በ2012 በኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ነው። አቶ መለስ በጠና ታመዋል የሚለው ዜና ተንጠባጥቦ መሰማት ከጀመረበት ከጁላይ 15 ጀምሮ በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ መናወጥ ተጀመረ። ነዉጡ አላቆመም። አሁንም ቀጥሏል። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about አቶ መለስ ዜናዊ የ2012 ታላቅ ኢትዮጵያዊ ይሁኑን?
Opinions
የኔ ሃሳብ
የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት
በዓለም የተበተንነው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በጣም ብዙ ነው። አሁንም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ዓለም ለመውጣት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖቻችን ቁጥር ቀላል አይደለም። በውጭ የምንኖረው፤ በየምንኖርበት ሀገር፤ የሀገሩን ዜግነት በተለያዬ ምክንያት የወሰድንና ያልወሰድን አለን። ይኼ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን፤ እኔም ሆንኩ እኔ የማውቃቸው ኢትዮጵያዊያን፤ ሀገራችን በልባችን ቋጥረን ነው የምንጓዘው። እኔ ቁጥሬ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ጊዜ ተወልደው አድገው፣ የንጉሠ ነገሥቱን አገዛዝ ኋላ ቀር ነው ብለው ተቃውመው፣ በደርግ ጊዜ ግብግብ ገጥመው፣ አሁንም የወያኔን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ በመቃወም ከሀገር ውጪ ካሉት ወገን ነው። በአስተዳደጋችን ሆነ በእምነታችን፤ ሀገራችን ከማንም ሀገር አሳንሰን ተመልክተን አናውቅም። የገዢዎቻችን ተግባር እንጂ፤ የሀገራችን ጉዳይ ላንዳፍታም እንኳ ጥያቄ ውስጥ … [Read more...] about የጄራርድ ዲፓርዱ የሩሲያዊ ዜግነት ጥያቄና ሀገር ማለት
የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች
1. መግቢያ የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን ህልፈተ-ህይወት ተከትሎ በኢህአዴግ እና በተቃዋሚ ኃይሎች የሚታየው የመረበሽና ትርምስምስ በመሰረታዊነት ምንጮቹ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቢሮክራሲያዊ ስልጣኖችን በአጠቃለለ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ በእጃቸው ማስገባታቸውና በእሳቸው ህልፈተ-ህይወት ምክንያት የተከፈተውን የስልጣን ክፈተት የሚሞላ ተቋማዊ አቅም አለመገንባቱና ሁለተኛ ግለሰብ በስርአቱ ውስጥ አለመኖር ናቸው:: ስለዚህም በእርሳቸው ህልፈተ-ህይወት የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት... (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች
የማፍረስ አባዜ
በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም፡፡ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ፣ መቃብሮችን ማፍረስ፣ የንግድ ድርጅቶችን ማፍረስ፣ ትምህርት ቤቶችን ማፍረስ፣ … ማፍረስ… ማፍረስ… ማፍረስ! ሳያለቅሱ … [Read more...] about የማፍረስ አባዜ
አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
ኅዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሥራ ጉዳይ ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ለሁለት ቀን ተኩል የሚበቃኝን ሸክፌ ከመሥሪያ ቤቴ በተመደበልኝ መኪና ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ለሚነሳው በረራ ለመድረስ ወደቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ላይ የተደረደሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት አቀባበል ወይንም ሽኝት የሚደረግለት ባለሥልጣን/እንግዳ እንዳለ ስለጠቆመኝ መንገዱ ሳይዘጋ ቦሌ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርግ ለሹፌሩ ጠቆምኩት፡፡ ብዙም ሳንጓዝ አትላስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ላይ ስንደርስ በስፍራው የነበሩት የትራፊክ ፖሊሶች ወደ ቺቺንያ ወይንም ወደ ቦሌ ሩዋንዳ የሚወስደውን መንገድ እንድንጠቀም አስገደዱን፡፡ ወዲያውኑ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ ለሰባት … [Read more...] about አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የወያኔን ቡድን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገው ትግል አሁንም ቀጥሏል። ይህ ትግል አንድነት የለውም። ይህ ትግል አንድ ማዕከል የለውም። ይህ ትግል አንድ መሪ የለውም። ያለንበትን መርምረን ወደፊት እንዴት እንደምንሄድ መወያየት አለብን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ በኔ በኩል መደረግ አለባቸው የምላቸውን እጠቁማለሁ። ይቺ ሀገር ያንቺም፣ ያንተም፣ የነሱም፣ የኛም የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ሀገር ናት። ስለሆነም ሁላችንም ለወደፊቷ እኩል ባለጉዳዮች ነን። ማንም የነገዋን ሀገራችን እድል ሲወስን፤ እኛ የበይ ተመልካች መሆን አይገባንም። “ከወያኔ የተሻለ እስከመጣ ድረስ እኔ ምን ቸገረኝ!” ብለን ለሌሎች ጉዳዩን የምንተወው ሊሆንም አይገባም። አዎ የሚሻል ይኖራል። ያባሰም አለ። የሚሻለውም ሆነ የባሰው ሲመጣ የራሱን አጀንዳ ይዞ ስለሆነ የሚመጣው፤ እኛም ሆነ የሀገራችን ጉዳይ … [Read more...] about የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።
“ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች እንደሁ ብቻ ነው። (ሙሉው ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ
እንደማንኛውም የአሜሪካ ኅብረተሰብ ሁሉ፤ በኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን፤ ማንኛውንም ምርጫ ከራሳችን ጥቅም አንፃር መመልከቱ ለሕልውናችን አስፈላጊ ጉዳይ ነው። እናም የ2012 ዓመተ ምህረቱን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ምርጫ የምንመለከተው፤ ከዚህ ተነስተን ነው። እኛ ምን ሠራን? ምን ተጠቀምን? ምን ተጎዳን? ምን አገኘን? ምን ቀረብን? ምን ማድረግ ነበረብን? በመጨረሻ ደግሞ፤ ምን ትምህርት ወሰድን? ይህ ነው ለምርጫው ግምጋሜ ጠቅላላ ይዘቱ፤ ከኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን አንፃር ሲታይ። የባራክ ኦባማ ከጥቁር ዝርያ መሆኑ ወይንም የሚት ራምኒ ነጭ መሆን ቦታ አልነበረውም። የዴሞክራቲክ ፓርቲው ማቸነፍ ወይንም የሬፑብሊኩ ፓርቲ መቸነፍ፤ ለኛ ትርጉሙ በፓርቲነታቸው ሳይሆን፤ የኛን ጉዳይ በሚመለከት ባላቸው አቁዋም ነው። በአሜሪካን ፓርቲ ስሌት ደግሞ፤ የምንፈልገውን ለማግኘት፤ የሚተማመኑበት የአንድ … [Read more...] about ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ
Leveling the playing field in Ethiopia
The press release was short and to the point. It was only six paragraphs long and was written in a matter of fact way. There were no trumpets blaring, no press conference with TV lights and no lavish dinner to commemorate the event. The announcement reminded me of the proverb ‘best things come in small packages.’ So it was without much fanfare I read the most important announcement on Abbay Media and Quatero. Tucked among the news was the announcement regarding the formation of Ginbot 7 Popular … [Read more...] about Leveling the playing field in Ethiopia
በአሜሪካ የ፳፮ ሕፃናትና መምህራን ግድያና ግንዛቤዬ
የምኖረው አሜሪካ ነው። አርብ ዕለት በከነቲከት ስቴት፣ ኒውታውን በምትባል ከተማ፤ ሳንዲ ሁክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ፤ ፳ የስድስትና የሰባት ዓመት የአንደኛ ክፍል ተማሪ ሕፃናትና ስድስት መምህርቶቻቸው በትምህርት ቤታቸው ተገደሉ። የተገደሉት የእናቱን መሣሪያዎች አንግቶ፤ መጀመሪያ እናቱን ከተኛችበት ገድሎ፣ የትምህርት ቤቱን መጠበቂያ ጥሶ በገባ የሃያ ዓመት ጎረምሣ ደጋግሞ በረፈረፈባቸው ጥይቶች ነበር። አሜሪካ ከላይ እስከ ታች በዚህ ኢሰብዓዊ ተግባር ተርገበገበች። ከዩጋንዳ ለሐዘኑ መልዕክትና ማስታወሻ ተላከ። ከቦዝንያ፣ ከአውስትራሊያ፣ በጠቅላላው ከዓለም ዙሪያ የሀዘን መግለጫዎች ጎረፉ። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በቦታው በመገኘት የስነ ሥርዓቱ ተካፋይ ሆነው፤ የሀገሪቱን አጠቃላይ የሀዘን ትብብር ለሙታን ወላጆችና ለከተማው ነዋሪዎች አቀረቡ። እኔም የዚሁ ሀገር ነዋሪ ሆኜ ጉዳዩን … [Read more...] about በአሜሪካ የ፳፮ ሕፃናትና መምህራን ግድያና ግንዛቤዬ







