አንድነት ይፈጠር - ሀገር ነጻ ትውጣ ንብረትም ይቅርብኝ - ምንም ነገር ልጣ ዳሩ መሀል ሳይሆን - ድንበሩ ተደፍሮ ርቱዕ አንደበት - እንዳይቀር ተቀብሮ ጋዜጠኝነትም - እንዲኖር ተከብሮ ቸነፈር ረሀብ - ሙቀቱን ሳይፈራ ውሎ የከረመ - ከታጋዮች ጋራ ጽናቱ ጠንካራ - ወገኑን የሚወድ ጌትነት የጠላ - ጭቆናን ለመናድ ነጻነት ናፋቂ - በደል የመረረው ውነተኛ ታጋይ - ቆራጥ ጀግና ማነው? … [Read more...] about ቆራጥ ጀግና ማነው?
Literature
ጽፈኪን
እኛ ያምላክ ጥጆች!!!
ስንኖር በዚህ አለም • • • ቆመን ለመራመድ፣ ጫናውን ለመቻል • • • ግፊያውን ለመልመድ፣ አቀበት ለመውጣ • • • ቁልቁለት ለመውረድ፣ ጠንክሮ መጓዝ ነው • • • የለም መንገዳገድ። እኛ ያምላክ ልጆች ~ ባምሳሉ የሰራን፣ እንደ ምድር አሸዋ ~ ምድርን የሞላን፣ ፈጣሪ ሲፈጥር ~ ከአፈር ሲሰራን፣ "ብዙ ተባዙ" እንጂ ~ መች ተጋፉ አለን? እንደ ቃሉም ሆነ = እልፍ አእላፍ ሆንን፣ ላይ በላይ ተዋለድን = እንደ አሸን ፈላን፣ ምድር ተጥለቀለቀ = አለምንም ሞላን፣ መሬት ተጣበበች = ቦታ አልበቃ አለን፣ አንዱ ባንዱ አሴረ = እርስ በርስ ተጋፋን፣ መንገድ ለማስለቀቅ = ጥሎ ማለፍ ጀመርን። ባምሳሉ የፈጠረን • • • እኛ ያምላክ ልጆች፣ ሰብእናው ጎሎን • • • ሆነን እንደ ጥጆች፣ ግጦሹን ለማግኘት • • • ሳሩን ለማሻመድ፣ ደካማውን ጥለን • • … [Read more...] about እኛ ያምላክ ጥጆች!!!
አድዋ ለኔ!
እውነት አድዋ ለኔ ምኔ ነው? ላንተ፣ ላንቺ ለርስዎስ ትርጉም አለው? ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ አንዱ ዓለም ተፈራ እስከመቼ፤ ረቡዕ፤ የካቲት ፲፰ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት ሳኒቬል፤ ካሊፎርኒያ ( Wednesday, 2/25/2015 ) … [Read more...] about አድዋ ለኔ!
ዝክረ አድዋ!!
ልክ የዛሬ 119 ዓመት እብሪተኛውን ጣልያን አድዋ ላይ ገጥሞ አይቀጡ ቅጣት የቀጣው የኢትዮጵያ ጦር በእምዮ ምኒሊክ ፊታውራሪነት በድል ተመልሶ አዲስ አበባ ሲገባ ህዝቡ በታላቅ እልልታና ጭፈራ ተቀበላቸው፤ ወዲያውም ግዳይ ሲጣልና ሲፎከር ለጀግኖቹ ክብር የሚከተለው ተገጠመለታቸው፡- ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ *************** ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡ በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡ ምኒሊክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡ አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል የጎጃሙ ንጉስ ግፋ በለው ሲል እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን ዳዊቱዋን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል፡፡ ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ … [Read more...] about ዝክረ አድዋ!!
አድዋ!
ዋ! አድዋ ፤ ያ ሑዳዴ መድፍና ፈንጅ ፤ በጎራዴ ባሕር ተሻግሮ ፤ የሐበሻን ምድር ቅኝ ሊገዛ ፤ የማን ደፋር! አንች አድዋ ፤ የበኩር ልጅ ላንቺ ውልደት ፤ ስንቱ ሲፈጅ ተጸንሰሽ ፤ ከውጫሌ ለደም መሬት ፤ ለአሞሌ እርግዝናሽ ፤ ዘጠኝ ወሩ ዓመታትን ፤ ማስቆጠሩ ክፉውን ቀን ፤ ይዞ አሳሩ ከብቱ እረግፎ ፤ ባገር ምድሩ ሰው ሁሉ አልቆ ፤ በችጋሩ በፋሽስት ሸር ፤ በእኩይ ግብሩ ከብት የሚፈጅ ፤ ደዌ ረጭቶ በምን ታርሶ ፣ በምን ለምቶ የገበሬው ፤ ሀብት ጠፍቶ አከርካሪው ፤ ተመትቶ የሚቀመስ ፤ እህል ታጥቶ ረሀቡ ፤ ሕዝቡን በልቶ ምኑ ተብሎ ፤ ስንቱን ነግሮ የግፍ ግፉ ፤ ተዘርዝሮ ዝም ይሻላል ፤ ምን ተቆጥሮ በክፉው ቀን ፤ ራብ ደክሞ ያለቀ ሕዝብ ፤ በአዋጅ ተሞ በዚያ … [Read more...] about አድዋ!
ዘጸአት ለኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ምድር፥ ምኒልክን (ዮሴፍን) 'ማያውቅ፥ አዲስ ንጉሥ መ'ቶ፣ "ለነፃነት" ብሎ፥ የነፃነትን ጧፍ፥ ረጋግጦ አጥፍቶ፣ "ከኔ ወዲያ ላሳር!"፥ አለን አፉን ሞልቶ፣ ያ'ባቶችን ክብር፥ አፈር መሬት ከ'ቶ። ያገሬ ፈርዖን፥ ልቡ እጅግ ደንድኖ፣ የፈጣሪን ፈቃድ፥ እንዳይሰማ ሆኖ፣ "እንደ'ኔ ያለ ንጉሥ!"፥ እያለ ይጽናናል፣ የበትሩን ምሬት፥ በጠገበ ጉልበት፥ ከተማን ያጸናል። ስንት አሮን ተላከ? ስንት ሙሴ መጣ? "የሠራዊት ጌታ፥ 'ህዝቤን ልቀቅ' ይላል!"፥ የሚል ቃል ሊያወጣ፣ ስንት ምርጫ ሆነ፥ ስንት ምርጫ ሄደ፣ ደንዳናው ፈርዖን፥ በህዝብና ፍትህ፥ እንደተጓደደ። ምልክቶች ታዩ፥ ታምራትም መጡ፣ ፈተናው ጸና እንጂ፥ የእብሪተኞችን ልብ፥ ቅንጣት አ'ለወጡ። የባሰው መጣና፥ የ'እብራውያን' በኩር፥ እየተሰደደ፣ መልአከ ሞት ጥላ ፥ 'የፈርኦንን በኩር'፥ … [Read more...] about ዘጸአት ለኢትዮጵያ
“ፍቅር እስከ መቃብር” በሰሜን ዋልታ
ዶክተር ሬዶልፍ ክኑት ሞልቨር (Reidulf Knut Molvær) የ77 ዓመት ኖርዌጂያዊ አዛውንት ናቸው። ዋና ሙያቸው የሥነ ጥሑፍ፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪነት ነው። በአማርኛ ሥነ ጽሁፍና ቋንቋ ጥናት ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ያገኙ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 14 ኬንያ ውስጥ ደግሞ 6 ዓመታትን ባለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በመሥራት አሳልፈዋል። የትዳር ጓደኛቸው ኬንያዊት ሲሆኑ፣ አራት ልጆችም በጋራ አፍርተዋል። ከልጆቻቸውም መካከል አንዱ የሕክምና ዶክተር፣ ሁለቱ ኢንጂነሮች ሆነዋል። ዶ/ር ሞልቨር ለፍልስፍና ማስትሬት ድግሪያቸው መመረቂያ አዘጋጅተውት የነበረው ጥናታቸው ቀዳሚውን እውቅና አስገኝቶላቸው የነበረ ነው። ይህን ጥናታቸውን “ልማድና ለውጥ በኢትዮጵያ - Tradition and Change in Ethiopia: Social and … [Read more...] about “ፍቅር እስከ መቃብር” በሰሜን ዋልታ
የደቡብ አፍሪካዊያን ዕዳ!
የማንዴላ ልጆች ወገኖቹ ፤ የዋልንላቸው ውለታ ይህች አፍሪካ በነጻነት ፤ እንድታገኝ እፎይታ ጥረታችን ሁሉ ሰምሮ ፤ አገኙና ነጻነት በእኛ ቀን ሲዘነብል ፤ ብንሔድባቸው ስደት ከቅኝ ግዛት እስከ አፓርታይድ ፤ የረገጣቸው እያለ ወንድም ጓዱን ሐበሻ ፤ ስለ እሱ ዋጋ የከፈለ ከሀገር ይውጣ ብሎ ጮኸ ፤ ጎዳናው ላይ እያቃጠለ፡፡ ምን ነው ወገኔ ምን ነው? ፤ አእምሮም የለህ ማሰቢያ? ምን እንደሆነች አታውቅም? ፤ ውዷ የኔ ሀገር ኢትዮጵያ? በከፈልንላቹህ ዋጋ ፤ በእናንተ የተነሣ እንዲህ ሆና እንደቀረች ፤ በነጫጭ ጅቦች ተነክሳ? ታወክን ታመስን እንጅ ፤ በነጭ ሰይጣናት እከይ ወደ እናንተ የተመምነው ፤ መች አጥተን ነበር ሲሳይ ስለእናንተ ባደረግነው ፤ ከዲፕሎማሲው ማሳደም መሪዎችህን አሠልጥኖ ፤ በግንባር እስከ … [Read more...] about የደቡብ አፍሪካዊያን ዕዳ!
አብዮት መንታ ነው
"የአብዮት ያለህ!"፥ አትበሉ ባ'ገሬ፣ በአብዮት መሃል፥ አብዮት አይጠሬ፣ ምስጋና ቢስ ትውልድ፥ ሆነነው ነው እንጂ፣ የግፈኛን ቀብር፥ የምናበጃጅ፣ የሚሞቱልንን፥ የደም ዋጋ ንቀን፣ በአብዮት መሃል፥ ካ'ብዮት ርቀን፣ በአርበኞች መሃል፥ ባ'ርበኝነት ስቀን... "ደሃ ህዝብ አስፈጁ"፥ ስንል ተሰምተናል፣ "አመሉ ሲታወቅ"፥ ብለን አድንቀናል፣ 'ያስፈጀው' ሲወገዝ፥ ፈጂውን ትተናል፣ አህያ እየፈራን፥ ዳውላ መ'ተናል። ልንገርህ ወገኔ፥ አብዮት ሁለት ነው፥ መንታ ነው ፍጥረቱ፣ እርግጥም አብዮት፥ ስም ያገኘበቱ፣ በዳዮችን ሲጥል፥ ስርአት ሲዘረጋ፣ ሙሉ ሥም ያገኛል፥ አቢዮት እዚህጋ። ነገር ግን ሲመታ፥ በበዳይ ፍላጻ፣ አቢዮት ተሽሮ፥ ይባላል አመጻ። "አብዮት የለም" አንበል፥ አብዮት አለን እኛ፣ ግዞት ቤቱ የሞላው፥ በአብዮተኛ። “There are … [Read more...] about አብዮት መንታ ነው
የካድሬ ብቻ
ኑሮ ተወደደ፣ ምሁር ከአገር ጠፋ እየተሰደደ፣ እውነትን የፃፈ ለሃቅ የቆመ ዘብጥያ ወረደ፣ በአገሬ ምድር ላይ ቁጥሩ የጨመረ ዋጋዉ የረከሰ፣ የካድሬ ብቻ ነው ሕዝብ እያስለቀሰ *ኢዮብ ብርሃነ … [Read more...] about የካድሬ ብቻ










