አቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ጽሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ፡፡ መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና አቶ አንዱዓለም መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው ያቀረቡት ምክንያት በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ጻፍሁ፡፡ ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይናገሩም የሚችሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ስንል ወያኔ ትናንትም የታገለው ዛሬም ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሰራው እነዚህን ነጻ ለማውጣት ነው፣ እነርሱም ነጻ አውጪነቱን አውቀውና አምነው የተቀበሉት ነው ወደሚል አንደምታ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ … [Read more...] about ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
Opinions
የኔ ሃሳብ
የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”
* የጅዳ ቆንስል ለባላቴናው መሀመድ ፍትህ ይትጋ * የጅዳ ቆንስል የስደት ያሰናከለውን ወንድም ይሸኝ * "ጅቦቹ!" የአንባሳደሩን ተሀድሶ ያኮላሹት ይሆን? የማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ ከወራት በፊት ለኦማኗ ተገፊ ለአልማዝ እና ሰሞኑን እርዳታ ስናሰባሰብለት ለሰነበትነው ወንድም ወጣት አባወራ ለመሀመድ ስላደረጋችሁለት ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ ነው። በላዩ ላይ የአልማዝ እርዳታ ሀገር ቤት በእንክብካቤ ለያዛት ለሜቅዶንያ የማስረከባችን መረጃ አካፍየ በሳምንት እድሜ ለመሀመድ ሁሴን ከ10 ሽህ የሳውዲ ሪያል ወይም ወደ 60 ሽህ የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ገንዘብ በላይ ማሰባሰቤን መረጃ ከማቅረቡ ጋር ምስጋናየን ለማስተላለፍ ነበር። ለዚህ መረጃ አቅርቦት ስሰነዳዳ በተዛማጅ ስለ ዜጎች መብት ጥሰትና ስለመብት ማስከበሩ ጭብጥ አስተምሮት እናገኝ ዘንድ አንድ መረጃ አገኘሁ። ምስጋናየን ወደ … [Read more...] about የጅዳ ቆንስላው ግቢ “ጅቦች”
የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው
በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረትና ለሚቀረጹ ፖሊሲዎች ጥራት ወሳኝ ነው። እንግዲህ በሃገራችን ኢትዮጵያ ግምገማ በሰፊው የተወራለት ጉዳይ የሆነው በዚህ መንግስት ጊዜ ነው። ህወሃት በጫካ ኑሮው ጊዜ የነበረው ማህበራዊ ህይወትና የትግሉም ባህርይ የየቀን ውሎውን እየገመገመ እንዲሄድ የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ስለከተተው በግለሰቦች ድክመትና … [Read more...] about የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው
የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው
የአንድ ለነፃነት የሚታገል ኃይል የመጀመሪያ ተግባሩ፣ ጠንካራ ምሽግ መገንባት ነው። ምሽግ ሲባልም መሬትን ጎርዶ ራስን መቅበር፣ ወይም ደግሞ በኮንክሪት መከታ እና ጠለላ ገንብቶ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወነጨፉ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አረሮችን መከላከል አይደለም። ጠንካራ ምሽግ ሲባል፣ ታጋዩ ኃይል ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ዓላማውን አሳውቆ፣ አሳምኖ እና አደራጅቶ የታጋዩ ኃይል የቀለብ፣ የመረጃ እና የሰው ኃይል ምንጭ ማድረግ መቻል ነው። በአጭሩ ሕዝቡን ባሕር፣ ታጋዩን ዓሣ ማድረግ መቻል «ለነፃነት እታገላለሁ» የሚል ኃይል የአደረጃጀት ስልት ሊሆን ይገባል። ይህን ያላደረገ ታጋይ ሌሎችን ነፃ ሊያወጣ ቀርቶ፣ ራሱም ነፃ አይሆንም። ራሱን ነፃ ያላወጣ ደግሞ፣ ብዙኃኑን ወደ ነፃነት ጎዳና ሊመራ አይቻለውም። ለነፃነት የሚታገሉ ኃይሎች ደረጃ በደረጃ ሊያሟሏቸው የሚገቧቸው ሁኔታዎች … [Read more...] about የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው
አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ
"የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል" አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡ በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ … [Read more...] about አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ
“አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም”
የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በጁን 23/ 2015 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። በሰልፉ ላይ ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የተገኙ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከ13፡30 ስዓት ጀምሮ ታላቋ ብርታኒያ ለዜጋዋ አቶ አንዳርጋቸው ልዩ ትኩረት አድርጋ ከዘረኛው ወያኔ ነጻ በማውጣት ወደ ቤተሰቡ እንዲመለስ ለማሳሰብ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የነጻነት ታጋዩን አንዳርጋቸውን በተመለከተ የተለያዩ መፎክሮችን … [Read more...] about “አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም”
ከገዥው ወገን የምንለይበት
እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና እቆማለሁ፤ የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት፤ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይልቅ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የበለጠ የጋራ የሆኑ መቀራረቢያ ጉዳዮች ስላሉት፤ ሰፈሩን ወደዚያ ቢያቀና ይቀለዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር መሠረታዊ … [Read more...] about ከገዥው ወገን የምንለይበት
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሄት
“ትግሌን አደራ” ነፃነቱን የተቀማ ሕዝብ ለድል የሚያበቃው ጠንካራ ድርጅት ይፈልጋል ምርጫና የሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ ምርጫ 2007 ሂደቱም ሆነ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብትና ደህንነት የሚጠብቅ መንግሥት የላትም በመሳሰሉና ሌሎችም ርዕሶች መጽሄቱ ታትሞ ወጥቶዋል - ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሄት
የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ
የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ! «ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔ ምንጮቻችን አረጋገጡ። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት፣ አጥኚዎቹ ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የትግሬ-ወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ያለፉትን የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት ጉዞ መዝነው፣ ለሥልጣኑ አስጊው ማን እንደሆነ በመተንተን፣ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ የትግሬ-ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት ዝርዝር ጥናት አቅርበዋል። በትግሬ-ወያኔ የስለላ ተቋሞች ከፍተኛ አካሎች አማካይነት የተደረገው ይህ ዝርዝር ጥናት፣ … [Read more...] about የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ
በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ
አቶ ፈቃደ ሸዋቀና የስደትን ነገር መነሻ አድርገው ስለ ብሔራዊ እርቅ የሰነዘሩት ሀሳብ ካለፈው የባሰ ጨለማ የሆነው የሀገራችን መጻኢ እድል አሳስቦ አስጨንቆአቸው ያቀረቡት በጎ ሀሳብ እንደመሆኑ አንብበን የምንተወው ወይንም ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ብለን ልናናንቀው የሚገባ አይደለም፡፡ ርሳቸውም አንዳሉት ሁሉም የየበኩሉን ይበጃል የሚለውን ሀሳብ በመሰንዘር በመተላለቅ ሳይሆን በመታረቅ የምናተርፈበትንና ሀገራችንንም አድነን ለመጪው ትውልድ ልጆቿ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማቆየት ወደሚያስችለን እቅጣጫ ብናመራ ነው የሚበጀው፡፡ በዚህ መንፈስ እኔም እንዲህ ቢሆን እላለሁ፡፡ ወያኔ ስልጣኑን ለብቻው ካደረገ ግዜ ጀምሮ በተለያየ መንገድ የብሔራዊ እርቅ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የሀሳቡ አቀንቃኞች በሁለት ወገን መወገዛቸውን እናስታወሳለን፡፡ ወያኔ የደርግ ሥርዓት ወንጀለኞችን … [Read more...] about በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ









