አቅቶን መለወጥ ለቅሶን በደስታ፤ ሃዘን ጠል አልብሶን ሳቅ ደርቦ ኩታ፤ ያንዱን ቤት ገንብቶ የሌላውን ሲያፈርስ፤ አንዱን ሳቅ አጅቦት ሌላው ከፍቶት ሲያለቅስ፤ ለቅሶ ሳቅ - ሳቅ ለቅሶ - እየደባለቀ፤ ግማሽ ጎኑ ሲያለቅስ - ግማሽ ጎኑ ሳቀ:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ
Literature
ጽፈኪን
የማይጠፋ ፍቅር
ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን በደቡብ አፍሪካ ያስመዘገበው ውጤት እስካሁን የብዙዎች መነጋገሪያ ዋና ሃሳብ ሆኗል፡፡ በተለይ ከእግር ኳሱ ጋር የታየው ወዳጅነት፤ አብሮነትና ተደጋጋፊነት ፖለቲከኞቻችንን “እንዴት ነገሩ፤ ካልሆነ … ብትሞክሩትስ?” የሚያስብል ሆኗል ቢባል የተጋነነ አይሆንም፡፡ ለዛሬ የግጥም ጨዋታ ይህንኑ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ወቅታዊ ጨዋታ እንደሚሆን በማሰብ ከድንቅዬ ገጣሚዎቻችን መካከል ብሌን ከበደ በፌስቡክ ላይ የለቀቀችውን ከታላቅ ምስጋና ጋር እነሆ ብለናል፡፡ ባለፈው “የጠቆሩ ልቦች” በሚል ላቀረብነው ጨዋታ ድንቅዬ ችሎታችሁን በግጥም በመመለስ ጨዋታውን ላስዋባችሁት በለው፣ Alelign፣ Yekanadaw kebede፣ ዱባለና inkopa እጅግ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ … [Read more...] about የማይጠፋ ፍቅር
ቅኔ
የዘወትር የድረገጽ ጋዜጣችን ተሳታፊ የሆኑት ወዳጃችን ዱባለ፤ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ያባታቸውን የኪነት ስራ አስባስበው ካሳተሙት መጽሕፍ ያገኘሁት የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔ ነው ብለው ገጣሚ ከሆነ ምስል ጋር የላኩልንን ግጥም ነው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡- ጎድን ከዳቢት ስብራዳ ይገባ ነበር ለእንግዳ አያችሁት ወይ ይህን ቀን ታላቅ ታናሽ ሲሆን? … [Read more...] about ቅኔ
ቆረቆረኝ መቃብራችሁ
በየከተማው በየገጠሩ በየጥሻው በየቆንጥሩ በለጋ ሕይወታችሁ ገና ፀሐይ ሳትመታችሁ፤ “ነፃነት ነፃነት የምትሹ ተዋጉለት አትሸሹ።” እያላችሁ ቆማችሁ፤ አባራሪ ግንባር ሆናችሁ ቀንዲል ብርሃን ተነስታችሁ፤ ፀሐይዋ በዕርጋታ በሀገራችን ወጥታ ገብታ፤ ጨለማው ፈርቶ ሸሽቶ ብርሃን ባገር ሞልቶ የማይታሰበውና ደረቁ ሀቅ በውጥረትና በጭንቅ ሴትና ወንድ ወጣቶች ሕፃናትና ሽማግሎች፤ የመኖር ሕይወት ትርጉሙን ለሌሎች ሕይወት መቆምን አስተምራችሁን ያለፋችሁ ቆረቆረኝ መቃብራችሁ። እሁድ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት (ስዕል: የገጣሚው) … [Read more...] about ቆረቆረኝ መቃብራችሁ
“መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
በበርካታዎች ዘንድ የተለያዩ ስሞች አሏቸው፤ የአደባባይ ምሁር፣ አንጋፋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ፣ ጋሼ መስፍን፣ ወዘተ፡፡ በእኛ ግምት ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ የሚለው ገጣሚ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በተለይ በቅርብ ዓመታት ያሳተሟቸው መጻህፍት፣ የጻፏቸው ጦማሮች፣ ወዘተ ይህንን ማዕረግ ሊያሰጥዋቸው ይችላሉ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ፕ/ር መስፍን በህይወት ዘመናቸው ካስተማሩትና ካስተላለፉት ዕውቀት በተጨማሪ እጅግ በርካታ መጻህፍትን በማሳተም ይህንን ለዘመናት የዳበረውን ዕውቀታቸውን ለመጪው ትውልድ እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ አራት መጻህፍትን አሳትመዋል፡፡ በመጪው ሚያዚያ ወር 83 ዓመታቸውን ከማክበራቸው በፊት ባለቅኔው መስፍን በሰማኒያዎቹ ዕድሜያቸው ይህንን ሁሉ ለማድረግ መብቃታቸው ከጻፉት መጻህፍትና አርቆ … [Read more...] about “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
“የጠቆሩ ልቦች”
“የጠቆሩ ልቦች” ይቺ አጉል ዘመናይ፣ የወንዜ ልጅ እቱ አፍሪካዊ መልኳ፤ “ደብሯት” ጥቁረቱ ፊቷን በ“ሜክ አፕ” እጇን በእንሶስላ ፀጉሯን ባንዳች ቀለም፣ ቀባችው ልትቀላ፡፡ ግን ባይገባት እንጂ፣ እንዲህ የምትደክም እንዲህ የምትለፋ … የቆዳችን ሳይሆን፣ የልባችን መጥቆር ነው አገር ያጠፋ፡፡ ሰለሞን ሽፈራው “ተወራራሽ ሕልሞች” መጽሐፍ ባለፈው “ሕልም እንኳ የታለ?” በሚል ርዕስ ላወጣነው ጨዋታ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት ዱባለ፣ በለው፣ inkopa እና Yekanadaw kebede ምስጋናችን እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ በዚህኛው አስደናቂ ቅኔዎችም ተዘርፈዋል፤ ወላድ በድባብ ተሂድና አገራችን አሁንም ባለቅኔዎችንና ጥበበኞችን እንዳላጣች እናንተ ምስክር ናችሁ፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ ለዚህኛው ጨዋታ ደግሞ እስቲ ተቀኙልን! (ፎቶውን ያገኘነው … [Read more...] about “የጠቆሩ ልቦች”
ሕልም እንኳ የታለ?
ሕልም እንኳ የታለ? በሕልሜ ተኝቼ፣ ሸጋ ሕልም አይቼ በአገሬ በአፍሪካ ዲሞክራሲ በቅሎ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መብቱ ተደላድሎ ወገኔ ሲያጣጥም የሰላምን ፍሬ ሽብር ተወግዶ በመላው አገሬ . . . ይህን እያለምኩኝ አልጋ ውስጥ አርፌ . . . ጥይት ቀሰቀሰኝ ከሞቀው እንቅልፌ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ከፀሐይ በታች መድብል 2004ዓ.ም “መሰላል” በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ ድንቅ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት በለው፣ ዱባለ፣ አሥራደው (ከፈረንሳይ) እና yeKanadaw kebede ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁ የቋጠራችሁት ግጥም በራሱ የግጥም ጨዋታ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለጨዋታ ያቀረብነው ግጥም ከዚህ በፊት “ሕልመኛው” በሚል ካወጣነው ጨዋታ ጋር በ“ሕልም” እንኳን የማይገናኝ መሆኑን ለመግለጽ … [Read more...] about ሕልም እንኳ የታለ?
እንዴት ሀገር (ህዝብ) ይጥፋ?
እንዴትሀገር (ህዝብ) ይጥፋ? ያለመተማመን ስለዘራን ዘር እንሰበስባለን የማያልቅ ‘መከር’። ‘’መግዛት’’ እውቀት ሆኖ፣ ገንዘብና ሀይል አቋራጭ ጎዳናው ‘መቦልተክ’ ሆኗል። ሃይማኖት ተንቃ ስትሆን መቀለጃ የእግዚአበሄርም ቃል ሆነ ምነገጃ። ሳይሰሩ ያገኙት ሀብት፣ ክብር - ዝና ያስከብር ጀመረ መናቁ ቀረና። ፈረሀ - እግዚአብሄር ከልባችን ወ’ቶ ህገ - አውሬ ይገዛናል ሰው-ከሰው አባልቶ። ለመሾም - መሸለም፣ መክዳት - መከዳዳት ምግባራችን ሆኗል ዋናው ሀይማኖት። እያለን የሌለን ስለሆን ተመፅዋች መጠሪያችን ሆነ እናንተ ለማኞች። እውነት ተገንዞ ስለተቀበረ ውሸት ገዥ ሆነና ሰው ለ’ሱው አደረ። ፍቅርና ሰላም ፈላጊ ስለአጡ ተባረው ሄደዋል በአገር እንዳይመጡ። በሌሎች ደም - እምባ፣ ንዋይ … [Read more...] about እንዴት ሀገር (ህዝብ) ይጥፋ?
መሰላል
መሰላል መሰላል ለመውጣት አለው ትልቅ ብልሃት፡፡ የላዩን ጨብጦ፣ የታቹን ረግጦ፣ ወደላይ መመልከት፡፡ እጆችን ዘርግቶ በኃይል መንጠራራት፡፡ ጨብጦ መጎተት የላዩን! ላዩ ታች እንዲሆን! አንድ ባንድ እየረገጡ፣ መሰላል የወጡ፡፡ ብልሆች የማይጣደፉ፣ ሞልተዋል በያፋፉ! ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ፣ የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ ሲወርዱ ግን ያስፈራል፤ የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡ (መስፍን ወልደማርያም፣ እንጉርጉሮ፣ 1967) yeKanadaw kebede “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ ላቀረቡት የግጥም ጨዋታ ዱባለ፣ በለው እና dawit ለጨዋታው ምላሽ ስለሰጣችሁ ከልብ እናመሰግናችኋለን፡፡ የጨዋታውን ደራሲ yeKanadaw kebede እንዲሁ፡፡ ስለ “መሰላል”ስ ምን ትላላችሁ? እስቲ ጨዋታውን አምጡታ!? … [Read more...] about መሰላል
ማነው ተጠያቂው?
ማነው ተጠያቂው? ለኅሊናችን፣ ለትወልድ፣ ለሀገር ሰው - ስለ ሰው ብሎ፣ እስቲ ሰው ይናገር፤ በዚች ዓለምችን፣ መለኪያው ምንድን ነው ከገዥና ተገዥ፣ ተጠያቂው ማነው? ጥቂቶች በቡድን፣ ብዙሀኑን ገፍተው የሰውን ስብዕና፣ ማንነቱን ገፈው፤ በጥይትም ይሁን፣ በታንክ ደፍጥጠው እነሱ እንዲገዙ … ማነው የፈቀደው? ሰለኅሊናችን፣ ስለ እውነት በሀቅ ሰው - ለራሱ ብሎ፣ ‘ራሱን ይጠይቅ። ብዙ በልተው - ብዙ ‘ለማበት’ ብዙ ተግተው - ብዙ ለመሽናት፤ …ለጮማ - ቅርናታቸው… …ለውስኪ - ቅርሻታቸው… …ለእኩይ - ምግባራቸው፤… እንደ አንድ ሰው ሆነው፣ሲቆሙ በአንድነት ለክቡር አላማ፣ ሌላው ሲሆን “ኩበት’’፤ እነሱ ምን ያ’ርጉት?... ምንስ ያቅርቡለት…? ሰው ነኝ የሚል ዜጋ፣ ከተነዳ እንደ ከብት። ሀገርን አፍርሰው፣ ትውልደን አጥፈተው እንድ ቅርጫ ስጋ፣ ህዝብንም … [Read more...] about ማነው ተጠያቂው?









