• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የግንቦት 20 አከባበር

May 28, 2016 07:22 am by Editor 1 Comment

* ግንቦት 20 ሲከበር
* አሸርጋጁ አደባባይ
* የግንቦት 20 ፍሬዎች

ልክ የዛሬ 25 ዓመት … የድሉ እወጃ!

በዚያች ቀን ነፍስ ያወቅን ሁላችንም  የምናስታውሳት አዋጅ ተነገረች  …”የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሠራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ ሬዲዮ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል፣ ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም!”

ግንቦት 20፣ 2008 ዓ.ም ማለዳ …

25 ዓመት የድል ነጻነት ኢዮቤልዩ የድል በአላቸውን የሚያከብሩት የኢህአዴግና ሹማምንትና ደጋፊዎች በአደባባዩ ተገኝተዋል፣ በኢህአዴግ ከፍተኛ ሹማምንት፣ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ታድመውበታል … ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኋይለ ማርያም ደሳለኝ ድሮ ሀገሬው “ሰው በላ”  እያለ ያወግዘው የነበረበትን ቃል ተጠቅመው ዛሬ እሳቸው “ሰው በላ” ያሉት ደርግ የተገረሰሰበትን የግንቦት 20 የኢህአዴግ የኢዩቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ ንግግር እያደረጉ ነው … የ25 ዓመቱ የሰመረ የልማት ትራንስፎርሜሽን ስኬት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተዘረዘረ ነው፣ በንግግራቸው ባይመስጥም በ25 ዓመታት ተደረጉ ያሏቸው እድገቶች፣ ልማቶች፣ የተፈጥሮ አደጋ ጋር የተደረገው ፈታኝ ግብግብ፣ ዲሞክራሲያዊ መንግስት፣ የመልካም አስተዳደር ግንባታ፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማጥፋት እየተደረገ ስላለው ትግል ዘራዘሩ  … እንዲህ የሚሏት ሀገር ሀገሬ ስለመሆኗ ተጠራጠርኩ፣ የሆነው እውነት ከሆነ መልካም ነው ስል በትዝብት አንገቴን ደፋ አድርጌ ቆዘምኩ …

ከ25 ዓመቱን የኢህአዴግ አገዛዝ 4 ያህሉን አመታት ብቻ በሀገር ቤት ሆኘ የማውቅ፣ ከ20 ዓመት በላይ በሳውዲ ስደት የከተምኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ!  25  ዓመቱን አገዛዝ፣ ኢትዮጵያውያንን  እንደ መረጃ ተቀባይና አቀባይ ማሰብ በራሱ ያማል … እናም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ያሉት እድገት እያለ ዛሬ ድረስ፣ ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ መልካም አስተዳደርና ፖለቲካው ገፍቶት ከሀገር የሚሰደደው ዜጋ እልፍ አእላፍ እየሆነ በመጣበት የታሪክ አጋጣሚ የጠቅላያችን ንግግር አልገባኝ አለ! የእድገት ትሩፋቱ ተጠቃሚዎች ከመላው ሀገሬ ምን ያህሉ ናቸው?  በ25 ዓመቱ አገዛዝ መብታችን ይከበር ባሉ የተረገጡት፣ በጻፉና በተናገሩ ወጣትነታቸውን እድሜ የተቀሙ፣ ለአመታት ለእስር የተዳረጉ፣ በህገ መንግስቱ የተሰጠው መብት ይከበር ባሉ ወህኒ የወረዱ … እኒህኞቹስ? አልኩ … አዎ በአሉ የእነሱ ሊሆን አይችልም! ድፍን 20 ዓመት በአረብ ሀገር ስደት የተጎሳቆሉት፣ አሁን ድረስ የመብት አስከባሪ አጥተው ለሚንገላቱት “በአሉ በአላችን አይሆንም!”  ቢሉ አልፈርድባቸውም፣  በአንጻሩ “በ25 ዓመቱ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ተጠቅመናል” ያሉ ሰንጋ አርደው በዓሉን ቢያከብሩት አይደንቀኝም፣ ተጠቅመዋልና! ለእኔ ቁም ነገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብዛኛው ሀገሬ የመጣው ድል አብዛኛው ሀገሬ ተጠቃሚ ነው ወይ? የሚለው ነው! ታዲያ ተጠቃሚ ከሆነ ሰው  ሞትን እየተጋፈጠ ለምን ስደትን ይመርጣል? ይህ አልገባኝ ብሏልና ዛሬም አጠይቃለሁ! ginbot20

አሸርጋጁ አደባባይ …

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግን አብቅቶ ትርኢት መታየት ሲጀምር የመስቀል አደባባይ ትዝ አለኝ … አሸርጋጁ አደባባይ ያልኩትን የመስቀል አደባባይ “ይህ የተረገመ አደባባይ!” አልኩት በልቤ … መንግስት በሄደ  በመጣ ቁጥር ሰው ተመርጦ፣ በደቦ ተጠርቶ፣ ይሰበሰብበታል፣ ሰው ተመርጦ ” … ይህን መፈክር በል፣ ይህን መፈክር ያዝ … በዚህ ሂድ … ” ይባልና እንደ እውነተኛ የህዝብ ስሜት ይነገርበታል … ይህ አደባባይ፣ ሀገሬው በኑሮ ውድነት፣ በፖለቲካው ግለት እየታመሰ መሪዎች የሚመሯት ሀገር እድገቷ የመጠቀ፣ መጻኤ ህይወቷ ብሩህ እንደሆነ የሚደሰኩሩባት አደባባይ በእርግጥም የመቀል አደባባይ መባል አልነበረበትም! ቢያንስ ለሰው ልጅ ድህነት ምልክት የሆነው የመስቀሉ በዓል የሚከበርበት ቦታ ከዘመነ ደርግ እስከ ኢህአዴግ የውሸት ዲስኩር መናገሪያ፣ የውሸት ሰልፍና ሽለላ ማሳያ አደባባይ ባልሆነ በመረጥኩ ስል ከራሴ ጋር ተሟገትኩ …

በአደባባዩ የብሔር ብሔረብ ብዝሃ ህዝብ …ትርኢቱ እንደ ቀጠለ ነው፣ በስደቱ አለም የ 20 ዓመት መብት ማስከበር ክሽፈት ምስክር ነኝና ጠባቂ ባጣው ስደተኛ የሆነው ሁሉ ከፊቴ ድቅን አለ …

ግንቦት 20 ሳስታሰውስ ደግሞ ደርግ ትዝ አለኝ፣ ደርግ ክፉ ነበር፣ እንኳንም ወደቀ! በደርግ ግፍና ጭቆና ተማርራችሁ ስለ እውነተኛ ዲሞክራሲ ደክማችሁ ላለፋችሁ፣ ጭቆናን ተጸይፋችሁ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ስትሉ ከአባገነኑ ደርግ ጋር ለተፋለማችሁ ክብር አለኝ ፣ እንኳን ደርግ ከወደቀበት 25 ዓመት አደረሳችሁ!

… ግን የታገላችሁበት፣ የመጣው ድል ከብዝሃነት እስኪደርስ  የሆነው ያኮራል አልልም … ሌላው ቀርቶ ሀገር የተባለውን ያህል ካደገች ለምን ሰው ይሰደዳል?  አልኩ፣ እንደሞኝ ነገር ደጋግሜ የጠቅላያችን የዛሬ ንግግር አስታውሸ … ከራሴ ጋር መጃጃሉን ተውኩት፣ ዝግጅቱን መከታተሉንም አቁሜ ራሴን አቀርቅሬ የአረብ ሀገሩ ስደትና የግንቦት 20 ፍሬዎች ስል በማለዳ ወጌን  መሞነጫጨር ቀጠልኩ …! የግንቦት 20 ፍሬዎች … ይቀጥላል!

ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. ሸመልስይማም says

    June 2, 2016 09:18 am at 9:18 am

    ጨካኙና አረመኔው ህወሀት ኢሀዴግ አባታቸው ሻቢያ ዘሬ Is Is የሚፈፅመውን ዘግነኝ ድርጊት በንፁሀን አትዮጵያን ላይ ፈፅመዉታል የኔ አንዲህ አንደ አሁኑ ቴክኖሎጂ ያልተስፋፋበተ ሰለነበር አለም አላወቃቸዉም ነበር አናም ከነዚ ገንጣይ አስገንጣይ ቡደኖቸ ልማተም ሆነ እድገት የለም

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule