አቶ ዠ ለዩናይትድ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊነት ውድድር ተመዝግበው ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። ፍላየር እያደሉ ነው። ፍላየሩ ላይ የዌብ ሳይት፣ ኢሜይል አድራሻ፣ እንዲሁም የትምህርትና የሥራ ልምዳቸው ተደርድሯል። የዌብ ሳይታቸው www.z.com ይነበባል። የሥራ ልምዳቸውና የትምህርት ደረጃቸው ደግሞ እንደሚከተለው፣ የሥራ ልምድ፣ በዩናይትድ ኔሽንስ ኢትዮጵያን ወክሎ መቀመጥ ከሃምሌ 2007 ጀምሮ የባህል ሚኒስቴር፣ ሚኒስትር ዴኤታ ከመጋቢት 2007 እስከ ሃምሌ 2007 የማስታወቂያ ሚኒስቴር፣ የቅርንጫፍ ዳሬክተር ከግንቦት 2007 እስከ ሃምሌ 2007 የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ከምርጫ 2005 ጀምሮ የኢሃዲግ ፍቅር ቴአትር ቤት አርቲስቲክ ዳሬክተር ከየካቲት 2007 … [Read more...] about የአቶ ዠ ለዩናይትድ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊነት ውድድር
Opinions
የኔ ሃሳብ
የግንቦት 20 አከባበር
* ግንቦት 20 ሲከበር * አሸርጋጁ አደባባይ * የግንቦት 20 ፍሬዎች ልክ የዛሬ 25 ዓመት ... የድሉ እወጃ! በዚያች ቀን ነፍስ ያወቅን ሁላችንም የምናስታውሳት አዋጅ ተነገረች ..."የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሠራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ ሬዲዮ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል፣ ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም!" ግንቦት 20፣ 2008 ዓ.ም ማለዳ ... 25 ዓመት የድል ነጻነት ኢዮቤልዩ የድል በአላቸውን የሚያከብሩት የኢህአዴግና ሹማምንትና ደጋፊዎች በአደባባዩ ተገኝተዋል፣ በኢህአዴግ ከፍተኛ ሹማምንት፣ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ታድመውበታል ... ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኋይለ ማርያም ደሳለኝ ድሮ ሀገሬው "ሰው በላ" እያለ ያወግዘው የነበረበትን ቃል ተጠቅመው ዛሬ እሳቸው "ሰው በላ" ያሉት ደርግ የተገረሰሰበትን … [Read more...] about የግንቦት 20 አከባበር
Undoing The Counterproductive Cultural Reforms TPLF Carried Out
“Our Insanity: Doing the same thing over and over again and expecting different outcomes”- my latest commentary, addressed the importance of carrying out cultural reforms to defeat dictatorship, lawlessness, and poverty that have been plaguing our country for so long. When it comes to reforming our culture, we have two big tasks ahead: To undo the counterproductive cultural reforms TPLF has already carried out (The theme of this article), and To implement additional cultural reforms that may … [Read more...] about Undoing The Counterproductive Cultural Reforms TPLF Carried Out
የስኳር ነገር!
እንዴት ስነበታችሁ? ስሞኑን በሀገራችን ዙሪያ ከሰማናቸው አስደማሚ ነገሮች አንዱ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሸን ጉዳይ ነው:: ለዚህም ነው ይህን አጭር ጽሁፍ መሳይ ነገር - የስኳር ነገር ብዬ መስየሜ:: እንግዲህ እንደሰማነው የሰኴር ኮርፖሬሸን ከመከላክያ ብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ (ሜቴክ) ጋር በመሳለጥ 77 ቢሊዮን ብር (3. 8 ቢሊዬን የአሜሪካን ዶላር) እንደሰለቀጡ ነው የኦዲት ቢሮም፣ ባለስልጣናቱም ጀባ ያሉን:: በስራ አጋጣሚ ከኮርፖሬሽኑ እና ከሜቴክ ጋር በነበረኝ ግንኝነት ስለ ጉዳዩ የማውቀውን ያህል ለማካፈል እየሞከርኩ ነው:: ከዚህ ጥረቴ አንዱ በቅርቡ በሜይ 23, 2016 በኢሳት አምስተርዳም ስቱዲዮ እንወያይ በሚለው ፕሮግራም ላይ ተካፍዬ ነበር። የዚህ ጽሁፍ አላማም በውውይቱ የጠቀሰኳቸውን ጉዳዬች በተጨማሪም በሰአት ጥበት ምክንያት አልተጠቀሱም ብዬ ያሰብኳቸውን ጉዳዬች … [Read more...] about የስኳር ነገር!
የኢትዮጵያዊያን ማሕበር በሆላንድ
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡ ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን … [Read more...] about መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ
ሃራም ቦኮ ሃራም – ሃራም አልሸባብ
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአፍሪካውያንን ህልውና እየተፈታተኑ ካሉ ጉልህ ችግሮች መካከል ኣሸባሪነት ዋና ጉዳይ ሆኗል። ISIL በሊቢያ፣ ኣልሸባብ በምስራቅ ኣፍሪካ፣ ቦኮሃራም በምእራብ ኣፍሪካ በከባድ ፍጥነት እያደጉ ነው። አፍሪካውያን ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሽብር ስራዎች ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያነሱ የሚገባበት፣ ህዝቦች ግንዛቤያቸውን በማስፋትና የዚህን ኣሸባሪ መንፈስ ሊዋጉ የሚገባበት ሰዓት ላይ ነንና እኛ ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ ላይ በጽኑ መወያየት ያሻናል። በተለይ ወጣቱ በኣህጉራችን ስላለው የሽብር እንቅስቃሴ በሚገባ ሊረዳ ይገባዋል:: መምህራን አፍሪካ ውስጥ ስላጠላው የሽብር ጥላ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ኖሯቸው ተማሪዎቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል። ወደ ዋናው ውይይታችን እናምራ። ስለ ሽብርተኞች ሲነሳ የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ለመሆኑ እነዚህ ኣሸባሪ ቡድኖች ምንድነው … [Read more...] about ሃራም ቦኮ ሃራም – ሃራም አልሸባብ
“አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዜጎች “አሸባሪ” እየተባሉ በሚታፈኑባት፣ በሚገደሉባት፣ የደረሱበት በሚጠፉባት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ ሰሞኑን “88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች” “ጠፍተዋል” እየተባለ በሰፊው እየተናፈሰ ከመሆኑ አልፎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የህወሃት ሹመኛ መኩሪያ ኃይሌ በህወሃት ለተሰየመው የኢህአዴግ ምክርቤት (ወግ እንዳይቀር “ፓርላማ” በሚባለው) ቀርበው ስለነዚህ “ጠፉ” ስለተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ምንም አስተያየትም ሆነ ዘገባ ሳያቀርቡ እንደ ካኔተራ ውልቅ ብለው ሊወጡ ሲሉ፤ ምናልባትም ቤቶቹ የጠፉባቸው “የፓርላማው” አባላት ሊሆኑ ይችላሉ፤ “የገባህበት ገብተህ ታመጣታለህ” የሚል እንደምታ ያለው ቀጭን ትዕዛዝ ለመኩሪያ ሰጥተው ሸኝተዋቸዋል፡፡ ከዜጋ እስከ ወርቅ የሚጠፉበት ህወሃት አሁን ደግሞ ብዙ ኮንዶሚኒየሞች ጠፍተውበታል፡፡ ወሮታው ምን እንደሆነ … [Read more...] about “አፋልጉን ማስታወቂያ! 88 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብሎኮች ጠፍተዋል” ህወሃት
ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500 ዓመተ ዓለም አንድ የነጻነት መሪ ነበር። በዘመናዊ የማኔጅመንት ትምህርት ውስጥ የስራ ክፍፍልን የፈጠረና መሰረት የጣለ ትልቅ ሰው ነው። ይህ ሰው የተወለደው በጭንቅ ሰዓት ነበር። እስራዔላውያን በግብጽ ምድር በባርነት ቀንበር ስር ባሉበት ሰዓት። ንጉስ ፈርዖን የእስራዔላውያንን የጥበብ ስራዎች፣ የሚሰሯቸውን ጡቦች ቢወድም ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ከመጡ መንግስቴን ይነጥቁኛል ብሎ ስለፈራ ህጻናትን ሁሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ የተላለፈበት የጨለማ ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የተወለደው ይህ ሰው ወላጅ እናቱ በዓባይ ወንዝ ላይ በእንዲት ቅርጫት ኣሳፈረችው። መደበቋ ነው። በርግጥም ከወታደሮች ሰይፍ መትረፍ ችሏል። ለሶስት ወራት በዚህ ሁኔታ ወላጅ እናቱ ደበቀችው። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን ልእልት እየችው። ልእልት ይህን ህጻን ስታየው ያማረ ነበርና ቤተመንግስት … [Read more...] about ዘ-ፀዓት! . . . . ውጣ!
“ሄዶ ኢትዬጵያ (hej då Ethiopia)”
በቅርቡ በዚህ በምኖርበት አገር አንድ የልደት በአል ላይ ተጠርሼ ሄጄ ነበር፡፡ በዚሁ ዝግጅት ላይ ከዝህ በፊት በአካል አግኝቼው የማላውቀው የዚሁ አካባቢ ከበርቴ ጋር ስጨዋወት ነበር፡፡ በተለይ ከአመታት በፊት በኢትዬጵያ ታስርው ስለነበሩት የስዊድን ጋዜጠኞች ልቤ እስኪጠፋ ጠየቀኝ፡፡ እኔም የምችለውን ያህል ለመመለስ ሞከርኩ፡፡ ስንሰነባብት ያለኝ ነገር ግን ሰሞኑን በኢትዬጵያ ዙሪያ የሚሰማኝን ውጥንቅጥ ስሜት ቅልብጭ አድርጎ ገለጠልኝ። ምን አለኝ መሰላችሁ... "ሄዶ ኢትዬጵያ"። አለፍ ብሎም ስሜን በወጉ መጥራት እንደከበደው ነገረኝ። በዚህ በስዊድን አፍ "ሄዶ (hej då)" ማለት ቻው ወይንም ደህና ሁን/ሁኚ እንደማለት ነው። ከዚሁ ቤት እየወጣሁ ቃሉን በውስጤ ደጋገምኩት... ሄዶ ኢትዬጵያ ... ቻው ኢትዬጵያ ... በተመስጦ አሰብኩት። አዎ ልክ ነው። አሁን ሰለ ሃገሬ የሚሰማኝ … [Read more...] about “ሄዶ ኢትዬጵያ (hej då Ethiopia)”










