የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባርን በራሳቸው ልክ አሰፍተው፤ ተቃዋሚዎቻቸውን አስገድለው፤ ሌሎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርገው አገር በነጻ አውጪ ስም ለዓመታት የገዙት መለስ ሞተውም ሬሳቸውን እና በሕዝብ ደም የጨቀየውን “ሌጋሲያቸውን” ለመጠበቅ ዜጎች ከመኖሪያቸው ይፈናቀላሉ፤ እምቢ ያሉ ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመለስ መዘከሪያ ቦታ ለማስቀቅ የተፈቀደበት ደብዳቤ ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በሰነድነት ደርሶናል፡፡ ደብዳቤው እንደሚያስዳው ሬሣ ለማክበር ሕያዋን እንዲገደሉ፤ እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሬሣ ሕያዋንን ለሞት ሲዳርግ! ህወሃት በኃይል በሚገዛት ኢትዮጵያ የማይሰማ ጉድ የለም፡፡ (ጎልጉል) … [Read more...] about የመለስ ሬሣ በህይወት ያሉትን ዜጎች እያፈናቀለ ነው
ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው
የሰሞኑ ርህራሄ የጎደለው የመንግስት እርምጃን የሚያሳዩ ዜናዎችና ምስሎችን ማየት እጅጉን ያማል፡፡ ገዢዎቻችን የህዝብን ቅሬታ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የሚባል ነገር ከራቃቸው ሰነባብተዋል፡፡ በውይይት ከያዙት አቋም የተመለሱበት ጊዜያት ጥቂት ቢሆንም፣ ከህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ተወካዮችን በማስመደብ እና ሽማግሌዎችን በመላክ ድርድሮችና ውይይቶች ይደረጉ የነበሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመንግስትም ላይ ሆነ በስሩ በሚያስተዳድራቸው ተቋማት ላይ ለሚነሱ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች ዘግናኝ እርምጃዎች መውሰድን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተያይዞታል፡፡ ከሰሞኑም በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ዙሪያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረስ እየተወሰደ ያለው ዘግኛኝ እርምጃ የስርአቱን ማን አለብኝነትና የአመራሩን ጭካኔ በግልፅ የሚያሳይ … [Read more...] about ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው
እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ!!
ኢቢሲ “በቀኑ ዜና እወጃየ በጎንደር ማረሚያ ቤት ትላንት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተ ሰው የለም ብየ የዘገብኩት ኮማንደር ሰይድ ሃሰን የሚባሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ "ዋሽተው" መረጃ ስለሰጡኝ ነው … ሃቁ ግን 17 እስረኞች ከእሳቱ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርስ በእርስ ተረጋግጠው ህይወታቸው አልፏል ይህንንም የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን ኮሚሽነር አስተዳደር ሃላፊ በላይ ዘለቀ የሚባሉ (ስሙንማ ይዘውታል) ገልፀውልኛል” ሲል ማምሻውን አስተባብሏል … (አላግጧል) መቸስ የሞተ ሰው የለም ብለው 17 ከሞተ … 17 ሰው ብለው ካመኑ የሟቹ ትክክለኛ ቁጥርም ሌላ ሊሆን ይችላል!! የሆነ ሁኖ ከዚህ የተዘበራረቀ አሳፋሪ ዜና … ሁለት ነገር ተረዳሁ … 1ኛ፡ ብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያቀርብ ግድ የለሽ ተቋም መሆኑን አውቀናል፤ 2ኛ፡ ማረሚያ ቤቶቻችን በስራቸው ላሉት ዜጎች … [Read more...] about እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ!!
ስለ ችጋር
• ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ "እየበሉ" በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ • ችጋር የሚያጠቃው ማንን ነው? ትልቁና ዋናው የችጋር እንቆቅልሽ የዚህ ጥያቄ መልስ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ችጋር የሚያጠቃው ከገበያ ጋር የማይገናኙትን ምግብ አምራቾችን ገበሬዎችን፣ በተለይም እያመረቱ ከእጅ ወዳፍ ብቻ የሚኖሩትን ነው፤ እነዚህ ገበሬዎች የገጠሩ ሕዝብ፣ ማለትም የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻ ደሀዎች ናቸው፤ ኑሮአቸው ሁልጊዜም በችጋር አፋፍ ላይ ነው፡፡ • ችጋር ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ነው? ከላይ እንደተባለው በችጋር ላይ የሚወድቁት ገበሬዎች ከገበያ … [Read more...] about ስለ ችጋር
FAMINE, STARVATION AND DEATH IN ETHIOPIA RENAMED BY ITS GOVERNMENT AS “FOOD INSECURITY”
December 1, 2015, Washington, DC, According to some inside Ethiopia, NGO’s are being warned not to use the words “famine, starvation or death” in their food appeals. Neither are they to say that “children are dying on a daily basis,” or refer to “widespread famine” or say that “the policies of the government in Ethiopia are partially to blame.” Neither are they allowed to “compare the current crisis to the famine of the eighties.” Instead, the latest drought in Ethiopia is to be described as … [Read more...] about FAMINE, STARVATION AND DEATH IN ETHIOPIA RENAMED BY ITS GOVERNMENT AS “FOOD INSECURITY”
“አብዮቱና ትዝታዬ” ሲያከራክር ዋለ
* ደርግ የረሸናቸው የንጉሡ ባለሥልጣናት 60 አይደርሱም ተብሏል * መፈንቅለ መንግሥቱ ቢሳካ ኖሮ ኤርትራ ከመገንጠል ትድን ነበር? * በዓሉ ግርማ መገደሉን ኮሎኔል ፍስሃ በመጽሐፋቸው ይፋ አድርገዋል በደርግ ዘመን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉትና በመጨረሻም የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ፍስሀ ደስታ፤ከ20 ዓመት እስር በኋላ የፃፉት “አብዮቱና ትዝታዬ” የተሰኘ መፅሐፋቸው፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በሂልተን ሆቴል ሲመረቅ አብዛኛውን ታዳሚ ለክርክር ጋብዟል፡፡ ደግነቱ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ከታደሙት አብዛኞቹ የ1960ዎቹ ትውልድ አባላት ነበሩ፡፡ የደርግ ባለሥልጣናት፣ ከፍተኛ የጦር አዛዦች እንዲሁም ከደርግ በተቃራኒ ቆመው ሲፋለሙ የነበሩ የኢህአፓ፣ መኢሶንና ሌሎች በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች … [Read more...] about “አብዮቱና ትዝታዬ” ሲያከራክር ዋለ
አንድ:- ከመጠምጠም መማር ይቅደም
በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፡፡ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቡክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው፡፡ ምናልባት 99.99% በእኔ ሰፈር ያሉ የፌስቡክ ተሳታፊዎች ወደፌስቡክ የሚገቡት ለመናገር ነው፤ መናገር የህልውናቸው ምስክር ወይም ማረጋገጫ አድርገው የሚወስዱት ጥቂት አይደሉም፤ ካልተናገሩ የሌሉ ይመስላቸዋል፤ ዋናው ነገር መናገር ይሆንና የሚናገሩት ነገር ወይም ጉዳይ ሌላው ቀድሞ ከተናገረው ጋር የሚያያዝ … [Read more...] about አንድ:- ከመጠምጠም መማር ይቅደም
ችጋርና የእውቀት ችጋር
በፈረንጆች ባህል እውቀት ሥልጣን ነው፤ እንዲያውም እውቀት ኃይል ነው ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ባህል እውቀት ሥልጣን የለውም፤ እንዲያውም ሥልጣን እውቀት ይመስለናል፡፡ በ1951 ዓ.ም. በትግራይ ችጋርን በዓይኔ አይቻለሁ፤ በጆሮዬ ሰምቻለሁ፤ በአካሌ ቀምሼዋለሁ፤ ጠኔ ይዞኝ ተደግፌ ወደቤቴ ገብቻለሁ፡፡ በመቀሌ ያየኋት አንዲት የመቀሌ ወጣት እናት ከነሕጻንዋ በአእምሮዬ ተቀርጸውና ተቆራኝተውኝ በሕልሜም በእውኔም እየወተወቱኝ ስለችጋር እንዳጠና አስገደዱኝ፡፡ ችጋርን እያገላበጥሁ ከሰባት ዓመታት በላይ አጠናሁ፤ የጥናቴ ውጤት RURAL VULNERABILITY TO FAMINE IN ETHIOPIA: 1958-1977 በሚል ርእስ በህንድ አገር፣ በኒው ዴልሂ ከተማ ታትሞ በ1977 ዓ.ም. (በአአ በ1984) ወጣ፤ በአሜሪካ የተማርሁበት ክላርክ ዩኒቨርሲቲ ለጥናቱ ድጎማ የሚሆን የ$30,000 ለቀዳማዊ … [Read more...] about ችጋርና የእውቀት ችጋር
በደልን መላመድ ባርነት ነው!
የማሰብ ነፃነት ማጣት ባርያነት ነው፤ ያሰቡትን አለመናገር: ባርያነት ነው፤ ያሰቡትን አለመጻፍ: ባርያነት ነው፤ ፍትህ ማጣት: ባርያነት ነው፤ ከገዛ አገሩ መሰድደ: ባርያነት ነው፤ ተማሪው "መሬት ለአራሹ" ብል በደሙ የዋጀውን የመሬት ባለቤትነት መብት: ከገበሬው ነጥቆ በማፈናቀል: በድንበር ዘለል ከበርቴ መቸብቸብ፤ የባርያነት ቀንበርን መልሶ መጫን ነው፤ ሠራተኛውን በዓለም አቀፍ ዘራፊ ኢንደስትሪዎች፤ በገዛ አገሩ ጉልበቱን ማስበዝበዝ: ባርያነትን ማስፈን ነው፤ ምሁራንን በአገራቸው ጉዳይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው በየምክንያቱ ማግለል: ባርነትን እንዲነግሥ ማድረግ ነው፤ ወጣቱን ለሥራ አጥነትና ለስደት መዳረግ አገርን መግደል ነው፤ ዝምታ ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል ነው፤ አድር ባይነት: ባርያ መሆን ነው፤ ሕዝብን በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች እንዲሆን ማድረግ: የባርነት ሥርአትን ማስፈን … [Read more...] about በደልን መላመድ ባርነት ነው!
Enough has not been said about the hyenas
I recently published an article on this blog titled ”me, my country and corruption”. Its about corruption. Where by I have tried to discuss the rampant corruption by the Ethiopian dictatorial regime. The article articulated the issue from different perspectives. Aiming to give a general frame work how systematically complicated its together with remedies. For any one reading this, I kindly request you to read my previous article to have the full grasp. Here is the link-Habtamu Bogale’s blog. I … [Read more...] about Enough has not been said about the hyenas










