• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የስኳር ነገር!

May 25, 2016 11:54 pm by Editor Leave a Comment

እንዴት ስነበታችሁ? ስሞኑን በሀገራችን ዙሪያ ከሰማናቸው አስደማሚ ነገሮች አንዱ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሸን ጉዳይ ነው:: ለዚህም ነው ይህን አጭር ጽሁፍ መሳይ ነገር – የስኳር ነገር ብዬ መስየሜ:: እንግዲህ እንደሰማነው የሰኴር ኮርፖሬሸን ከመከላክያ ብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ (ሜቴክ) ጋር በመሳለጥ 77 ቢሊዮን ብር (3. 8 ቢሊዬን የአሜሪካን ዶላር) እንደሰለቀጡ ነው የኦዲት ቢሮም፣ ባለስልጣናቱም ጀባ ያሉን:: በስራ አጋጣሚ ከኮርፖሬሽኑ እና ከሜቴክ ጋር በነበረኝ ግንኝነት ስለ ጉዳዩ የማውቀውን ያህል ለማካፈል እየሞከርኩ ነው:: ከዚህ ጥረቴ አንዱ በቅርቡ በሜይ  23, 2016  በኢሳት አምስተርዳም ስቱዲዮ እንወያይ በሚለው ፕሮግራም ላይ ተካፍዬ ነበር። የዚህ ጽሁፍ አላማም በውውይቱ የጠቀሰኳቸውን ጉዳዬች በተጨማሪም በሰአት ጥበት ምክንያት አልተጠቀሱም ብዬ ያሰብኳቸውን ጉዳዬች ለመዳስስ ነው።

እንግዲህ በህወሐት ጐራ ላለፉት ስድስት (ሰባት) አመታት በትልቁ ሲጐሰሙ ከነበሩ ትላልቅ (ሜጋ) ፕሮጅክቶች የስኳር ኰርፖሬሽን ዋንኛው ነው። በተጨባጭ መረጃዎች መሰረት በላዪም የመንግስት ቱባ ባለስልጣናት እንዳመኑት የስኳር ነገር “ወፍ የለም” እንደሚሉት ከሆነ ከራርሞአል፡፡ አይደለም ሰባት አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ይቅርና  የነበሩትን “ማስፋፊያ ፕሮጀክት” ብለው ነካክተው ምስቅልቅሉን አውጥተውታል፡፡ “ጥድቁ ቀርቶ በቅጡ በተኰነንኵ” እንዲሉ::

ላለፉት ስባት እና ስድስት አመታት እከሌ የሚባለው ኘሮጀክት ይህን ያህል ተጠናቋል፤ ያኛዉ ደግሞ በሚቀጥለው አመት ማምረት ይጀምርና ይህን ያህል ሚሊዬን ኩንታል ስኳር ወደ ዉጭ አገራት እንልካለን፤ እና የመሳሰሉትን የመግለጫ ጋጋታዎች ለሕዝቡ በስኳር ኰርፖሬሽን እና በሜቴክ የተጋቱ እንደ ስኳር ነጭ የሆኑ ዉሸቶች ናቸዉ። ለምን ይዋሻል? እንጠይቃለን። እስከመቼስ? በዉሸት እንዲህ ያሰከሩንስ ምን ሆኑ? ለዚህ ሁሉ ዉሸት ሐላፊነት ማን ወሰደ? አሁንም እንጠይቃለን። መልስ እስኪገኝ።

ባከነ የተባለዉ ገንዘብስ? 77 ቢሊዬን ብር (3.8 ቢሊዬን ዶላር)። ባከነ የሚለዉ ቃል ለእኔ ብዙ አይመስጠኝም። አማረኛ ማሳመሩን ትተን እዉነቱን በግልፅ አማርኛ መተንፈስ ነው የሚያዋጣው። ስለዚህ ተዘረፈ። ተሰረቀ። ነው የሚባለው። ሜቴክ በስኳር ኳርፖሬሽን ኘሮጀክቶች ስም ከኢትዬጵያ ሕዝብ ላይ ብሎም በሕዝብ ስም የተገኘውን የብድር ብር ዘረፈው ብንል እውነታውን በተሻለ መልኩ ይገለፃል። እንደ እኔ አሁን አማርኛ የምናጣፍጥበት ወቅት ላይ አይደለንም። 20 ሚሊዬን ሕዝብ ተርቦ የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለተረጂ ወገኖቻችን የ 1.5 ቢሊዬን ዶላር ያለህ እያለ ሲጮህ፣ ሜቴክ ደግሞ 3.8 ቢሊዬን ዶላር ላፍ አድርጐ አየሁሽ አላየሁሽ እያለ ሲያፌዝብን የምን አማርኛ ማሳመር ነዉ? ምንስ ሊበጀን?

በግሌም ከኮርፖሬሽኑ ጋር ለመስራት የተስማሙ የውጭ ኩባንያዎችን በመወከል እሰራ ስለነበር የዘረፋውን ሒደት ለመታዘብ ችያአለሁ። የውጭ ኩባንያዎችን ወክዬ ከኮርፖሬሽኑ ጋር የተወሰኑትን ፕሮጀክቶች ለመውሰድ ስደራደር፣ ሜቴክ ከኋላ “ቀይዋን ያየ” በሚመስል ጨዋታ ስኳር ኮርፖሬሽን ሆኖ ብቅ አለ። ለካስ ኮርፖሬሽኑ ለስሙ ነው እንጂ ሙሉ በሙሉ በሜቴክ ቁጥጥር ስር ነው። ድርድሩንም፣ ብሩንም ወደ እኔ አለን ሜቴክ በወታደራዊ ቀጭን ትእዛዝ። ያው ወታደሮች አይደል የሚመሩት ወዴት እንደሆነ ባይታወቅም። የሜቴክ ሐላፊዎች የድፍረታቸው ድፍረት ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን፣ በብድር ከሚገኘው ገንዘብ ላይ ኢንተረስት ሬትን ለመቀሸብ ሳይቀር ይደራደራሉ!? ወይ ድፍረት! አጃኢብ የሚያሰኝ ነው። በነገራችን ላይ ይህ ብድር በኢትዬጵያ ሕዝብ ስም እና በኢትዬጵያ ሶቨሪን ጋራንቲ (ዋስትና) የሚገኝ ነው። የማላስቸግራችሁ ከሆነ እና በግሌ ከሜቴክ ጋር የገባሁበትን እሰጥ እገባ ወይም ውዝግብ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ከኢሳት ጋር ባደረኩት ውይይት በዚህ ማስፈንጠሪያ መኰምከም ይቻላል።

ጐበዝ ይኼ የሙስና ጉዳይ ብቻ አይደለም። በሙስና በሚታሙ አገሮች ሰርቼአለሁ። በእነዚህ አገራት ሌላው ቢቀር ሙስናው እንዴት እንደተከወነ ማየት የሚቻልበት መዋቅር (structure) አለ። በኢትዬጵያ ሁኔታ ይኸ ፈፅሞ አይታይም። ዘረፋው እጅግ አስፈሪ እና አደገኛ ነው። ሕወሐት አገሪቱን በኢኮኖሚ ሴክተሮች በመከፋፈል በምርቃና ፕሮጀክቶች ስም ሰቅዞ ያለማቋረጥ እየዘረፈ እና እየሰረቀ ነው። ስለዚህ ወይ ጉድ!? ወይ ሜቴክ? ወይ ስኳር ኮርፓሬሽን? እያልን በመደመም እንደ ተከታታይ ፊልም የምናየው የሙስና ጉዳይ ብቻ አይደለም። ኢትዬጵያ በዝርፊያ እየተናጠች ነው። የዝርፊያው መጠን እና አካሔድ እንደ አገር የመዝለቃችንን ነገር ፈተና ውስጥ ያስገባ ውስብስብ ቀውስ ነው።

ዳሩ ለውጥ አይቀሬ ነው። እንዲያው በዘገየ ቁጥር ለለዋጩ ሐይል አዲስ ጉልበት ሲጨምር፣ ለተለዋጩ ግን ወደ ማይወጡት ማጥ ውስጥ መነከር ነው። እንዲህ በአገር ላይ እያፌዙ መቀጠል ከቶ አይዘልቅም፣ አያዛልቅም። ለዘራፊዎች ግን አንድ ነገር ልበል። በቅርቡ አቶ አሰፋ ጨቦ “የትዝታ ፈለግ” የሚለውን መጽሐፍቸውን አስመልክተው አንድ ቃለ-መጠይቅ ሲሰጡ የተናገሩት ገጠመኝ ትዝ አለኝ። ደርግ ወድቆ ህወሐት አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት ነው አሉ። አዲስ አበባ ቀውጢ ሆናለች። እሳቸውም ከእስር የተፈቱበት ሰሞን ነው። እናም የጓደኛቸውን መኪና ይዘው ለመንዳት በአካባቢው ያገኙትን ሰው ቤንዚን የት ማግኘት እንደሚችሉ ይጠይቃሉ። ሰውየውም የት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁሟቸው፣ አንድ ነገር ግን ጠየቃቸው “ለመሆኑ ቤንዚኑን ቀድተህ መኪናውን የት ልትነዳው ነው በዚህ በቀውጢ ጊዜ?” እኔም ኢትዬጵያን እየዘረፉ ያሉትን ዘራፊ ባለስልጣናት ተመሳሳይ ጥያቄ ልጠይቅ። ለመሆኑ ይኼን ሁሉ ዘርፋችሁ የት እና መቼ ልትበሉት ነው?? ሊበላ?! አለች አሉ።

አገራችንን ፈጣሪ ይባርክ።

ወንድማአገኝ እጅጉ። ከ-ስቶኰልም፤ ስዊድን


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule