ሰሞኑን የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ አሰልጥኖ ጃዝ ባላቸው ቅልብ ነፍሰ ገዳዮቹ፣ በኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያና ማፈናቀል፣ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በጽኑ ያወግዛል። ይህ አንዱን ነገድ በሌላው ነገድ ላይ በማስነሳት፣ አንደኛው ሌላውን ከክልሌ ውጣ ማለት የወያኔ የሥልጣን ዘመን ማራዘሚያና ኢትዮጵያን የማፈራረሻ ስልቱ እንደሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ሁሉ ዐውቆ ፣ወያኔ ሆን ብሎ ከሚያጠምደው የራስ በራስ መጠፋፋት ተግባር ራሱን ሊቆጥብ ይገባል ብለን እናምናለን። ይህ ሰሞኑን ወያኔ ሆን ብሎ በሶማሌና በኦሮሞ ነገዶች መካከል የለኮሰው ብጥብጥ ፣ ከገጠመው ሕዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ የሕዝቡን የትብብር እንቅስቃሴ ለማዳከምና ሕዝባዊ አመጹን በሚሻው መልኩ ለማጨናገፍ ፣ የትግሉን አቅጣጫ ለማሳትና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ያጠመደው ወጥመድ … [Read more...] about ግድያ፣ ሥቃይና መፈናቀል በእኛ ይቁም!
Opinions
የኔ ሃሳብ
ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
የአዘጋጆቹ ማስታወሻ፤ ባለፉት ዓመታት ከህወሓት እየኮበለሉ የወጡ የቀድሞ አባላት በርካታ ናቸው። እንዳንዳቸው የሚወጡበት ምክንያት ቢኖራቸውም ህወሃትን በማጋለጥና ማንነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ የአቶ ገብረመድኅን አርአያን ያህል ታላቅ ሥራ የሠራና መስዋዕትነት የከፈለ አለ ለማለት ያስቸግራል። አብዛኛዎቹ የቀድሞው አባላቱ የህወሓትን ምሥጢራዊ አሠራር እና እጅግ አረመኔያዊ ግፍ፤ ኤፈርት በኢትዮጵያ ሐብት ላይ የፈጸመውንና እስካሁንም እየፈጸመ ያለውን የኢኮኖሚ ግፍ፣ ዝርፊያ፣ ሌብነት፣ … የመሳሰሉ ጉዳዮች በአደባባይ ከመናገር ሲቆጠቡ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በህወሓት ከፍተኛ አመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ አባላት ቢሆኑም፤ ኤፈርትም ሲያስተዳድሩ የቆዩ ቢሆኑም ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ አባይ ጸሐዬ ወይም ስብሃት ነጋ ከሚሰጡት ምላሽ ያልተለየ ሆኖ ተገኝቷል። አቶ ገብረመድኅን … [Read more...] about ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው! ህወሓትና ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዓላማው!
መስከረም፣ መስከረም
ኢዮሃ አበባዬ / መስከረም ጠባዬ ኢዮሃ አበባዬ / መስከረም ጠባዬ ... የወራት ሁሉ ቁንጮ መስከረም። ግንቦት እሳት፣ ሰኔ ውኃ ነው። የኢትዮጵያ ምድር በእሳትና በውኃ ሳትጠመቅ እረፍት እና ልምላሜዋን አታጋራም። ከግንቦት ማብቂያ እስከ መስከረም መጀመሪያ ሦስት ወር ብቻ ቢሆንም፣ እስኪጠባ መጠበቁ ሦስት ዓመት ያስመስለዋል። የመከራ አንዱ ቀን እንደ ዘላለም ነው፤ እግሮቹም በብረት ሰንሰለት ከብደዋል። ደስታ ግን ክንፍ እንጂ እግር የለው። ግንቦት ድርቅና ብክነት ነው። መስከረም እረፍትና ልምላሜ። ወራት መኳንንት ቢሆኑ መስከረም ንጉሥ ነው። መስከረም ደጅ ያስጠናል። ደጁን ካልከፈተ፣ ፊት ከነሳ ጥቅምትን ማየት አይቻል። አስራ ሁለቱን ወር እንደ ምን ተንፏቆ የደረሰ፣ አምስት እና ስድስት ቀን ጨምሮ ደጅ ይጠናል፤ ራሱንና ጓዳውን እንዲያዘገጃጅ ይገደዳል። ይህን ያህል ርቀት ተጕዘው … [Read more...] about መስከረም፣ መስከረም
Open Letter to Columbia University Faculty and Students:
Dr Tedros Adhanom: A TPLF central committee member, a criminal who is leading the WHO will be a keynote speaker at the Columbia University World Leaders Forum to be held on September 19, 2017 at Casa Italiana, 1161 Amsterdam Ave., New York. Dr Tedros Adhanom has been and still is a member of a killing, torturous and genocidal regime that has perpetrated crimes against humanity in Ethiopia. For the past twenty-six years, a regime controlled by his party,the Tigrayan People’s Liberation Front … [Read more...] about Open Letter to Columbia University Faculty and Students:
Ethiopia: Addressing the alarming conflict in the border areas of Oromia National Regional State and Ethiopia’s Somali Regional State
Press Release (September 14, 2017) Your Excellences, The General Assembly of the United Nations United Nations Human Rights Council African Commission on Human and Peoples Rights The Subcommittee on Human Rights of the European Parliament Association for Human Rights in Ethiopia (AHRE) writes to draw your attention to the alarming conflict in the border areas of Oromia National Regional State and Ethiopia’s Somali Regional State that has led to grave violations of human rights; and to call … [Read more...] about Ethiopia: Addressing the alarming conflict in the border areas of Oromia National Regional State and Ethiopia’s Somali Regional State
Ethiopia Needs Its Elders and Trusted Leaders to Help Stop the Cycles of Violence and Revenge in Our Communities and to Bring Us Together!
FOR THE SAKE OF OUR CHILDREN! Ethiopia Needs Its Elders and Trusted Leaders to Help Stop the Cycles of Violence and Revenge in Our Communities and to Bring Us Together! Press Release Washington, D.C, September 14, 2017--We in the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) strongly condemn the horrific and inhumane murder of 32 or more Ethiopian civilians in the Somali and Oromo regions of Ethiopia. Shocking reports of unbelievable brutality and cruelty to the victims on both sides … [Read more...] about Ethiopia Needs Its Elders and Trusted Leaders to Help Stop the Cycles of Violence and Revenge in Our Communities and to Bring Us Together!
አጽማቸው የፈለሰው የመላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ የአምስቱ ዘመን ተጋድሎ
የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን(ዮሐ 3፡11) ዓለም እንደሚያውቀው የጣሊያን ጦር በአድዋ ጦርነት እጅግ በሚያሳፍር ቅጣት ተቀጥቶ ከኢትዮጵያ ምድር መውጣት ለመላ አውሮጳ የሐፍረት ማቅ መከናነብ ምክንያት ሆነው። በዚህ ታሪካዊ ውርደት የተሸማቀቀው ጣሊያን፤ ዘመናዊ የምድርና የሰማይ ጦሩን ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ አደራጅቶ፣ኢትዮጵያን በጎሳ ሸንሽኖ በቋንቋ ለያይቶ እርስ በርሱ የማዋጋት ስልቱን ቀምሮ፣ አማራና ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የማጥፋት እቅዱን ዘርግቶ እንደገና በ1928 ዓ.ም. ወረረን። የመጀመሪያውን የክተት ጥሪ የሰሙ ኢትዮጵያውያን የየራሳቸውን መሳሪያ እየገዙና ሥንቃቸውን እያዘጋጁ ከሸዋ፣ ከወሎ፣ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከመካከለኛውና ደቡቡ ክፍል ወረራውን ለመመከት በማይጨው በኩል ዘመቱ። በተከዜ በኩል ከጎጃም ከቤገምድርና ስሜን ጣልያን መሰረቱን ወደ ጣለበት ወደ … [Read more...] about አጽማቸው የፈለሰው የመላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ የአምስቱ ዘመን ተጋድሎ
የቅማንት ጉዳይ!
ብዙ ወዳጆቼ ስለምንድን ነው የቅማንትን ጉዳይ ዝም ያልከው እያሉ በየቀኑ መልዕክት ይልኩልኛል፡፡ ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወው ቆጫት ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ጽንፍ ይዞ መሔዱን አማራጭ አድርጌ አላየሁትም፡፡ መሀል ሰፋሪ ለመሆንም አይደለም፡፡ ግና ዕውነታውን ይዘን ለሁሉም የሚበጀውን መከተል አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ እነኚህ ወዳጆቼ እንደሚሉት ዝም ብዬም አላውቅም፡፡ ነገርን ከሥሩ ውኃንም ከጥሩ እንደሚሉ ከሥር መሠረቱ ጉዳዪን መዘርዘር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ የቅማንትን ጉዳይ መከታተል የጀመርኩት በ2003/4 ዓም ጀምሮ ነበር፡፡ ይህም የተፈጠረበትን አጋጣሚ ከዚሁ ላይ መግለጹ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ አይከል ከተማ እሜቴ አይከል የምትባል ዛፍ አለች፤ የሚገባላት ብጻት ብዛት ይኽ ነው አይባልም፡፡ ምርጥ ምርጡን ገብስማ ዶሮ ከጊወን … [Read more...] about የቅማንት ጉዳይ!
ኢትዮጵያ ያለ”ኢትዮጵያዊነት” ልትኖር አትችልምን?
በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በጣም ተወዳጁ ኤፍኤም ሬዲዮ ሸገር ነው ቢባል የሚያጣላን አይመስለኝም። ሸገር መፈክሩ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፖለቲከኞችም ይህንኑ መፈክር የንግግራቸው ማሳረጊያ ዓረፍተ ነገር እያደረጉት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከመግለጫዎቹ ግርጌ “ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር” የሚል ዓረፍተ ነገር ያስቀምጣል። አዲሱ በእነሰይፉ ፋንታሁን እና ሠራዊት ፍቅሬ… የተከፈተው ኢትዮ ኤፍኤም ሬዲዮ “ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ” የሚል መፈክር ይዞ መጥቷል። በቅርብ ጌዜ ከተከፈቱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንዱ – ጄቲቪ – መፈክሩ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት” የሚል ነው። “ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ዘፈን የአገር ውስጥ ሽያጭ ሪከርድ ሰብሯል። የሐበሻ ቢራ ማስታወቂያ ‘ኢትዮጵያዊነት’ የሚለውን ቃል ማዕከል ያደረገ እና ስለኢትዮጵያ ‘ገናና ታሪክ’ የሚያወሳ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ያለ”ኢትዮጵያዊነት” ልትኖር አትችልምን?
ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል
የህወሃት አገዛዝ 2010 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ለማክበር የጀመረውን ከባህሪው የወጣ ድርጊት ተመልክተው አንዳንዶች ስርዓቱ እውነተኛ የመንግስትነት ባህርይን እየያዘ ነው ሲሉ ይደመጣል። እነዚህ የዋሆች ሰሞኑን ከነሀሴ 26 ቀን ጀምሮ የፍቅር ቀን፣ የእናቶችና ህፃናት ቀን፣ የአረጋውያን ቀን፣ የሰላም ቀን፣ የንባብ ቀን፣ የአረንጓዴ ልማት ቀን፣ የመከባበር ቀን፣ የሀገር ፍቅር ቀን፣ የአንድነት ቀን እና የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ መለያዎች አዲሱን ኣመት ለመቀበል ህወሀት የያዘውን ፕሮግራም እንደ አንድ ማስረጃነት ሲጠቅሱ ይታያል። ታርሟል በሚል። መሬት ላይ የምናያቸው የስርኣቱ ባህርያት በምክንያት ለገመገመ ሰው ግን ስርዓቱ ለመሻሻል ፍላጎት እንደሌለው ይገነዘባል። በእኔ ምልከታ ችግሩ ከድርጅቱ ፍጥረታዊ ባህርይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ ህወሀት ከምስረታው ጀምሮ … [Read more...] about ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል










