ወያኔ ስልጣንን የሙጥኝ ይዞ ሀገራችንንና ህዝቧን ቁም ስቅል ማሳየት ከጀመረ እነሆ 26 ዓመታት ተቆጠሩ። ከጀሌዎቹና ፍርፋሪ ከሚበትንላቸው አጨብጫቢዎቹ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል የህዝብ ድጋፍ ሳይኖረው ይልቁንም በህዝብ ተጠልቶና ተተፍቶ ከሩብ ምዕተዓመት በላይ ስልጣን ላይ የመቆየቱ ነገር እንቆቅልሽ የሆነባቸው እጅግ በርካታ ናቸው። በአንፃሩ ስርዓቱን ለማስወገድ በተለያየ አቅጣጫ የሚደረገው ትግል ውጤት አልባ መሆን ተስፋ አስቆርጧቸው የወያኔ ከወንበሩ መነሳት የማይታሰብ እንደሆነ የደመደሙም አልጠፉም። ይህ ፅሁፍ የገዢው ቡድን የስልጣን ዕድሜ እንዲህ የተንዘላዘለበትንና እስካሁን የተደረጉ የለውጥ ትግሎች ውጤት ያላመጡባቸውን ምክንያቶች እንዲሁም ወደፊት ወያኔን ለማስወገድ የሚደረጉ ትግሎች ከግንዛቤ ቢወስዷቸው መልካም የሚሆኑ ነጥቦችን ለመዳሰስ ይሞክራል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ … [Read more...] about የወያኔ የሩብ ምዕተዓመት ስልጣንና ፀረ−ወያኔው የትግል ጉዞ
Opinions
የኔ ሃሳብ
አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ምን ነካው?
ከአጭር ግዜ እረፍት በኋላ፣ EBC ላይ ብቅ ያለው "ቤቶች" በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በክፍል185 እጅግ አስደምሞናል። ተመልካቹ ህዝብ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ጥላሁን ጉግሳ ላይ እየወረደበት ያለው "አሽቃባጭ፣ የወያኔ አቃጣሪ..." ወዘተ ውግዘቶችና ስድቦችን ባልጋራም፣ ይህ አንጋፋ አርቲስት ጥበብን የፖለቲካ መደለያ ስለማድረጉ ግን ምስክር አያሻም። በአንድ ወቅት እጅግ ተወዳጅ የነበረ ይህ ድራማ በመጠነኛ የህወሃት ልማታዊ ቅኝት እየተቃኘ መጥቶ አሁን ላይ ወገን የለየ ይመስላል። ዶፍ ሲጥል ገሚሱ ይበሰብሳል፤ ሌላው ተጠልሎ ይመለከታል፣ ጥቂቱ ደግሞ ይቀልዳል። ቀልደው ሞተዋል! ይህንን ድራማ ስመለከት፣ ገሃዱን አለም ከምናቡ አለም በቅጡ ሳይለዩ፣ ሃያልነትዋን ያልተረዱ አርቲስቶች ጥበብን ለተልካሻ ጉዳይ ሲመነዝሩዋት አስተዋልኩ። ወዶ ይሁን ተገድዶ ብቻ፣ በህዝብ ላይ የተከፈተ … [Read more...] about አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ምን ነካው?
ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ
በነዚያ የነተቡ ብዕሮች "ተራራውን ያንቀጠቀጠ" እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩ ሁሉ እነሆ በአንድ ብላቴና ሲንቀጠቀጡ ከማየት የበለጠ ምስክር ከየትም ሊመጣ አይችልም። የ"ኢትዮጵያ" ስም ሲጠራ ብርክ እንደያዘው የሚሽመደመዱ፤ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እያልን በጣት የምንቆጥራቸው የጥላቻና የበቀል ጉግማንጉጎች ለመሆናቸውም ትውልድን ደፍሮ ይናገርላቸዋል። የዚህ ቡድን አባላት ከመጠን ያለፉ ጭቃዎች መሆናቸውን እንኳ ለማወቅ ራሳቸውን በመስታወት የሚመለከቱ አይመስልም። መቶ ሚሊዮን ሕዝብ እየመራ ያለው ይህ ቡድን በየትኛውም መመዘኛ ቢለካ አርቆ ማሰብ እና አስተዋይነት ይጎድለዋል። አስተዋይነት ደግሞ የታላላቆች ውድ ስጦታ ስለሆነ ከርካሽ ሰዎች አይጠበቅም። አበው ትተውልን ያለፉት አንድ ቅርስ፣ ያቺ የቀስተደመና ተምሳለት፣ ያቺ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስትነሳ አጋንንት እንደለከፈው እርያ … [Read more...] about ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ
Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
Remembering Peaceful Demonstrators Murdered by TPLF in Bahir Dar One Year Ago The area in which this took place is called Abay Mado“Kobel”, located in Bahir Dar. It was in the August of last year when all over the country, Ethiopians, including the youth were peacefully demonstrating in large numbers, expressing their displeasure towards the ethnocentric, extremely corrupt and suppressive regime of the TPLF. The youth in Bahir Dar was expressing its solidarity with “Welkite” and “Oromo” … [Read more...] about Abay Mado “Kobel” Massacre by TPLF
ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ክምሩን የሀገር ሀብት ስርቆት ፣ ብክነት ሳስበው ... ክምር በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር መዋዕለ ንዋይ ከመቶ ባልበለጡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የመዘረፉን ወንጀል እየሰ ማን ነው ። ጥሎብኝ ገንዘቡን ወደ አባይ ግድብ አስጠጋውና የሳውዲ ነዋሪ ለአመታት ካጠራቀመው ጋር አወዳድረዋለሁ። አልገናኝህ ይለኛል ... ገንዘቡ ከፍ ሲል ሌላ ማወዳደሪያ እፈልጋለሁ ። .. ውጭ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ ወደ ሀገር ከሚልከው ገንዘብ የተገኘውን ገቢ አስበውና እንደገና የተሰረቀው ከባድ የመሆኑን ክብደት ያስደነግጠኛል ፣ እደነግጣለሁ ። "ጠፋ ፣ ተሰረቀ" የተባለው የዚህች ድሃ ሀገር ገንዘብ ስንት አውሮፕላን እንደሚገዛ ሳሰላ ውዬም አውቃለሁ፣ የሞኝ ነገር ትሉኝ ይሆናል። ግን አይደለም። የገንዘቡን ክብደት ለማወቅ እንጅ ... እንዲህ ሲቆጨኝ ስዳክር ነው የሰነበትኩት ክምሩ የሀገር ሀብት መሰረቅ … [Read more...] about ግፍ ያልገታው፣ ያልተንበረከከው መንፈስ !
ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫሎች ላይ የቦይኮት (እቀባ) ዘመቻዎች ተነስተው ነበር። የዘመቻዎቹን ውጤቶችም አይተናቸዋል። በዚች አጭር ጽሁፌ የማተኩረው በውጤቶቹ ላይ አይደለም። በሲያትሉም ሆነ በሮም ዝግጅቶች ላይ ስለነበርኩ፣ የቦይኮት ዘመቻዎቹ ከጅምሩ ጥቅም እና ጉዳቶችን አመዛዝነው ነበር ወይ የሚለውን በጥቂቱ ለመፈተሽ እሞክራለሁ። በዚህ ርዕስ ላይ ስጽፍ አዋራ እንደሚነሳ አምናለሁ። በጉዳዩ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲወያዩ ብታዘብም በፍርሃት ይሁን በሌላ ምክንያት ሃሳባቸውን በአደባባይ ለመናገር ግን ሲደፍሩ አይታይም። ሃሳባቸውን በድፍረት የሚሰነዝሩ ወገኖችም ቦይኮት ስለሚደረጉ ብዙዎች ዝምታን ቢመርጡ አይደንቅም። "አህያ የለኝ ከጅበ አልጣላ" ብሎ ሃሳቡን በነጻ ለመግለጽ የሚሞክር ደግሞ ይሰደባል። በሳይበሩ አለም፣ ወቅትን እየጠበቀች በምትነደው … [Read more...] about ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!
የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ - የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ሰጡዋቸው። ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት አብስረዋል። እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም። ታሳሪዎቹን ሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር እንደማንኛውም ተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል? ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው - መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምን አቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል? የሙስና ጉዳይ … [Read more...] about ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!
መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በዲሴምበር 5, 1989 ዓ.ም. በምስራቅ ጀርመኗ የድሬዝደን ከተማ ነዋሪው በነቂስ ወደ ጎዳና ወጥቶ ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያሰማ ነበር። የተቃውሞው ኃይል እየበረታ ሲመጣ ህዝቡ ወደ አንድ ህንፃ መትመም ጀመረ። ላለፉት 40 ዓመታት የራሱን ህዝብ መተንፈሻ በማሳጣት ከፍተኛ አፈና ያደርግ ወደነበረው የደህንነቱ መስሪያ ቤት፥ወደ ''ሽታዚ'' ተብሎ ወደሚጠራው መስሪያ ቤት። ጥቂት ወጣቶች ግን የሽታዚን ቢሮ ሰብሮ ከገባው ህዝብ በመነጠል በጥቂት ሜትሮች ርቀት ወደሚገኝ አንድ ህንጻ አመሩ።የወጣቶቹ ወደ ህንፃው እየተጠጉ መምጣት ያሳሰበው የጥበቃ ሰራተኛ በፍጥነት ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት አንድ ቀጭን እና አጭር የሆነን የ37 ዓመት ሰው አስከትሎ ወደተሰበሰቡት ሰዎች አመራ። ያም ቀጭኑ ሰው ጥርት ባለ ጀርመንኛ ''ይህ ህንፃ የሶቭየት ህብረት … [Read more...] about መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የጥላቻ መንስዔ፣ መዘዝና መፍትሄ
የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? በዚህ ላይ ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው። … [Read more...] about የጥላቻ መንስዔ፣ መዘዝና መፍትሄ
የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት
የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት - ያኔ ነው ያበቃለት! ከቶውን "የአለምን ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር" የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ አይሆንም። ይነፋ የነበረው የእድገት ቀረርቶ እና ይነገር የነበር ሁለት ዲጅት እድገት ቁጥር ሁሉ ውሸት ነበር፣ ወይንም ደግሞ የሃገሪቱ ሃብት በጥቂቶች እየተዘረፈ ነው። ጆሮን ያሰለቸው የ"እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ" ዘፈን ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር የ "ደብል ድጅቱ" የፈጠራ ተረት እንደ በረዶ እየነጻ መሄዱ አልቀረም። እድገቱ የህዝቡን ህይወት አልለወጠም። ተጀምሮ ከሚቋረጥ ህንጻ … [Read more...] about የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት










