• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት

July 23, 2017 07:18 am by Editor Leave a Comment

የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ  አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት – ያኔ ነው ያበቃለት!

ከቶውን “የአለምን  ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር” የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ አይሆንም።  ይነፋ የነበረው የእድገት ቀረርቶ እና ይነገር የነበር ሁለት ዲጅት እድገት ቁጥር ሁሉ ውሸት ነበር፣  ወይንም ደግሞ የሃገሪቱ ሃብት በጥቂቶች እየተዘረፈ ነው።

ጆሮን ያሰለቸው የ”እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ” ዘፈን ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር የ “ደብል ድጅቱ” የፈጠራ ተረት እንደ በረዶ እየነጻ መሄዱ አልቀረም። እድገቱ የህዝቡን  ህይወት አልለወጠም። ተጀምሮ ከሚቋረጥ ህንጻ እና መንገድ ውጭ ትራንስፎርሜሽኑም በተግባር አልታየም። ይልቁንም ተሸፍኖ የነበረው ችግር አሁን ፈጥጦ ወጥቶ በህዝብ ጫንቃ ላይ ጉብ ሊል ዳዳው፣ ገበሬውን መሬት በመንጠቅ፣ ነጋዴው ላይ ደግሞ ሚዛናዊ ባልሆነ የገቢ ግምት – ከፍተኛ ግብር በመጫን።   ምላሹንም እንደምናየው ነው።  አድማ፡ ህዝባዊ አመጽ፣… ተቃውሞ!

በዘንድሮው የበጀት አመት የህወሃት መንግስት 320 ቢሊዮን ብር ማጽደቁን አብስሮን ነበር።  ይህ በጀት የ100 ቢሊዮን ብር  (1/3ኛ) የበጀት ጉድልት ነበረበት። ይህ የ100 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ከብድር እና እርዳታ ይሸፈናል ተብሎ  ነበር የተጠበቀው። የ11 በመቶው እድገት ተረት – ተረት  ውስጥ የእርዳታው እና የብድሩ መጠን ተገልጾ አያውቅም። ሃገሪቱ በደፈናው እያደገች ነው አሉን። በፈጣን እድገት የአለምን ኢኮኖሚ የምትመራ ሃገር ተባለ።  ፈረንጆቹም አመኑ።

እርዳታን  እንደ ስትራቴጂ የቀመሩት የህወሃት ጠበብቶች፣ ፈረንጆች ፊታቸውን ማዞር እንደማይሳናቸው እንኳን አላሰቡትም። በሶማሊያ ውስጥ የነሱን ቆሻሻ ጦርነት ስለተረከቡ ብቻ ጉዳዩን እንደ ይገባኛል መብት (for granted) አዩት። የሶማልያ ጉዳይ፣ የአልሻባብ ፖለቲካ ዲስኩር፣ የጸረ-ሽብር እንቶፈንቶ አሁን የለም። አሜሪካም ሆነች የአውሮፓ ህብረት ዜጎችን በአዋጅ እና በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አፍኖ የያዘው ስርዓት ጋር በረጅሙ እንደማይዘልቁ ግልጽ ነው። ታዲያ ከቻይናው የእድሜ-ልክ የእዳ ቁልል ውጭ የታሰበው የውጭ ገቢ ጠፋ። ማጠፍያው አጠረ። ለሰራዊቱና ለደህንነቱም ደሞዝ መከፈል አለበት።  …ቀሪው ገንዘብ ከግብር እና ከሃገር ውስጥ የሚሰበሰብ ገንዘብ ብቻ ነው።

እናም እዳው ሕዝብ  ላይ ተቆለለ። የቀን ገቢ በግምት እየታየ ተጫነ። በገቢና ወጪ ሳይሆን፣  በህዝብ ላይ በግምት ግብር ሲጫን በታሪክ የመጀመርያው ሳይሆን አይቀርም። አዲሱ የግብር ትመና በንግዱ ህብረተሰብድ ከባድ ቁጣ ቀስቅሷል። ከጫፍ እስከጫፍ የተነሳው የሥራ ማቆም አድማ የት ላይ እንደሚቆም አይታወቅም። በአስቸኳይ ግዜ በምትተዳደር ሃገር የተነሳው ይህ አድማ ቀድሞ የተጀመረው የመብት እና የነጻነት ትግል ቅጣይ ይመስላል። ቀድሞ የተነሳው የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።  የህወሃት የአፈና ሰንሰለትም እንደቀጠለ ነው። ዛሬ ነጋዴው ህብረተሰብ የሰለባው ባለሳምንት ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሰረታዊ ችግር ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የግብር ፖሊሲ አይደለም። ችግሩ ስርዓቱ ራሱ ነው። ዛሬ የንግድ ቤቶች ቢዘጉ ሌላ የንግድ ቤቶችን የመክፈት አቅም ያላቸው የህወሃት ሰዎች በደስታ መፈንጠዛቸው አይቀርም። …አሜካላው ሳይነሳ መፍትሄ አይታሰብም።

ዋናው ነገር ወዲህ ነው። ግብር ለመክፈልም እኮ የህዝብ ውክልና ያለው ስርዓት መኖር ግድ ይላል። የሀዝቡን ይሁንታ ያላገኘ መንግስት፣ በሕዝብ ያልተመረጠ መንግሥት ግብር የማስከፈል መብት የለውም፣ ሕዝቡም ላልወከለው መንግስት ግብር ለመክፈል አይገደድም።

እ.ኤ.አ. በ1750ቹ እና 1760ቹ አስራ ሶስቱ የአሜሪካ ቅኝ ግዛቶች ይዘውት የተነሱት መፈክርን ያስተውሏል። “No Taxation Without Representation” ይላል። “ውክልና ከሌለ ግብር አይኖርም” እንደማለት ነው።  አሜሪካኖች በዚያ የነጻነት ትግላቸው ወቅት አቋማቸውን ለመግለጽ የተጠቀሙበት መሪ ቃል ነበር።  አመሪካውያኑ ይህንን መፈክር ይዘው በማመጽ የብሪትሽን ኤምፓየር እንዳናፈጡት የታሪክ ማህደር ያወሳናል።

ህወሃት የህዝብ ይሁንታም የለው፣ መረጃም የለው። ሃይለማርያም ደሳለኝ በብሄራዊ ቴሌቭዥን ለይ ወጥተው እንዲህ አሉ። ስራችንን የምንሰራው፣ ውሳኔም የምንወስነው መረጃ ሳንይዝ እንዲሁ በግምት ነው። “መረጃ የሚጠናከርበት ስርዓት የለም።” አሉ።  እኚህ ሰው አንዳንዴ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ  እውነትን ይለቁልናል። ንግግራቸው እኝህ ሰው ነጻ ያለመሆናቸውን ይጠቁመናል።   ሃገሪቱ ነጻ መውጣት ካለባት በመጀመርያ ነጻነትን ማወጅ ያለበቸው እሳቸው ናቸው። እውነት ነው።  ህወሃት እየመራ ያለው በግምት እና በጥይት ነው።

የሃይለማርያም ንግግር አጉልቶ የሚያሳየን ነገር አለ። ስርዓቱ ችግር ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፣ ስርዓቱ ራሱ ችግር መሆኑን ግልጽ ያደርግልናል።

ትግራይ “ክልል” ፕሬዝዳንት እና የመቐሌ ከንቲባ ላይ ከሰሞኑ የተፈጠረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የሚሰብቀን ነገር ይኖራል። ከሰሞኑ በመቀሌ ስታድዮም የገባው ህዝብ በዝግጅቱላይ በተገኙ የህወሓት አመራሮችን “ሌባ ሌባ ሌባ .. ሃሳዊ (ውሸታም) መሲህ ሲሉ ተደምጠዋል። እንግዲህ የትግራይ ህዝብ ራሱ ተወክያለው ያለውን አመራር “ሌባ ሌባ ” ካለ ምን ቀረ?… እንደኔ ግምት የቀረ የለም። ሃገር እየተመራች ያለችው መረጃ በሌላቸው፣ ራዕይ በሌላቸውና የህዝብ ይሁንታ ባላገኙ ሌቦች ነው።

ከትግራይ ውጭ ያለውም ሕዝብ እንዲህ ነው የሚለው። “ወያኔ ሌባ ነው! ለሌባ ግብር አንከፍልም!”

“ኢትዮጵያንና ህዝቧን በጉልበት አፍኖ ለያዘ ዘራፊ ቡድን አንገብርም!!” ብለዋል ጊንጪዎች። ይህ የግብር አመጽ የፍጻሜው ጦርነት ይሆን? እድሜ ከሰጠን እናየዋለን።

ለዛሬ በዚህ ላብቃ በመጪው ጽሁፌ ስለ “ኳስ እና ፖለቲካ” የምለው አለኝ።

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule