• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ

June 20, 2015 08:28 pm by Editor 2 Comments

  • የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ!

«ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔ ምንጮቻችን አረጋገጡ። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት፣ አጥኚዎቹ ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የትግሬ-ወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ያለፉትን የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት ጉዞ መዝነው፣ ለሥልጣኑ አስጊው ማን እንደሆነ በመተንተን፣ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ የትግሬ-ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት ዝርዝር ጥናት አቅርበዋል።

በትግሬ-ወያኔ የስለላ ተቋሞች ከፍተኛ አካሎች አማካይነት የተደረገው ይህ ዝርዝር ጥናት፣ «የመፍትሔ ኃሣብ ነው» ያለውን ለሕወሓት ፖሊት ቢሮ ማቅረቡን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በስለላ ቡድኖቹ አንኳር የጥናት ውጤት መሠረት ወያኔ ገና «ሀ» ብሎ የትጥቅ ትግል ሲጀምር ከኢምፔሪያዝም በላይ እና በፊት «ዐማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው» ብሎ መፈረጁ ትክክል እንዳልነበር፣ የትግሬ-ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላም ቀደም ሲል የፈጸመውን ስሕተት በማረም እና በማስተካከል ፋንታ በያዘው የቆየ የተሳሳተ ፍረጃ ገፍቶ በዐማራው ላይ ያደረሰው ጥፋት፣ እኒህ ሁሉ ተደማምረው ዐማራው «ትግሬ ጠላቴ ነው» ብሎ እንዲያስብ እና በነገዱ ዙሪያ እንዲሰባሰብ እንዳስገደደ ያመለክታል። ይህም ለተተኪው የትግራይ ትውልድ ቋሚ ጠላት የገዛ መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ከሻዕቢያ ጋር የተገባው መቋጫ ያልተገኘለት ጦርነት የትግራይን ሕዝብ ከሥጋ ዘመዱ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም ያቃባ እና ቋሚ የደም ጠላት የገዛለት መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ ከላይ በኤርትራውያን፣ ከታች እና ከመሐል ደግሞ በዐማራው መካከል ሣንዲዊች ተደርጎ እንዲያዝ ያደረገ በመሆኑ፣ የወያኔ የ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት የሥልጣን ጉዞ ለመጭው የትግራይ ትውልድ ደም የገዛለት፣ የሥጋት ምንጮችን ያራባበት እንደሆነ የስለላ ቡድኖቹ የጥናት ውጤት አረጋግጧል።

የስለላ ቡድኖቹ ጥናት ለወደፊት የትግሬ-ወያኔ እንዴት በሥልጣን ላይ መቀጠል እንደሚችል የሚከተለውን ምክር መስጠቱ ታውቋል። ለጊዜው ወያኔ በሥልጣን ላይ በመሆኑ፣ ችግሩን ማስተዋል ቢሣነውም፣ የትግራይ ትውልድ በመጭዎቹ ዘመናት የሚታወቀው በሀገር ከሃዲነት፣ በኢትዮጵያ አፍራሽነት፣ ኢትዮጵያውያንን በጎሣ አቧድኖ በማጫረስ እና አገሪቱን ዝግ መሬት በማድረጉ እንደሚሆን ጥናቱ ያወሣል። ለወደፊቱም ወያኔ እንዴት መቀጠል እንዳለበት የሰጠው የመፍትሔ ኃሣብ፥ የተፈጸመውን ጥፋት በምንም መልኩ ወደኋላ ተመልሶ ማስተካከል ስለማይቻል፣ ማድረግ ያለበት በዝምታ ወደፊት መቀጠል መሆኑን፣ በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ነገዶች ትግሬን የሚያሰጋው ሌላ ማንም ሳይሆን፣ ዐማራው መሆኑን፣ እና ይህ ነገድ በምንም ተዓምር የመደራጀት ዕድል እንዳያገኝ ወያኔ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባል። ለዚህም ግብ ተግባራዊነት የተነደፉ ስልቶች፦

ሀ) ዐማራዎች ከሁለት በላይ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ የተጠናከረ የስለላ እና የክትትል መረብ እንዲዘረጋ ማድረግ፤

ለ) ወደውጪ አገር ለመሰደድ የሚፈልገውን ዐማራ በተለያዩ ስልቶች እንዲሰደድ ሁኔታዎችን በስውር በማመቻቸት ማሰደድ፤

ሐ) በአገር ቤት ያለውን እና ለመሰደድ ፈቃደኛ ያልሆነውን ደግሞ አንገቱን ሳያቀና በልዩ ልዩ መንገዶች ማስወገድ፤

መ) አንገታቸውን ያቀኑትን በተቀነባበረ መንገድ በሐሰት በመክሰስ በፍርድ ቤት የረጅም ጊዜ እስር በማስፈረድ ዕድሜያቸውን በእስር እንዲጨርሱ እና ተከታዮቻቸው ሞራላቸው እንዲላሽቅ ማድረግ፤

ሠ) ድኃ ከዕለት ምግቡ በቀር ሌላ ነገር ማሰብ ስለማይችል፣ ዐማራውን በድኅነት ማጥ ውስጥ የሚከቱ ስልቶችን በመንደፍ ከሆዱ አልፎ ሌላ ነገር አንጋጦ እንዳያይ ማድረግ፤

ረ) ዐማራው በብዛት ተከማችቶ የሚገኝባቸውን ከተሞች እና መንደሮች በልዩ ልዩ የግንባታ ስበቦች በማፍረስ የዐማራውን የአብሮነት እና ማኅበራዊ ትሥሥር መበጣጠስ፤

ሰ) ሌሎች ነገዶች፣ በተለይ ኦሮሞዎቹ፣ ከዐማራው ጋር ምንም ዓይነት ቀና ግንኙነት እንዳይኖራቸው በሁለቱ ነገዶች መካከል ልዩነቶችን የሚያሰፉ የፕሮፓጋንዳ ሥልቶችን ቀይሶ መንቀሳቀስ፣ የሚሉ ይገኙበታል።

ለእነዚህም ስልቶች ተግባራዊነት፦

ሀ) እያንዳንዱ ትግሬ በስለላ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ፣

ለ) የትግራይ ሕዝብ የትግሉ መሠረት እንደመሆኑ መጠን ከአሁኑ በተሻለ መንገድ የሁሉም ነገሮች ተጠቃሚ በማድረግ በሙሉ ኃይሉ ከሕወሓት ጎን እንዲሰለፍ ማድረግ፤

ሐ) ሕወሓት በሥልጣን ላይ ከሌለ የትግሬ ነገድ ዛሬ የጨበጠው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት የማይቀጥል ከመሆኑም በላይ በወያኔ ተባባሪነት ተጠያቂ የሚሆነው ሕዝብ ጥቂት እንደማይሆን አውቆ ለሕወሓት ኅልውና የተለመደውን ትብብር ማድረግ እንዳለበት ያላሰለሰ ትምህርትና ቅስቀሳ መስጠት የማይታለፉ ተግባሮች መሆናቸውን የጥናት ቡድኑ መክሯል።

በቅርብ ሣምንታት ይህ አዲሱ የትግሬ-ወያኔ ዕቅድ በተግባር መተርጎም መጀመሩን የሚያመለክቱ ድርጊቶች ተበራክተዋል። ለአብነት ያህል ከሦሥት ቀናት በፊት ሰኔ ፰ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሣሙኤል አወቀ የተባለውን እና ሰማያዊ ፓርቲን ወክሎ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለፓርላማ አባልነት የተወዳደረውን የ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ዓመት ወጣት በአሠቃቂ ሁኔታ ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ የገደሉት አንድ ምሣሌ ነው። ቀደም ብሎም በሚያዝያ እና በግንቦት ወራት አያሌ የዐማራ ተወላጆች ለግድያ፣ ለእሥር እና ለእንግልት መዳረጋቸው የአደባባይ ሚሥጢር ነው።

የትግሬ-ወያኔዎች እንዲህ ያስባሉ፣ ኃሣባቸውንም በተግባር ይተረጉማሉ። ዐማራውስ ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ምን ያስባል? መጥፋት ወይስ መክቶ ጥፋትን መከላከል? እንደሞረሽ ወገኔ አቋም «ጅብ ከሚበላህ፣ በልተኸው ተቀደስ» ነውና፤ ይህ አገርን እና ትውልድን አጥፊ የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ ቡድን አጥፍቶን ከመጥፋቱ በፊት እንቅስቃሴውን የሚያመክን የተግባር እርምጃ ይጠይቃል። ለዚህም ዐማራው ተደራጅቶ ራሱን እና አገሩን ከፈጽሞ ጥፋት ሊታደግ ይገባል ብለን እናምናለን። ይህ ጉዳይ «ቆይ እንመካከር፣ እንወያይ» የሚባልበት አይደለም። አፋጣኝ የተግባር እርምጃ ይጠይቃል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

mwaoipr@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. rasdejen says

    June 25, 2015 12:21 pm at 12:21 pm

    TPLF is committing all the crimes against Ethiopia/Ethiopians supported by America, UK, EU and their subsidiers.

    3 days ago I wrote this to these intruders:

    Letter to the whitehouse, World bank, IMF, UN, etc: http://www.ethiomedia.com/102shows/5081.html
    It is clear for humans as well as for the inhumans. Isn’t it? Needless to tell you but
    Ethiopians’ sufferage is due to the USA-lead globalisation scheme rather the neocolonialism scramble. Everyone dies any way, but as usual Ethiopians shall endure all forms of inhumanities and liberate humanity including the (“disguised”) inhumans!

    Reply
  2. tewodros says

    July 2, 2015 01:12 am at 1:12 am

    what do u something , ለምን የተሻለ መረብ ፈጥራችሁ ወጣቱን እንዲገናኝ አታደርጉም!!”

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule