• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የደቡብ አፍሪካዊያን ዕዳ!

January 30, 2015 04:01 am by Editor Leave a Comment

የማንዴላ ልጆች ወገኖቹ ፤ የዋልንላቸው ውለታ

ይህች አፍሪካ በነጻነት ፤ እንድታገኝ እፎይታ

ጥረታችን ሁሉ ሰምሮ ፤ አገኙና ነጻነት

በእኛ ቀን ሲዘነብል ፤ ብንሔድባቸው ስደት

ከቅኝ ግዛት እስከ አፓርታይድ ፤ የረገጣቸው እያለ

ወንድም ጓዱን ሐበሻ ፤ ስለ እሱ ዋጋ የከፈለ

ከሀገር ይውጣ ብሎ ጮኸ ፤ ጎዳናው ላይ እያቃጠለ፡፡

ምን ነው ወገኔ ምን ነው? ፤ አእምሮም የለህ ማሰቢያ?

ምን እንደሆነች አታውቅም? ፤ ውዷ የኔ ሀገር ኢትዮጵያ?

በከፈልንላቹህ ዋጋ ፤ በእናንተ የተነሣ

እንዲህ ሆና እንደቀረች ፤ በነጫጭ ጅቦች ተነክሳ?

ታወክን ታመስን እንጅ ፤ በነጭ ሰይጣናት እከይ

ወደ እናንተ የተመምነው ፤ መች አጥተን ነበር ሲሳይ

ስለእናንተ ባደረግነው ፤ ከዲፕሎማሲው ማሳደም

መሪዎችህን አሠልጥኖ ፤ በግንባር እስከ ማፋለም

በእኛ ጥረት ነበርና ፤ ነጻነትህ የተገኘ

ጥርስ ነከሱ በእኛ ላይ ፤ ልባቸው በቀል ተቃኘ

እርስ በርሳችን ብንባላ ፤ እንድንሆን ከንቱ መና

ያለእነሱ ማንም የለም ፤ የሴራው ምንጭ ሲጠና

ላንተ ስንል በከፈልነው ፤ ለዚህ ብንበቃ ብናጣ

ማስጠጋት ሲገባህ በክብር ፤ የጠላትህን ባላንጣ

የክፉ ቀንህን አጋር ፤ የተሰጠህን ዕጣ

እሳት በላዩ እየለቀክ ፤ ማባረሩ ነው የሱ ዋጋ?

ከቶ በምን ሒሳብ ነው? ፤ ሕሊናም የለ አንተ ጋ?

ፍዳ ያስቆጠረህ ባዕዱ ፤ እየኖረ ተንቀባሮ

ላንተም ኢምንት ያልከፈለው ፤ መጥቶ ከህንድ ተሸግሮ

በምቾት ድሎት እየኖረ ፤ ሞጃ ሆኖ ገኖ ከብሮ

በገዛ የራስ ሀገርህ ፤ አንተን ባዶ አርጎ ገፍትሮ

የገዛ ሀገርክን ከተማ ፤ እያስቋመጠህ አማልሎ

ነጻነትህ ትርጉም አጥቶ ፤ ገብተህ ለመርገጥ ከልክሎ

ይሄ ሳያምህ ሳይቆጭህ ፤ ወኔህ ተሰልቦ ተገሎ

ሀሞትህ ፈሶ ፈራርሶ ፤ ጉልበትህ ከድቶህ ሰልሎ

ይሄንን የሚያህል ውርደት ፤ ተሸክመኸው እያለ

በዚህ ዘመን አሁን ዛሬ ፤ ነጻ ነኝ እያልክ ታደለ

ምስኪኑ ደሀው ወንድምህ ፤ ምን አረገ? ምን በደለ?

ያንተን ቀንበር ተሸክሞ ፤ በሞተልህ በቆሰለ?

ሀገሬን ካልክ መብቴን ፤ የራሴን ሀብት እንጀራ

የወሰደብህ እያለ ፤ ድልቡን ዋናውን ጎተራ

ፍርፋሪውን ለቃሚው ፤ ወንድም ሐበሻው ምን ሠራ?

እንዴት ነው እሱ ነገሩ ፤ የባሕል ወጋቹህ ዕይታ?

ተገላቢጦሽ ነው እንዴ? ፤ ለወዳጅ ክፉን መልሶ

ዘርፎ እራቁቱን ማስቀረት ፤ ካገር ማባረር አስለቅሶ?

ገድሎ መንገድ ላይ መጎተት? ፤ መልካም ምግባሩን አርክሶ?

መልካሙን ለጠላት በማቅረብ ፤ ባርነትን መኖር መልሶ?

ይሄነው ባሕላ ወጋቹህ? ፤ የማሰብ ልካቹህ ተሐድሶ?

እኛ እኮ እንደዚያ የደከምን ፤ ከዲፕሎማሲም ኃይል እርዳታ

እንድትኖሩ አልነበረም ፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ

ወይ ከዳር ደርሶ አላየን ፤ የነጻነቱን ፍልሚያ

ድካማችንን ከንቱ አረገው ፤ ዛሬ ያለብህ ግሊያ

እንዲህ በአድሎ እየኖርክ ፤ ከማዶ ከኬላ ወዲያ

አፓርታይድ የለም ትላለህ? ፤ በዚህ አናፍርም ታዲያ?

ዕያየነው በመሆኑ ፤ ዛሬም ሆናቹህ ባሪያ::

ወገኔ ማጥፋት ማስወገድ ፤ ድል ማድረግ ያለብህ እኮ!

ይሄንን ውርደትህን ነው ፤ ያስቀረህን አንበርክኮ

ሀገርህን ማስመለስ ነው ፤ ከተወሰደብህ ምርኮ፡፡

የኔስ ግምት የነበረው ፤ ወገኔ ሆኖ ስደተኛ

ወዳገርህ ስጎርፍ ሲተም ፤ ሆኖ ሊኖር ጥገኛ

ያለውን ህልም ያውቃሉና ፤ ዓላማ ምኞቱን ለአንተ

የፈራሁ ነጮቹን ነበር ፤ ግምት ሥጋቴ ሳተ

ጭራሽማ እዚህ ገብቶ ፤ አብሮ ሆኖ እየኖረ

በምክር እያነሣሣ ፤ ገፋፍቶ እያዳፈረ

መፈጸሙ አይቀር ብለው ፤ የቀረውን የቤት ሥራ

ያነቃብናል ዋ! ኋላ ፤ መንገድ ጠቁሞ እየመራ

አይሆንም ሐበሻ ይውጣ ፤ ብየ እንዳያሴሩ ሴራ

እንጅ አንተንማ እንደምን? ፤ እኮ እንዴት ብየ ጠርጥሬ?

ወንድም ነው ዕዳም አለበት ፤ ባልኩት እንዳይን አሳሬ?

ግን ምንም ያለህ አልነበረም  ፤ እሱ አባትህ ማንዴላ

ዕዳ አለብን አላለህም? ፤ ያንን ዕዳ እንዳትበላ?

ወይስ ነው ችግሩ ያንተ? ፤ ቃሉን ያልሰማህ አደራ

ማዲባዬ እያልክ አባቴ ፤ የነጻነት ታጋይ አውራ

ኧረ ተው አባትህን ስማ ፤ ሰምተናል ብዙ እንዳለ

ጠብቅ እንጅ ቃል አደራን ፤ ምን ነው? በማን ተማለ?

ይሄንን ቃል ባትሰማ ፤ በሰማይ ባንተ ፍርድ አለ!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ጥር 19 2007ዓ.ም.

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Literature

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule