ያለስም፣ ስም - ስጡኝ ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤ አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣ ... በማጎሪያችሁ እሰሩት… እጀን፣ … በካቴናችሁ ‘ጠንዙት’ እግሬን፣ …. በእግር ብረታችሁ ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ ... ይደንዝዝላችሁ ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’:: ... እንካችሁ …. ጀርባዬን መጫሚያ፣ መዳፌን፤ ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ ገመድ የሰራ አከላቴ፣ ይክሰል፣ ይሁን ዓመድ:: … ዝረፉት … ሀብቴን ቤትና ንብረቴን፣ በምድር ያለኝን፤ ሰብስቡ፣ አከማቹት፣ ለዓለም ይሁናችሁ ለማይጠረቃው፣ ለከርስ ዓላማችሁ ለማፍረስ፣ ለመናድ፣ ለጥፋት ግባችሁ:: … እንካችሁ…… ደረቴን እንካችሁ…… ግ’ባሬን፤ ለታንክ፣ ለመትረጊስ፣ ለጥይታችሁ አፍስሱት ደሜን፣……. እስኪከረፋችሁ አድቅቁት አጥንቴን፣……. … [Read more...] about እኔ አማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….
Literature
ጽፈኪን
የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በቅርቡ ያረፉት ዶ/ር መሠረት ቸኮል ላለፉት 8 ዓመታት ሲለፉባት የነበረውና የኢትዮጵያን የ100 የፕሬስ ታሪክ የሚያሳይ መጽሐፍ ለገበያ መቅረቡን ቤተሰቦቹ ገለጹ። ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር መሠረት ቸኮል የጻፈው ታሪካዊው መጽሐፍ “The Quest for Press Freedom: One Hundred Years of History of the Media in Ethiopia” የሚሰኝ ሲሆን በamazon.com እንዲሁም በባርነስ ኤንድ ኖብል የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮች እንደሚገኙ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። ይህ መጽሐፍ ለማስተማሪያነት ሁሉ ታስቦ እንደተጻፈ የገለጹት የዶ/ር መሠረት ባለቤት ወ/ሮ በልዩ ወደፊት መጽሐፉን በአማርኛ ለማሳተም እንደተዘጋጁም ገልጸዋል። “ዶ/ር መሠረት ይህን መጽሐፍ በአማርኛም ጀምሮት ነበር። ሆኖም ግን በድንገት ሳጨርሰው በማረፉ … [Read more...] about የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
ትውልድ ያናወጠ ጦርነት
የመጽሐፉ ርእስ.................. ትውልድ ያናወጠ ጦርነት ደራሲ.................................. ንጋቱ ቦጋለ (ሻለቃ) አሳታሚ............................... በግል አታሚ.................................. ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ የሕትመት ሥራ የገጽ ብዛት............................ 341 ዋጋ........................................ 55 ብር ቅኝት..................................... በአበራ ለማ ". . . የሽሬ ውጊያ ብሎም በትግራይ ውስጥ የነበረው የመንግሥት ጦር አመራር በነመጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ችሎታ ማነስ ምክንያት፣ ምን ያህል ተፍገምግሞ እንደወደቀ ደህና አድርገህ ገልጸህዋል፡፡ መጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ጀምለው በያዙት … [Read more...] about ትውልድ ያናወጠ ጦርነት
ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ
ዛሬ ብቻ ኖረው - በዛሬ ያልቀሩ ነገንም አስበው - ለነገ የሠሩ ለራሳቸው ሳይሆን - ለህዝብ የኖሩ ግዴታ ሆነና ሞት - ቢሆን ዕጣቸው ሲበራ ይኖራል - አይጠፋም ሐቃቸው ግጥም - አስራት ዳምጠው በስድስተኛ ዓመቴ መጨረሻ ግድም አንድ ቀይ እንግዳ እቤታችን መጣ። ከናትና አባቴ ጋር ሆኜ ከሰውየው ጋር የመቀመጥ እድል አገኘሁ። ቀዩ ሰውዬ ሳቂታ ፊት፣ የሚቁለጨለጩ አይኖች፣ ሰልካካ አፍንጫና፣ የሞሉ ጉንጮች አሉት።ያም ሆኖ ሙሉ ፊቱ ስትታይ አነስተኛ ነች። ይህን ሰው ከዛን ቀን በፊት ስለማወቄ እርግጠኛ አይደለሁም። እንኳን እሱን ሌሎች አብረውኝ ያሉትንም ዝምድናቸውን ለይቼ ለመናገር እቸገራለሁ። ያን ቀን ያንን ሰው አይነ ህሊናዬን ምን እንዳበራው አላውቅም ቀረብኩት። አንድ አይነት የሚያስተሳስረን ነገር እንዳለን ገባኝ። ነፍስ ማወቅ ይሄ ይሆን? ይሄ ካልሆነ ሌላ ምንም … [Read more...] about ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ
አወይ አማሪካን …
ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... አያልቅ ሽቅቦሹ፥ አይቆም ቆልቁሎሹ መንገድ እየሄዱ መንገድ እየበሉ መንገዱ እየጠጡ አያልቅም ቢሄዱት፥ አያልቅም ቢጠግቡት፤ አወይ አማሪካን... አወይ የሰው አገር የበላን ያላየ፥ የዋጠን ያልሰማ አወይ አማሪካን፥ ሰው በላብ ያደማ፤ ቢሄዱት ቢሄዱት፥ እረፍትን ማን አውቆት እዚማ ከሆኑ… እንቅልፍ ለምኔን፥ ለብሶ ነዪ መኛት፤ አወይ አማሪካን፥ አገረ ማራቶን አገረ እሩጫ ለማምለጥ መፏደድ፥ ቢል ከሚሉ ጡጫ መኖር አለመኖር፥ ካንድ ራስ ፍጥጫ፤ አወይ አማሪካን... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት አያልቅ መንገድ እንደ ጅማት የሚላግበት አወይ አማሪካን ሕልም ያጠጠበት እንቅልፍ ለምኔን የሚያነቡበት_ እንቅልፍ ለምኔን የሚገምጡበት_ እንቅልፍ … [Read more...] about አወይ አማሪካን …
ይላችኋል እስክንድር!!
