ ሀይማኖታዊ እውቀቱም የተመሰከረለት ነው፡፡ ሙስሊም ተማሪዎችን በመሰብሰብ በስነ ምግባር እንዲታነጹና ለሀገራቸው ተቆርቋሪ እንዲሆኑ ያስተምራል፡፡ በግቢው ውሰጥ ተሰሚነት ካላቸው የሀይማኖት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ ካሚል ሽምሱን መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሳለ አውቀው ነበር፤ አንድ ባችም ነበርን፤ በህግ ፋከልቲ ተደልድለን ለአምስት … [Read more...] about ጥቂት ስለ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
“ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር! በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ ሆነን። 40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን እነሆ ግጥሙን በትህትና እያቀረብሁ፤ መዝሙሩ ብዙ ውጣ ውረድ ታሪክ ስላለው ወደፊት በሰፊው ይገለፃል። ፨ ፨ ፨ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረሰባዊነት አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
አዲስ ዓመት ያለ ተስፋ!?
የተወደዳችሁ የአገራችን የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም የየእምነቱ ምዕመናን፡- ይህንን መልዕክት የምጽፍላችሁ ወንድማችሁ ይህንን ጥሪ የማቀርብላችሁ እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለእናንተ ሃሳቤን ለማቅረብና እንደ እምነቴ ደግሞ በጌታችን የሱስ ክርስቶስ ባለኝ እምነትም ጭምር ነው። ይህንን ስል ሌሎች እንደ እኔ ዓይነት እምነት የሌላችሁን የሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች ያገለልኩ መስሎ እንዲሰማችሁ ወይም ከእኔ ጋር ተመሳሳይ እምነት በሌላችሁ ላይ ጫና ለማድረስ በጭራሽ ምኞቴ እንዳልሆነ አስቀድማችሁ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። የራሴን መግለጼ እንደ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር እና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ማንነቴን አሳውቄ ሃሳቤንም በዚያው መልኩ እንድትረዱልኝ ከማድረግ አኳያ ነው። ኢትዮጵያ በምንላት አገራችን ሁላችንም የተለያየ ሃይማኖት እንከተላለን፤ እንደየ እምነታችንም የአምልኮ ሥርዓታችንን … [Read more...] about አዲስ ዓመት ያለ ተስፋ!?
ባለቤት ያጣ ሕገ መንግሥት?
የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና በሌሎች ግለሰቦች ላይ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 60/89፣ 368/95፣ 622/2001 እና የወንጀል ሕግን በመጥቀስ፣ በሥልጣን አለአግባብ በመገልገልና በጥቅም በመተሳሰር የቀረጥ ነፃ መብትን ያላግባብ በመገልገል፡ እንዲመረመር አለማድረግ ወይም እንዳይመረመር ማድረግ፣ ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ዕቃዎች (መድኃኒቶች) በማስገባት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው፣ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ እያለ አዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ወጥቷል፡፡ አዲሱ አዋጅ ነባር የጉምሩክ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ ሽሯል፡፡ ስለዚህም ከላይ የተጠቀሱት ድርጊቶች በአዲሱ ሕግ ወንጀልነታቸው ቀርቷል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 22 ንዑስ … [Read more...] about ባለቤት ያጣ ሕገ መንግሥት?
መልካም አዲስ ዓመት!
የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣ መውጣት መውረድ፣ የዓለም ህግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣ ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ..፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና..፣ አንዴ ጽልመት..፣ አንዴ ብርሃን..፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤ ስትወድቂ..፣ ስትነሺ..፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣ ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት! (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መልካም አዲስ ዓመት!
የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!
ከልብ በመነጨ፣ ፍጹም በሆነ የወገን ፍቅር በሶማሊያ በውትድርና ላሉ ወገኖች ፈጣሪ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንመኛለን። በማያውቁት ጉዳይ የበረሃ ጥሩር ለሚገርፋቸውና የነፍሳቸው ዋጋ በውል ለማይታወቀው ወገኖቻቸን እንኳን አደረሳችሁ ከማለት በላይ ሁሉም ወገኖች ድምጽ እንዲሆኗቸው እንጠይቃለን። በወር 30 ዶላር አበል ህይወታቸው ላለፈና አሁንም እያለፈ ለሚገኙት ሃዘናችን ትልቅ ነው። ትርጉም በሌለው ጦርነትና ለወደፊት ንጹሃን ዋጋ የሚከፈሉበት የፖለቲካዊ ቁማር ስትራቴጂ የደም ግብር ለመክፈል ሰልፍ ለያዛችሁ ፈጣሪ አሁንም ይድረስላችሁ!! ለራባችሁም ለጠገባችሁም፡- እንደ ልማዳችን እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ፣ እንቁጣጣሽ!! ስንል ለማለት ብቻ ባንለው ምንኛ ደስ ባለን ነበር። አዲሱን ዓመት ተቀብለን እልፍ ሳንል ባለንበት ቆመን ያረጅብናል። እኛም ያለ አንዳች ለውጥ ጎመን/አረም አሮብን … [Read more...] about የግጭት ምንቸት ውጣ የእርቅና የሰላም ምንቸት ግባ!!
“ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በህወሃት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አሰሙ”
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?" በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ነዋሪዎች ውይይት በተካሄደበት ጊዜ ነው። በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/13/2007 ዓም በአቶ ተስፋአለም ተወልደብርሃን (የመቀሌ ከንቲባ)፣ አቶ አሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን “የህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል?” የሚል አጀንዳ ተሰጥቶት ነበር። የትግራዩ አንጃ በጉባኤው ወቅት … [Read more...] about “ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በህወሃት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አሰሙ”
ሳሞራ ወይስ ሕወሃት “ሕገመንግሥቱን” የጣሱት? ወይስ ሁለቱም?
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ሳሞራ የኑስ ህወሃትን ለብሰው፣ ህወሃትን አጥልቀው (ጫማቸውና ሌላው አይታይም እንጂ) ህወሃትን ሆነው ታይተዋል፡፡ “ተጋብዘው ነው” ለማለት ለምትፈልጉ እንትኖች መልሱ ህወሃት ላይ ተጋብዘው ከተገኙ ወደፊት እንደ ሰማያዊ፣ መድረክ፣ ወዘተ ያሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ የፓርቲዎቹ አርማ ያለበት ባርኔጣ አድርገው ይገኛሉ ማለት ነው - የተነፈሰ ሃሳብ ነው፡፡ ሳሞራ ህወሃትን ሲያይ ዋለ ተቃዋሚ ፓርቲ የት ነሽ እያለ ከነጠላው ፉከራ መልስ - “ሕገመንግሥቱ” ያለጥርጥር ተጥሷል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ “ሕገመንግሥቱንና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ …” በሚል ክስ መመሥረት አለበት ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ተከሳሽ “አሸባሪ” ሊባል ነው፡፡ ከዚያ ተከሳሽ ወደ … የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር … [Read more...] about ሳሞራ ወይስ ሕወሃት “ሕገመንግሥቱን” የጣሱት? ወይስ ሁለቱም?
ጀርመን አገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ኮፐቲክ ቤተክርስቲያን የጋራ ሲኖዶስ አቋቋሙ!
በጀርመን የኦርየንታል (የመካከለኛው ምስራቅ) ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት አንድ የጋራ ሲኖዶስ ለመመስረት ስለፈለጉ፤ ትላንት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን እርምጃ ወስደዋል። በዚህም መሰረት ጳጳስ አንባ ዳሚያን (የኮፐት ኦርቶዶክስ) እና ሊቀጳጳስ ሙሴ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ) ውል ተፈራርመዋል። በኮፕት ገዳም የውል ሰነድ ፊርማ፤ ሊቀጳጳስ ሙሴ (2. ከገራ ወደቀኝ) እና ጳጳስ አንባ ዳሚያን (የመካከለኛው ) (ከመሃል) ፊረማቸውን በውሉ ሰነድ ላይ አስቀመጡ። በዚሁ ጊዜ በቦታው የነበሩ፤ አባ ዳዊት ሙሳ ከግብጽ እንዲሁም የገዳሙ ጎብኝ እንግዶች/ካቶሊኮች/ ሞሲኞር ፔተር ፎን ሸታይኒትጽ (ከግራ) እና ዲያቆን ክርስቶፍ ፐሪንስ ቤተልሄም (ከቀኝ) እንዲሁም ሚዛን ገብሩ (ሁዋላ ከግራ) ማግዳሌና ግርማ፤ ሳራ ኪዳኔ እና ሞገስ ተሾመ … [Read more...] about ጀርመን አገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ኮፐቲክ ቤተክርስቲያን የጋራ ሲኖዶስ አቋቋሙ!
ሻዕቢያ ህወሃትን አስጠነቀቀ
ቀደም ሲል የአባትና ልጅ “አፈጣጠርና ግንኙነት” የነበራቸው ወዳጆች ሻዕቢያና ወያኔ ያልተጠናቀቀውን የባድመን ጦርነት ካካሄዱ በኋላ ለዳግም ግጥሚያ ዝግጅት እያደረጉ ነው። “የጦርነቱ ሁኔታ” ያሳሰበው ሻዕቢያ በማስታወቂያ መ/ቤቱ በኩል ለህወሃት ማጠንቀቂያ ሰጥቷል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዘገበው መሠረት መግለጫው ህወሃት ኤርትራን እንዲወጋ የአሜሪካንን ይሁንታ አግኝቷል ብሏል። የፈረንጅ የቀን አቆጣጠር የሚከተለው ሻዕቢያ በማስታወቂያ መ/ቤቱ በኩል 4 September 2015 ያወጣው መረጃ እንደጠቆመው ህወሃት የተለመደውን የጦርነት አታሞ እየመታና ሳንጃ እየሳለ እንደሆነ ጠቁሟል። የህወሃት አገዛዝ “ሌሎች ክፍሎች ከኤርትራ ጋር እንዳይወግኑ ትንኮሳ እያደረገ” መሆኑን የጠቆመው መግለጫ ወያኔ በኤርትራ ጦርነት ማካሄድ እንዲችል ከአሜሪካ ይሁንታ ማግኘቱን በገሃድ … [Read more...] about ሻዕቢያ ህወሃትን አስጠነቀቀ










