የማይነጥፈው የኢትዮጵያ ማህፀን፤ ከዓመት ዓመት፣ ከገዢ ገዢ ካምባገነን አምባገነን፤ ሳይደክም ሳያርፍ የሚጎርፈው፣ ሚሊዮን ሃያ ሁለት አፍርቶ ነበር በትውልዴ እኔ ሳውቀው። አሁንማ፣ አሁንማ፣ ካራት እጥፍ በላይ አድጓል አሉኝ፤ ደስታ በፊቴ ሲረጩልኝ። (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about እስከመቼ ኢትዮጵያ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
ጥያቄ አለኝ፥ የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው? ዛሬ ያላቅሜ አንድ ጥያቄ ማንሳት ከጅያለሁ። ለነገሩ ዶክተር ያልተጠየቀ ማን ይጠይቃል? እናም ዶክተርን ልጠይቅ ነው። ዶክተር መሳይ በኢትዮጵያ የዘውግን ፖለቲካ የጀመረው ማነው? ዶ/ር መሳይ ከበደ፥ የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ፥ በሚል ርእስ በአንድ መድረክ አቅርቤው ነበር ያሉትን ፅሁፍ በዚህ ድረ-ገፅ ላይ አውጥተው አስነብበውናል። እንደውነቱ ከሆነ በመድረኩ ተገኝተን ፅሁፋቸውን ለመከታተል እድል ላላገኘን ሰዎች በረከቱን ስላሳተፉን አመሰግናለሁ። ግን ጥያቄ አለኝ። ለጥቂቶች ስውር የስልጣን ጥም ማርኪያ፣ ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ደግሞ የህልውና ፈተና የሆነውን የዘውግ ፖለቲካ በዚያች አገር የተከለው ማነው? ህወሃት ወይስ አማራ? ለችግሩ መፍትሄው ክልሎችን ማጥፋት ሳይሆን ራስ ገዝ ማድረግና ስልጣን መስጠት ነው … [Read more...] about የዘውግን ፖለቲካ በኢትዮጵያ የጀመረው ማነው?
የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ከ25 ዓመታት በፊት አንድ የኮሌጅ ዲፕሎማ የነበረው አስተማሪ ሲቀጠር የመነሻ ደመወዙ 347 ብር ነበር። ይህን ገቢ በወቅቱ ከነበረው የዶላር ምንዛሬ አንጻር ስናየው 173.5 ዶላር ይመዝን ነበር። ይህ አስተማሪ ገና ሲቀጠር የቀን ገቢው 5.8 ዶላር ነበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ነበር። ከ25 አመት “እድገት” በሁዋላ በህወሃት ኢህዓዴግ ዘመን አንድ የኮሌጅ አስተማሪ ዲፕሎማውን ይዞ ሲቀጠር 1663 ብር ቢከፈለው አሁን ባለው ምንዛሬ ሲታይ 77.3 ዶላር ያገኛል። ይህ ማለት የቀን ገቢው በዶላር 2.57 ሳንቲም ነው ማለት ነው። ይህ ማለት የደርግ ጊዜው አስተማሪ ደመወዝ ከህወሃት ኢህዓዴግ ጊዜ አስተማሪው ደመወዝ ከሁለት እጥፍ በላይ ይበልጣል ማለት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የድህነት ወለል የሚባለው ሁለት ዶላር አካባቢ ሲሆን ይህ በህወሃት ኢሃዴግ ዘመን የኮሌጅ ዲፕሎማ የያዘው አስተማሪ … [Read more...] about የሲቪሉ ሰራተኛ ኑሮ በሁለቱ ዘመናት
ብክነትና ምክነት
በኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ የሚያባክን ማን እንደሆነ እናውቃለን። ጊዜም የሚያባክነው ማን እንደሆነ ሳናውቅ አንቀርም። እንዲሁም ወንድና ሴት እንደየተፈጥሯቸው እንዳይወልዱ የሚያመክናቸው ምን እንደሆነ አሳምረን እናውቃለን። አንናገርም እንጂ። ምሁራንንስ የሚያባክንንና የሚያመክን ማነው? ጎበዝ ማለት ይህን የሚያውቅ ነው። እኔም ማወቅ የምፈልገው ያገሬን ምሁራን የሚያባክንብኝና የሚያመክንብኝ ማን እንደሆነ ነው። ሰሞኑን ያዲስ አበባው መንግስት ቀለም ቀለም ሲሸተው ጊዜ እኔንም እንዲሁ ቀለም ቀለም ስለሸተተኝ ስለምሁራን ብንጫወት ምናለ ብዬ ለዛሬ ቁም ነገሬ እንዲሆን መረጥኩት፤ የኢትዮጵያ ምሁራን ጉዳይ፤ በተለይ ያቋማቸውና የጥቅማቸው ጉዳይ። በይበልጥ ደግሞ እንዲያው እንደዋዛ የመባከናቸው ነገር። ባክነዋል እንዴ? ካላችሁ መልሴ እንክት ነዋ! የሚል ነው። ላስረዳ። የምናገረው ባሁኑ ወቅት … [Read more...] about ብክነትና ምክነት
ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም
የአንድ አገር ድንበር የሚደፈረው፣ ሕዝቡ ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጠው የአገሩን ድንበርና የሕዝቡን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል በሕዝብ፣ ለሕዝብ፣ የሕዝብ የሆነ መንግሥት በሌለበትና ለጸረ ሕዝብ ሃይሎች አመቺ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በሃይል የጨበጠው የጎሳ ስብስብ በተደጋጋሚ የአገራችንንና የሕዝባችንን ጥቅምና ደህንነት ለአደጋ እያጋለጠ እራሱም የአደጋው ፈጣሪ እየሆነ መቆየቱን የሥልጣን ዘመን ታሪኩ ይመሰክራል። ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም
Our Insanity: Doing the same things over and over again and expecting different outcomes
After reading my recent articles, a colleague thought that writing about the leadership gaps and accusing of our culture as the root cause for our major troubles at this very critical moment is a distraction from the main thing. For him, the main thing is removing TPLF by all means with a sense of urgency. After a thorough discussion, we finally reached a common understanding. We agreed that these articles aren’t diversions but rather alarms and necessities if our desire is to quicken our … [Read more...] about Our Insanity: Doing the same things over and over again and expecting different outcomes
በቴሌኮንፈረንስ ለሚደረግ ስብሰባ ጥሪ
በሰሜን አሜሪካ ለምትኖሩ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አባሎች፣ ደጋፊዎች እና አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የስብሰባው ቀን፦እሑድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008 ዓም (Sunday April 24, 2016)፤ ሰዓት፦በኒውዮርክ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9:00 (3፡00 PM) ሰዓት ጀምሮ፤ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባሎቹ እና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የፕሮጀክቱን አላማ የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር በቴሌኮንፈረንስ የሚደረግ ስብሰባ ለማካሄድ አቅዷል። የስብሰባው ዓላማ የሞረሽ-ዐማራ ድምፅ የሬድዮ ፕሮጅክትን እውን ለማድረግ የሚያስችል የገንዘብ እና ሌሎች ዓይነት ድጋፎችን ለማሰባሰብ ይሆናል። ስለሆነም «የዐማራ ጉዳይ የኢትዮጵያም ጉዳይ ነው» የምትሉ ሁሉ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተገኝታችሁ የትውልድ እና የታሪክ አደራችሁን በመወጣት፣ ድምፅ-አልባ … [Read more...] about በቴሌኮንፈረንስ ለሚደረግ ስብሰባ ጥሪ
የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች፤ አልታረቅ ያሉ ሕልሞችና የኢህአዴግ ቆርጦ-ቀጥል ፖለቲካ
በዋሽግንቶን ዲሲ ለቪዥን ኢትዮጵያ ይቀርብ የነበረ ጽሑፍ • መንደርደሪያ ሀሳቦች የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ ባለሳምንት የሆነው ኢሕአዴግ፣ የደርግ ተመሳሳይ እድል ይግጠመው፤ አይግጠመው ባይታወቅም፤ አሁን ባለው ሁኔታ በሚሠራቸው ሥራዎች ውስጥ ከደርግ ያላነሱ ባዶ የመፈክር ጫጫታዎች ይበዙበታል፡፡ ሕልሞቹም የኢትዮጵያውያን የጋራ ሕልም መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ብዙ ነገሮች የሉበትም፡፡ በአሥር ዓመታት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ እንገባለን ተብሎ ከበሮ ቢመተም በዓለም ደረጃ በሚወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያቸን አሁንም የዓለም ጭራ ከሆኑት ሀገሮች ተርታ ናት፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች፤ አልታረቅ ያሉ ሕልሞችና የኢህአዴግ ቆርጦ-ቀጥል ፖለቲካ
የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ
ይህ ጽሁፍ በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ ያቀረብኩት ነው። የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በሠላም ወይም በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ ቢችሉም እንኳን፤ ባለፉት 24 ዓመታት የተዘረጋውን ዘውጋዊ ክፍፍል ለማብረድና ብሔራዊ አንድነትን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ራዕይና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ሁሉ ተቀዳሚና እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ዘውጋዊ ፖለቲካ በመሆኑ ያለውን መንግሥት ለመጣልና አዲስ ሥርዓት ለመመስርት ስለ ዘውግና ዘውጋዊ ፖለቲካ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘትን ይጠይቃል። ወያኔ ከተሸነፈ የዘውግ ፖለቲካ በራሱ ይጠፋል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው። ይህ ጽሁፍም “የዘውግ ፖለቲካ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ከብሔራዊ አንድነት ጋር በምን ሁኔታ ሊጣጣም … [Read more...] about የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሔ ሃሳብ
ወያኔና ትግሬ
አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤ የተጠቀሰውን አባባል የማያውቅ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፤ ለእስላሞችም ቢሆን አዲስ ነገር አይሆንባቸውም፤ አዳም ትእዛዝ ጥሶ ዕጸ በለስን በላና ተረግሞ ከገነት ወጣ፤ አዳም በደለ የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፤ አዳም በገነት ባካሄደው አብዮት የተነሣ የሰው ልጆች ሁሉ ከገነት እንደወጡ የሚቀሩ ሆነ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አዘነ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወረደና ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ እግዚአብሔር ይህንን በማድረጉ ሰዎች ከአዳም የወረሱት የጅምላ ኃጢአት ተሻረ፤ ከዚያ በኋላ ኃጢአት የግል እንጂ የጅምላ መሆኑ ቀረ፤ ይህ የሆነው መድኃኔ ዓለም የሰው ልጅን ከራሱ ጥፋት ለማዳን በመሰቀሉ ነው፤ ሃይማኖት ለመስበክ ሳይሆን የጅምላ አስተሳሰብ ቀና እንዳልሆነ እግዚአብሔር እንዳስተማረን ለማመልከት ነው፤ በዚህም መሠረት ፍትሐ … [Read more...] about ወያኔና ትግሬ










