በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አስመራ ላይ የተሰየመው የሻእቢያ መንግሥት ለ 23 ዓመታት የተከተለውን አካሄድ እንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ገጽታን ለማሳየት እና ራሱን አለሳልሶና የሰላም አባወራ ሆኖ ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን ኢትዮጵያስ ምን እንደምታ አለው? የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋናአላማው ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የሻእቢያ “የተሀድሶ” ስትራቴጂ አካሄዱና እንደምታው
Opinions
የኔ ሃሳብ
ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ
የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚ/ር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ማምሻውን ገብተዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም በዚያው የሚገኙ የኢህአዴግ ሹሞችና ልማታዊ ዲፕሎማቶች ድንገተኛውን ጉብኝት ተከትሎ ከብርሃነ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ ለነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች፣ ለልማት ማህበራት ተወካዮችና ለደጋፊዎቻቸው በሚስጥር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ምስጢራዊውን ጥሪ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን አንድ ባለስልጣን በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሟቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለስራ ጉብኝትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲገቡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን … [Read more...] about ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በድብቅ ጅዳ ገቡ
Ethiopia’s hope for changing an unwanted government by ballot box dashed
The Ethiopian current ruling party (actually it has been ruling the country for the past 25 consecutive years) has shown an enormous growth in becoming more and more dictatorship in each elections held every since it got on power by bullet not by ballot in 1991. On may 21 .2015 the ethnic based Ethiopian government organized a fake election as usual for the 5th time since the day it clinged on to the power by slaughtering Ethiopians during the harsh civil war which stayed for about 17 years. The … [Read more...] about Ethiopia’s hope for changing an unwanted government by ballot box dashed
በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
* የእናት 9 ዓመት ሰሚ ያጣ ጩኸት የ4 ዓመት ደልዳላ እያለ ድክ ድክ እያለ ሮጦ ለቀላል ህክምና ከጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አፍንጫ ስር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ገባ። ብዙም ሳይቆይ ከሰመመን መንቃት አልችል አለ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከሰመመን አልነቃም፣ በሃኪሞች ስህተት ብላቴናው መሀመድ ህይዎቱ ተሰናክሎ ላለፉት 9 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነል። ትናንትም ሆነ ከትናንት በስቲያም መሀመድና ቤተሰቦቹ ፍትህ ርትዕ ያገኙ ዘንድ ደጋግሜ ጠይቄያለሁ፣ ዛሬም እጠይቃለሁ! ላለፉት በዘጠኝ አመታት ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጀምሮ ሳይኖር "አለሁ" እስከሚለን የሴቶች ማህበር ተወካዮች ፍትህን ለመሀመድ ያስገኙ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ ፍትህ ማስገኘት ገዷቸዋል፣ ተበዳዮች ፍትህ ርቋቸዋል. . .! ክልትሙ ተንከባሎ ዛሬ ላይ ሲደርስ . . . ታሪኩን ከመሀመድ እናት ቃል በቃል ስሙት፣ ከዚህ ሁሉ … [Read more...] about በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
የስርዓቱን ብልግና ለመድነው
አሁን አሁንማ ዜና የሚሆን ነገር ጠፍቷል፡፡ መታሰር ተለምዷል፡፡ መደብደብ ተለምዷል፡፡ የሀሰት ምስክርነት ተለምዷል፡፡ ከአሁን ቀደም ‹‹ጉድ ነው!›› ያሰኙ የነበሩ ህገ-ወጥነቶች አሁን የቀን ተቀን ተግባር ሆነው ወደ ጎን እያየን እየተውናቸው ነው፡፡ በአጠቃለይ የስርዓት ነውር፣ ብልግና፣ ስርዓት አልበኝነትን ለዜናም የሚበቁ አልሆኑም፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹እንትና ጠያቂ ተከለከለች፣ እንትና ምግብ እንዳይገባለት ተደረገ›› ተብሎ ዜና ይሰራ ነበር፡፡ እንደ ትልቅ የስርዓቱ ብልግና እና ነውርም ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ እንዲያውም ይህ አይነት በደል የሚፈፀምባቸው በፀረ ሽብር ህጉ ተከሰው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን በሰልፍና በሌሎች ሰበቦች የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ በደል እየተደጋገመ ወደ ተራ አሰራርነት (የስርዓቱ ህግና ደንብ) ተቀይሯል፡፡ ነውር ቢሆንም እኛ ግን … [Read more...] about የስርዓቱን ብልግና ለመድነው
ምርጫ ሲባል፣
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ። ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል … [Read more...] about ምርጫ ሲባል፣
ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
ሰሞኑን በታጋዩ ወገን ስለ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ እየተወራ ነው። ገና ብዙ እንደሚወራም አጠያያቂ አይደለም። ለምን ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ በኛ ትግል ሂደት፤ ይሄን የመሰለ ቦታ ይዘው እንደተገኙ፤ ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው። ነገር ግን፤ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው ስለኢትዮጵያና ስለሚደረገው ትግል ያላቸው ሃሳብ ተዘግቧል። በአንጻሩ ደግሞ ስላሳቸው የኢትዮጵያ ጠላትነትና የትግሉ እንቅፋትነት ምስክርነት የሠጡ አሉ። በዚህ ሂሳብ፤ እስኪ እኔም በውል የማውቀውን ላቅርብ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለመጀመሪያ ጊዜ ተከዜን ተሻግሮ ወልቃይት በገባ ጊዜ፤ ሸረላ ላይ ጦርነት ገጥመን ክፉኛ ቆስዬ ነበር። በዚህም ምክንያት፤ የነበርኩበት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት በጣም ተመናምኖ፤ ሕልውናው አስጊ በሆነበት ሰዓት፤ ለመሰባሰብ፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር - ጀብሃ - … [Read more...] about ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
The truth may not be black or white. It may be gray. And embracing this fact is good for Ethiopia. Here is my take as an independent voice. My heart is for Ethiopia to find a bridge in reconciliation and mutual understanding. The Story of White The government is joyful that it had secured 100% of the known seats yet (442). This story states that the people had given a green card to the government and thus empowers the government to continue with the status quo. The story dictates that the … [Read more...] about Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ
የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም … [Read more...] about የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ
አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ . . .
የ"ምርጫው" ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ። "ሃሎ?" "ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?" "ነኝ፣ ምን ፈለግክ?" "ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።" "ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?" "99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!" "0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?" "አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?" "99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።" አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል። አንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። … [Read more...] about አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ . . .










