• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኢትዮጵያ ቅደሚ!”

September 14, 2015 07:55 am by Editor 2 Comments

የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር!

በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና  አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ  ሆነን።

40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን እነሆ ግጥሙን በትህትና እያቀረብሁ፤ መዝሙሩ ብዙ ውጣ ውረድ ታሪክ ስላለው ወደፊት በሰፊው ይገለፃል።

፨      ፨     ፨

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ    ኢትዮጵያ ቅደሚ

በኅብረሰባዊነት           አብቢ ለምልሚ!

ቃል ኪዳን ገብተዋል     ጀግኖች ልጆችሽ

ወንዞች ተራሮችሽ        ድንግል መሬትሽ

ለኢትዮጵያ አንደነት    ለነፃነትሽ

መስዋዕት ሊሆኑ          ለክብር ለዝናሽ!

ተራመጅ ወደፊት        በጥበብ ጎዳና

ታጠቂ ለስራ             ላገር ብልፅግና!

የጀግኖች እናት ነሽ      በልጆችሽ ኩሪ

ጠላቶችሽ ይጥፉ         ለዘላለም ኑሪ!

፨     ፨     ፨

የሙዚቃው ደራሲ አቶ ዳንኤል ዮሃንስ ነው፤ የሙዚቃ ትምህርት ቡልጋሪያ ነው የተማረው።

ማሳሰቢያ፦ በግጥሙ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ቃላት አንዳንድ ሰዎች በማወቅ ለተንኮል ወይም ባለማወቅ በየዋህነት የተሳሳተ ትርጉም ሲሰጡ ተደምጠዋል። ስለዚህ ማብራሪያ መስጠቱ ተገቢ ይመስለኛልና እነሆ!

  1. ኅብረሰባዊነት፡- ይህ ቃል በእንግሊዝኛው social democracy የሚባለው አቻ ነው እንጂ ኮሚኒዝም ወይም ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም አይደለም! በ1967ዓ.ም የታወጀው የደርግ መንግሥት የመጀመሪያው ፖሊሲ መመሪያም “የኢትዮጵያ ኅብረተ-ሰብአዊነት – Ethiopian Socialism” እንደነበር ያስታውሷል! የገጣሚውም የቀድሞውም ይሁን የአሁኑ የፖለቲካ አቋም እንደ ስዊድን በመሳሰሉት አገሮች እንዳለው አይነት “ኅብረሰባዊነት social democracy” ነው!
  2. ጀግና፡- ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የጀግኖች አገር መሆኗ እየታወቀ አንዳንድ ተንኮለኞች “ደርጎችን ነው” የሚያሞግሰው ሲሉ ተደምጠዋል! በፊትም አሁንም ወደፊትም እምዬ ኢትዮጵያ የጀግኖች አገር መሆኗን በፅኑ አምናለሁ።
  3. ጠላት፡- በኢትዮጵያውያን መካከል ብዙ ግጭቶችና ጦርነቶች ተካሂደዋል ከረጅሙ ታሪካችን እንደምንረዳው። ሆኖም የ“ጠላት” ጦርነት አይባልም! ምንም ጊዜ “ጠላት” የምንለው የውጨውን የባእድ ወራሪ ነው! ስለዚህ በግጥሙ ውስጥ “ጠላቶችሽ ይጥፉ!” ሲል ማንን እንደሆነ ግልፅ ነው። ከዚህም በቀር የኢትዮጵያ “ጠላቶች” – “ድርቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ድህነት፣ መሃይምነት፣ ስራ አጥነት…” ጭምር በመሆናቸው ድራሽ አባታቸው እንዲጠፋ ገጣሚው ምኞቱን መግለፁ ነው “ጠላቶችሽ ይጥፉ!” ሲል በመዝሙሩ ውስጥ!
  4. አንዳንድ ወዳጆቼ በየትኛውም አይነት ዴሞክራሲ የሚያምኑትን ሁሉ መዝሙሩ “እንዲያቅፍ” “በኅብረሰባዊነት ምትክ በዴሞክራሲ ሥርዓት ቢባል ጥሩ ነው፤ ሌላው እንዳለ ሆኖ” ይሉኛል። በበኩሌ ተቃውሞ የለኝም የትና ማን እንደሚዘምረው በበኩሌ ባላውቅም! እርግጥ የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ማኅበር አባሎች እዚህ ላስ ቬጋስና ዋሽንግተን ዲሲ ስብሰባ ላይ “ኢትዮጵያ ቅደሚ”ን ሲዘምሩ አዳምጫለሁ፤ አብሬም ዘምሬአለሁ።

በተረፈ በዚሁ ልሰናበት! ላላነበቡ/ላልሰሙ በበኩላችሁ አካፍሉ ጎሽ!

(ሙዚቃውን ለመስማት እዚህ ላይ ይጫኑ)

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አቶ አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ (Assefa GMT) የ“ኢትዮጵያ ቅደሚ” ደራሲ ናቸው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. wonchifu says

    September 15, 2015 06:53 pm at 6:53 pm

    ጎሽ አሰፋዬ! እውነተኛውን ኢትዮጵያዊ መዝሙር በማስታወሴ ረጅም እድሜ ይስጥህ::

    Reply
  2. mahlet says

    September 9, 2019 03:46 am at 3:46 am

    thx

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule