ዘመን ፊትሽ ተከምሮ እየታዬ ስራሽ አምሮ እንቁጣጣሽ አንድ ብለሽ አርባ ድረስ እድሜ ቆጥረሽ እንደ ቤቶች የሳቅ ተውኔት እንደ ጨቤ ስካር ህይወት ሞት ራሱን ያሾፍሽበት ለምንድነው? በይ ንገሪኝ እባክሽን አደብቂኝ ባንቺው ቀዬ የተወለድኩ ፊደል በጄ እዛው የያዝኩ መስፍን ሜዳ የተራገጥኩ በጨበጣ ብይ ያስቆጠርኩ ቲቸር ታዬ ያስተማሩኝ ገብሬ ኩርኩም ያቀመሰኝ የሲሚንቶ ጭስ ያወዛኝ ቅዱስ ያሬድ ተሳልሜ ከሽፋ ቤት ተሰይሜ ያቶ ማሞን ኪኒን ቅሜ እዛው ኖሬ እዛው ያደኩ የቃጠሎው ቀን የተረፍኩ እኔ እማውቅሽ የማታውቂኝ የሰፈርሽ አንድ ስው ነኝ ይሄን ሁሉ ዘርዝሬልሽ ጥያቄዬን ስጠይቅሽ ዝም አትይም መቼም ከፍተሽ ፊት ለፊትሽ ተስፋሽ ሞልቶ እየታየ ዝናሽ ጎልቶ እንደጸደይ ባገር ፈክተሽ በህዝብ ፊት ደምቀሽ ታይተሽ በአዲስ አመት በንቁጣጣሽ በ´ለቱ ለት … [Read more...] about በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
Literature
ጽፈኪን
እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ
ከአዘጋጆቹ፤ ከጥቂት ወራት በፊት በወዳጃችን ወለላዬ ለቀረበው የበርካታ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩ ባለሥልጣናትን ፎቶ ለያዘው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተባበራችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን:: ከተለያዩ ምንጮ ያሰባሰቡትን ምላሽ ወለላዬ አጠር ካለች ግጥም ጋር በቁጥራቸው ቅደም ተከተል አቅርበውታል፡፡ ከዘመኑ መብዛትና መረጃ መዛባት ምክንያት በምላሹ ላይ ስማቸው ወይም ማዕረጋቸው የተዛባ ቢኖር ማስተካከያ ለሚሰጡ ሁሉ አሁንም በቅድሚያ ምስጋናችን ይድረሳቸው፡፡ መልስ በዝርዝር ማስቀመጥ - በቁጥሩ በስሙ ለመግጠም የሚያስችል - ነበረኝ አቅሙ ነገር ግን ለአንባቢ - እዚህጋ ሲቀመጥ እንደዚህ ሲሆን ነው - የሚጥመው ይበልጥ በማለት አስቤ - የሁሉም ዝርዝር ከስር አስፍሬያለሁ - በስማቸው አንፃር መርዕድ መንገሻ (ሜ/ጄኔራል) … [Read more...] about እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ
ሌቦ ነይ …
ማስታወሻ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የህወሃት አባል ወይም ተላላኪ እንደሆነ የታሰበ ግለሰብ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት (በፎቶው እንደሚታየው) ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን እንግሊዝ ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ለመጀመሪያ የፍርድ ምርመራ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኛው “ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ግለሰቡ “ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጾዋል። ይሁን እንጂ ዳኛው “ይህን ያህል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ ለጊዜው በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሚ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የወለላዬ ግጥም በዚህ ዘረፋ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ (ቅርብ የሆናችሁ … [Read more...] about ሌቦ ነይ …
“ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር! በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ ሆነን። 40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን እነሆ ግጥሙን በትህትና እያቀረብሁ፤ መዝሙሩ ብዙ ውጣ ውረድ ታሪክ ስላለው ወደፊት በሰፊው ይገለፃል። ፨ ፨ ፨ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረሰባዊነት አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about “ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
መልካም አዲስ ዓመት!
የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣ መውጣት መውረድ፣ የዓለም ህግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣ ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ..፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና..፣ አንዴ ጽልመት..፣ አንዴ ብርሃን..፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤ ስትወድቂ..፣ ስትነሺ..፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣ ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት! (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መልካም አዲስ ዓመት!
ጤፍ እንኳን ባቅሟ!
ትንሿ የ'ሕል ዘር፤ ዐይን እንኳ ብትገባ የማትቆረቁር፤ ድንገት ጠብ ብትል የማትገኝ ከምድር፤ ቁልቁል አሾልቃ በንቀት እያየች፤ በድሃው ወገኔ ከት ብላ ሳቀች! ........ እጅጉን አሾፈች:: አሹቅህን አውልቅ - ሽንብራህን ቆርጥም፤ ባቄላህን ጠርጥር - በቆሎህን ከርትም፤ እኔን ካሁን ወዲያ እንኳን ልትበላኝ፤ ድንገት በመንገድ ላይ ባይንህም አታየኝ፤ እያለች አፌዘች፤ በወገኔ ሳቀች !.......... በወገኔ አሾፈች !! አረም እንዳይውጣት - ወፎች እንዳይለቅሟት፤ ካቡን ዙሪያ ክቦ - ከብቶች እንዳይበሏት፤ አጭዶና ከምሮ - በሬዎች ለጉሞ፤ ሲወቃ እንዳልዋለ - ቀኑን ሙሉ ቆሞ_ _ _፤ በመንሽ አበጥሮ - በቁና ለክቶ፤ በሰፌድ አንፍሶ - በስልቻ ከቶ፤ ነቀዝ እንዳይበላት - ብርድ እንዳያጠቃት፤ ወቅቶ በጎተራ - እንዳላስቀመጣት_ _ _፤ አንተ አትቀምሰኝም! … [Read more...] about ጤፍ እንኳን ባቅሟ!
ትረገም ሆነብኝ!!
ልጇ ነፍሰ ገዳይ - ስለሆነ እርጉም እሱን የወለደች - እናቱ ትረገም ብለው ሲናገሩ እያሉ ሲያወሩ ... አትረገም ብዬ - ልጽፍ አሰብኩና ትረገም ሆነብኝ - “አ” እረሳሁና! … [Read more...] about ትረገም ሆነብኝ!!
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
ከአዘጋጆቹ፤ የጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ “እኚህ ሰው ማናቸው?” በሚል ዓምድ ሥር ለአገራቸው የለፉና የደከሙ ኢትዮጵያውያንን እንዲነሱ፣ እንዲወደሱ፣ እንዲከበሩ፣ … በማድረግ ግሩም ሥራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ባለፈው ጠቅሰን ነበር፡፡ እርሳቸው ባለባቸው በርካታ ኃላፊነቶች ለተወሰኑ ጊዜያት ሳይመቻቸው ቢቀርም አሁንም ግን “እኒህ ሰው ማናቸው” ዓምድ በልባቸው ነው ያለው፡፡ በመሆኑም ሰሞኑን ከቀድሞ ፎቶዎች መካከል የሆነውን ይህንን በመላክ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩትን በቁጥር በማድረግ እነማን እንደሆኑ እንደተለመደው ቢቻል በግጥም አንባቢያን በማቅረብ እንዲሳተፉ በግጥም ጥሪ አድርገዋል፡፡ በጃንሆይ ዘመን የካቢኔ አባላት በመሆን ሰርተዋል እኒህ የሚታዩት እስቲ እነማናቸው ግለጹ በዝርዝር በፎቷቸው አንጻር በተሰጠው ቁጥር፡፡ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፱
ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
ለረጅም አመታት፣ ለብዙ ዘመናት፣ ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣ መንግስት ሲረግጠኝ፣ ፖሊስ ሲነርተኝ፣ ሕጉ ሳይደግፈኝ፣ ዳኛው ቢፈርድብኝ፣ በቡድን ተካፍለው፣ በስም ተሸንሽነው፣ የሚጠልዟት ኳስ፣ የሚነርቷት ኳስ፣ ምትለጋዋ ኳስ፣ እኔ ራሴን መስላኝ፣ ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ። … [Read more...] about ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ
… አልሞት አለኝ
በስራው ላይ ልፈላሰፍ ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ የማደንቀው ሰው ነበረኝ ሳይሞትማ ሳይቀበር ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር የማደንቀው ሰው እያለኝ ልጽፍለት ተቸገርኩኝ አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና ሀይማኖቱን አጠንካሪ ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ ብዬ ልለው ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው በቁም ሆኖ ከምረዳው ከማከብረው ከማደንቀው እደርሳለሁ ሲሞትልኝ ከምድር በታች ሲውልልኝ ያንጊዜ ነው ስሙ ገኖ የሚነሳው እሱን ሆኖ የብዕር ጫፍ የሚመዘዝ እንባ የሚረጭ የሚተከዝ ሚጻፍለት ሚደነቀው ታሪክ ገኖ ሚነበበው ገንዘብ ከኪስ ሚመዘዘው ለሟች በድን አካሉ ነው ያን አይቼ ልምድ አብቶኝ የቆየ ወግ አንቆ ይዞኝ የማደንቀው ሰው … [Read more...] about … አልሞት አለኝ