ይላችኋል እስክንድር !!!! ---------------------------------- “በሚመች ሰፊ አልጋ ላይ ከሚስቶቻችሁ ጎን ብትሆኑም እንደኔ ተመችቷችሁ የሰላም እንቅልፍ አታገኙም” ይላችኋል እስክንድር ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ስትባንኑ ለምትኖሩት በቁም ለሞታችሁት አዝኖ ሰብእናችሁ ተሟጦ አውሬነታችሁ ቢታየውም ተፈጥሮ ሳይሆን ተመክሮ እንደሰጣችሁ አላጣውም ከሽፍታ ፍትሕ መጠበቅ ሞኝነት እንዳይመስላችሁ ለሁሉም ጊዜ ስላለው ለቅሶ ይሆናል ሳቃችሁ እና “እኔ እንደሆንኩ በዕምነቴ እንደፀናሁ በአገሬ እንደኮራሁ … ለዘላለም እኖራለሁ ምግባራችሁ ለቆሸሸው ስማችሁ ለተበላሸው እራሳችሁን ላሳነሳችሁት ግን … እስከወዲያኛው … [Read more...] about ይላችኋል እስክንድር!!
የሙት ምላስ
(ግጥሙ በPDF እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የሙት ምላስ
ቀይ-ሽብር ሲጀምር
ቀይ-ሽብር ሲጀምር ከደርግ ዲሞክራሲ ከወያኔ እኩልነት......ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ ሰብዕናችን ተፍቆ ማንነታችን ተንቆ.....ከዕምነታችን ስንርቅ ውርደታችንን ተመልክተን፤ በቃ ማለት ካቃተን ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን ----------------- ዘመናት አስቆጥራ ብዙ ትውልድ ተሻግራ መቃብር ዛፍ ሲያበቅል፤ የብሶቱ ቀን ሲርቅ የደም አሻራ ሲጠፋ፤ የወላጅ እምባ ሲደርቅ ያኔ ይመስለኝ ነበር ታሪክ እራሷን የምትደግም ሕብረተ-ሰቡ ሲዘናጋ፤ ሰው ከሐዘኑ ሲያገግም ለካ ተሳስቻለሁ! መፃፍ፤ መናገር ሲከለከል: ማሰር፤ ማሳደድ ሲጀመሩ የሐሰት ዶኩሜንታሪ በቴሊቪዥን ሲሠሩ በጋዜጣ ሲያስፈራሩ፤ … [Read more...] about ቀይ-ሽብር ሲጀምር
ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ
እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ ሀገርንና ትውልድን የሚያጠፋ እኩይ አመለካከትና ምግባር ይዞ ተነስቶና ተሳክቶለትም የሚገዛ ከኢትዮጵያ ውጭ በአለም ላይ ያለ ሀገርም ሆነ የሚገዛ ህዝብ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ የገዛ ወገኑንና ሀገሩን በጠላትነት ፈርጆ፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የሚወጋና የሚያፈራርስ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ አገዛዝም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊንን የማጥፋቱንና የመበታተኑን ምግባር እንዲያቆም እሽሩሩ የተባለና እየተለመነ ያለ የለም።..... በልመና ቢሆን..... ፍትህ - እኩልነት በልመና ቢሆን... ነጻነት - አንድነት በልመና ቢሆን.... ሰላምና ሕይወት፤ እመጣ ነበረ- አንች ካለሽበት ትመጭልኝ ነበር - እኔ ካለሁበት ዓለም ይሆን ነበር፣ የሁላችንም ቤት። እንደ ደርግ ያለ አምባገነን መንግስት ሀገሩን በክህደትና በጥላቻ ለተሞሉ፤ እንደ ሻአቢያዊንና እንደ … [Read more...] about ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ
እንደ ሻማ
አንደ ሻማ ነው ማንባት፣ ቀልጦ ጠብ እንደሚለው፤ የነፍሳችንን ስቃይ፣ ይሉኝታ ሳይጋርደው፤ ማስመሰል ሳያርቀው፡፡ እንደ ሻማ ነው መቅለጥ፣ በነበልባል ነዶ በግኖ፤ ሰብእናን በህይወት ጣር፣ ሰርቶ በማደር ፈትኖ፡፡ እንደ ሻማ ነው መብራት፣ ማለቅም እንደ ሻማ፤ ለሌላም ባይሆን ለነፍስ፣ አብርቶ የእውነትን ፋና፡፡ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) ፣ /ፍካት ናፋቂዎች፤1999ዓ.ም/ ባለፈው ሁለት ግጥሞችን አቅርበን ነበር፡፡ “ቅኔ” እና “የማይጠፋ ፍቅር” በሚል ርዕሶች ለቀረቡት ግጥሞች ጨዋታውን በማድመቅ የተቀኛችሁትን እና ማብራሪያም የሰጣችሁትን ተሳታፊዎቻችንን በለው፤ YeKanadaw Kebede፤ አሥረዳው፤ እስከመቼ እና ዱባለ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ ለዛሬው ደግሞ በግጥም ልተንፍሥ ከተባለ የፌስቡክ ገጽ ይህንን ግጥም አግኝተን ለጨዋታ አቅርበነዋል፡፡ “እንደ … [Read more...] about እንደ ሻማ








