• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት

July 3, 2015 03:33 am by Editor Leave a Comment

አቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ጽሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ፡፡ መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና አቶ አንዱዓለም መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው ያቀረቡት ምክንያት   በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ጻፍሁ፡፡

ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይናገሩም የሚችሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ስንል ወያኔ ትናንትም የታገለው ዛሬም ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሰራው እነዚህን ነጻ ለማውጣት ነው፣ እነርሱም ነጻ አውጪነቱን አውቀውና አምነው የተቀበሉት ነው ወደሚል አንደምታ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ ወያኔ የሚፈልገው ነው፡፡

እሱ የሚለውን ተቀብሎ ትግሬና ወያኔን አንድ አድርጎ የመመልከቱ አደገኛነት የታያቸው ኢትዮጵያውያን ገና ከጅምሩ ወያኔንና ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ለይቶ ማየት እንደሚገባ፣ ሁለቱን መቀላቀል ትግሉን የሚጎዳና ወያኔን የሚጠቅም ብሎም በወደፊት የኢትዮጵያ አንድነት ላይ መጥፎ ደንቃራ የሚያስቀምጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፣ጽፈዋል፡፡ ይህም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት በማግኘቱ ወያያኔ ባሰበውና በተመኘው መጠን ትግረኛ ተናጋሪውን ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ነጥሎ የርሱ ብቸኛ መከታ ማድረግ አልቻለም፡፡

ወያኔዎች ትናንትም ሆነ ዛሬ አላማ ፍላጎታቸው ስልጣን ነው፡፡ ትግል ሲጀምሩ መላ ኢትዮጵያን መያዝ አንችልም ብለው ስላመኑ ትግራይን ይዘው የሥልጣን ፍልጎታቸውን ለማርካት ስማቸውን ተሀህት፣ማገብት ህውሀት እያሉ ለትግረኛ ተናጋሪው ወገን የሚታገሉ መስለው ተጓዙ እንጂ ከራስ ጥቅም ያለፈ አላማም አጀንዳም ያላቸው አይደሉም፡፡ ይህን ደግሞ በሀያ አራት አመታት አገዛዛቸው በሚገባ የተገነዘብን ይመስለኛል፡፡ በዓላማም በግብርም የማይመስሉትን የቀዳማይ ወያኔን ስም የያዙትም በእምነት ሳይሆን ድጋፍ ለማግኘት ካልሆነም ተቃውሞን ለመቀነስ እንደሆነ የትግራይ አባቶችን ጠጋ ብሎ ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያዊ እምነትና ስሜታቸው ጥያቄ የማይነሳባቸው ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ በአንድ ጽሁፋቸው እነዚህ ሰዎች ከቀዳማይ ወያኔ ጋር በዓላማም በተግባርም ስለማይመሳሰሉ ወያኔ ተብለው መጠራት የለባቸውም አስመሳይ ወያኔዎች ናቸው ማለታቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ለግብራቸው የማይመጥን ስም ነው፤ ይበዛባቸዋል፡፡ እንደውም ለእነርሱ ፍላጎት መሳካት የሚበጃቸው ነው፡፡

አቶ አንዱአለም በጽሁፋቸው እኔ ራሳቸውን እንዲጠሩበት በመረጡት ስም ነው የጠራኋቸው ይላሉ፡፡ ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንዲሉ ወያኔ ትክክለኛ ማንነቱን የሚከልልለትንና ትግረኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ወገን ጋሻ ማድረግ ያስችለኛል ብሎ የመረጠውን ግብሩን የማይገልጽ ስም ለራሱ ስለሰጠ  እኛ ተቀብለን ማስተጋባት የለብንም፡፡ ይህን አደረግን ማለት በተዘዋዋሪ የወያኔን ፍልጎት ማሳካት ነው የሚሆነው፡፡ የወያኔ ስብከትና ማስፈራራያ ያልበገራቸው በርካታ ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞው ጎራ ጥንቃቄ የጎደለው ተግባር ያለፍላጎታቸው ወያኔን ለመደገፍ መገደዳቸው የአደባባይ ምስጢር ይመስለኛል፡፡ የሚወዱትን ሲያጡ እንደሚባለው ሆኖባቸው፡፡

አቶ አንዱአለም ትግሬዎችን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ግንባር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ሲል፤ ሌላ ምን ብዬ ልጠራው ይላሉ፡፡ ይህን አባባል ከላይ ለመግለጽ በሞከርኩት አስተሳሰብ ስናየው ሶስት ጉድለቶች አሉት የመጀመሪያው ትግሬዎችን ነጻ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ የሚለው ሲሆን ይህን ከላይ ለማሳየት ሞክሬአለሁ፤ ሁለተኛው ግንባር የሚለው ነው፡ከመጠሪያው ጋር ሊቀራረብ የሚችለው ህወሀት ነው እሱ ደግሞ ግንባር አይደለም፤ ግንባሩ ኢህአዴግ ነው፡፡ እሱን በጥቅሉ የትግሬ ነጻ አውጪ ለማለት ተፈልጎ ከሆነ ደግሞ ወያኔ ሀገራዊውን የፖለቲካ ትግል የጎሳ ትግል ለማድረግ ሌት ከቀን የሚማስንበትን ስራ እያሳካንለት ነው ማለት ነውና አደጋ አለው፡፡ ሶስተኛው ነኝ ሲል እኔ ምን ብዬ ልጥራው የሚለው ነው፡፡ እኛ መጠራት ያለብን እሱ ነኝ በሚለው ማንነቱን በማይገልጸው ሳይሆን ለማንነቱ በሚመጥነው ለግብሩ መገለጫ በሚሆን መጠሪያ መሆን አለበት፡፡ አሁን ልማታዊ መንግሥት እያለ ራሱን እየጠራ ነው ታዲያ እኛ በዚህ እንጠራዋለን?

ነገርን ነገር ያነሳዋል አንዲሉ በዚህ ረገድ ሌሎች ስህተቶችም ስንፈጽም ኖረናል አሁንም እየፈጸምን ነው፤ ብሶት የወለደኝ ሲል ተቀብለን ብሶት የወለደው ብለናል፣ በረሀ የወረድነው አንባገነኑን የደርግ መንግስት ለማስወገድ ነው ሲሉ ሰምተን አሰምተናል ተቀብለን ተናግረናል፡፡

እንደሚነግሩን ጫካ የገቡት የካቲት 1967 ነው፡፡ በዚህ ወቅት ንጉሱን ከሥልጣን ያወረዱት ወታደሮች ይይዙት ይጨብጡት የጠፋባቸው፣ ይሆኑት ያደርጉት ነገር የቸገራቸው ነበሩ፡፡ እናም ወያኔዎቹ ብሶት የወለደን ለማለት የሚያበቃቸው ምክንያት አልነበረም፤ሊሆን የሚችለውን የመተንበይ ችሎታ ነበረን ወይም ጠንቋይ እንቀልብ ነበር ካላሉ በስተቀር ደርግም በዛን ወቅት አንባገነን የሚባል አልነበረም፡፡

የሀገሬ አርሶ አደር አልጋ ፈርሶ አልጋ እስኪደላደል

               ይህን ግዜ ነበር የጠሉትን መግደል

እንደሚለው የንጉሱ ሥርዓት ፈርሶ መጪው ማንና ምን እንደሚሆን በውል ባልታወቀበትና የመንግስት ክፍተት በተፈጠረበት አጋጣሚ ሲያልሙት የኖሩትን ከአጼ ዮሀነስ በምንይልክ ከትግሬ በሸዋ ተነጠቀ ብለው የሚቆጩበትን ስልጣን የሚያገኙበት አጋጣሚ ያገኙ መስሎአቸው ምኒልክ ቤተ መንግሥት መድረስ ባይችሉም ከዮሀንስ ቤተ መንግሥት ሰተት ብለው ሲገቡ እየታያቸው ተጠራርተው ደደቢት ወረዱ፡፡ ነገር ግን ያሰቡት ያለሙት ሳይሆን ያልጠበቁት ሆነ፡፡ የ17 አመታት ትግልና ምኒልክ ቤተ መንግስት የመግባት ድል፡፡ ታዲያ እነዚህ እንደምን ብሶት የወለዳቸው፤ የደርግን አምባገነን ሥርዐት ለመታገል በረሀ የወረዱ ፣የትግሬ ነጻ አውጪ ሊባሉ ይችላል?

ይገረም አለሙ

amele.278@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule