የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሐምሌ 11,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባዊ ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡ በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮች ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን … [Read more...] about አንድነት ተጨማሪ ህዝባዊ ስብሰባ የሚካሄድባቸውን ከተሞችና ቀናት ይፋ አደረገ
Right Column - Primary Sidebar
ፍልስፍና አልባ የሆነ ፖለቲካ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል
ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በብዙ አፍሪካ አገሮች የሚታየው የአስተዳደር ብልሹነት፣ የህዝቦች ኑሮ መዘበራረቅና ዓላማ-ቢስ መሆን፣ እንዲያም ሲል በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በሃይማኖትና በጎሳ አሳቦ ርስ በርሱ እንዲጠላላ ማድረግና፣ የመጨረሻ መጨረሻም ወደ ርስ በርስ መተላለቅ እንዲያመራ መንገዱን ማዘጋጀት፣ በተራ አነጋገር ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከአምባገነናዊ አስተዳደር መስፈንና ከዲሞክራሲ አለመኖር ጋር ሲያያዝ ይታያል። አንዳንዶች እንዲያውም እንደዚህ ዐይነቱን ዓላማ-ቢስ የህብረተሰብ ጉዞ የአፍሪካ መሪዎች ወይም የጥቁር ህዝብ ችግር አድርገው የሚመለከቱ አሉ። በእርግጥ ለአንድ አገር ስርዓት ባለው መልክ መተዳደርና፣ ህብረተሰቡም በዕቅድና በዓላማ እንዲመራ ከተፈለገ በዚያ የሰፈነው አገዛዝ ህብረተሰቡን በማደራጀት ረገድ የሚጫወተው ከፍተኛ ሚና አለ። ጥያቄው ግን አንድ ህብረተሰብ … [Read more...] about ፍልስፍና አልባ የሆነ ፖለቲካ የአንድን ህብረተሰብ አስተሳሰብ ያዘበራርቃል
ቤተልሔም ፕላዛና ደብረወርቅ ታወር አገልግሎት እንዳይሠጡ ተከለከሉ
(ከጎልጉል አዘጋጅ - ለመስታወቱ ብቻ ቤተልሔም 9ሚሊዮን ብር ደብረወርቅ ደግሞ ከ15ሚሊዮን ብር በላይ አውጥተው እዚህ እስኪደርስ ድረስ የከንቲባ ኩማ መስተዳድር የት ነበር? ላዲሱ ከንቲባ ድሪባ የከተማውን ቁልፍ ሲያስረክብ ይሆን?) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ የሆናቸው ሁለት ሕንፃዎች ደረጃቸውን አልጠበቁም በሚል ምክንያት የመጠቀሚያ ፈቃድ ከለከላቸው፡፡ሁለቱ ሕንፃዎች መገናኛ ድልድይ አካባቢ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛና ሜክሲኮ አካባቢ ከቡናና ሻይ ሕንፃ ፊት ለፊት የሚገኘው ደብረ ወርቅ ታወር ናቸው፡፡ ሁለቱ ሕንፃዎች የተጠቀሙበት የውጭ መስታወት አንፀባራቂ ነው በሚል ምክንያት አስተዳደሩ መስታወታቸው እንዲነሳ ማዘዙ ታውቋል፡፡ መገናኛ የሚገኘው ቤተልሔም ፕላዛ ባለ ሰባት ፎቅ ነው፡፡ ያረፈው በ800 ካሬ ሜትር ቦታ ነው፡፡ … [Read more...] about ቤተልሔም ፕላዛና ደብረወርቅ ታወር አገልግሎት እንዳይሠጡ ተከለከሉ
የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት
የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን … [Read more...] about የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት
ይድረስ ለተገፋው ወገኔ !. . .
ይድረስ ትናንተም ሆነ ዛሬ ግፍ በነገሰባት ምድር ኑሮን በመከራ ለምትገፋው ወገኔ ! ይድረስ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ በደል ለተጫነብህ ፣ ፍትህ ርትዕ ተዛብቶ የአስተዳደር ሚዛኑ ኑሮህን ላጨለመው ወገኔ ! ይድረስ ከዲስኩር ባላለፈ "የእድገት ስልጣኔ መንገድ እየተጓዝክ ነው " ለሚሉህ ፣ ይድረስ ግልጽነት በጎደለው "መልካም አስተዳደር" ለምትረገጠው ታጋሽ ወገን፣ ይድረስ ትናንትም ሆነ ዛሬ ከአብራክህ ወጥተው አንተን ያልሆኑ ፣ ህመምህ የማያማቸው፣ በደልህ በማይገባቸው የመንግስት ምስለኔ ልጆችህ እየተሰቃየህ ላለህው ! ይድረስ የግፍ በደል ቀንበር ከትከሻህ ላልወረደልህ፣ ስቃይ መከራው ላላባራልህ ይድረስ ለከልታማው ወገኔ! ይድረስ የአንድ ጎልማሳ እድሜን በጭቆና መግፋቱ እያመመህም ቢሆን ለቻለከው፣ በቁጣ አመጻን ከመግለጽ ተገትተህ ጎስቋላ ኑሮን በዝምታ፣ በይሁንታ እየገፋህ ላለህው … [Read more...] about ይድረስ ለተገፋው ወገኔ !. . .
በሕዝቡ ያልተመራ አመፅ፤ ሰላማዊ ቢሆንም ውጤቱ ሕዝባዊ አይሆንም
ሰላማዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጥሩ አቅጣጫ አመልካች ሰላማዊ ሰልፍ ግንቦት ፳ ፭ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ በማድረግ፤ የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎት ባደባባይ አሳዬ። ይህ ታሪካዊ ነው። ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎች መጪ መሆናቸውንና አይቀሬነታቸውን አረጋገጠ። ካሁን በፊት ታጋዮች፤ በተደጋጋሚ፣ በየቦታው፣ ሰላማዊና የትጥቅ አመፅ በማድረግ ግባቸውን ለመምታት ጥረት አድርገዋል። በሕዝቡ ላይ በደል እስካለ ድረስ፤ አመፅ በተለያዬ መልክና በተለያዩ ቦታዎች መቀጠሉ፤ የሕልውና ግዴታ ነው። ለዚህ ምስክር አያሻም። ሕዝባዊ ግቡ አንድ በሆነበት ወቅት ደግሞ፤ ለሕዝባዊ ግቡ የትግሉ አንድ መሆን፤ ግዴታ ነው። ማሳየት የፈለግሁት፤ ሰማያዊ ፓርቲ በጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ ተነሳስትን፤ አሁንም የተለያዬ ሰላማዊ ሰልፍና የተነጣጠለ ትግል እያካሄድን፤ ሕዝባዊ ድል ለማግኘት ማሰብ የትም እንደማያደርሰን … [Read more...] about በሕዝቡ ያልተመራ አመፅ፤ ሰላማዊ ቢሆንም ውጤቱ ሕዝባዊ አይሆንም
Proving them wrong – the Ethiopian way.
They say all kinds of bad stuff about us. It is said so many times and so often sometimes some of us start to believe the lie. That is always the problem with being lied to. I am sure by now Woyanes are drunk with their own silly propaganda. The situation with us is that they used to own the means of communication and we were their potted plants waiting to be told, lectured and abused to no end. I have so many instances of this situation I just don’t know where to start. I believe 2005 is day … [Read more...] about Proving them wrong – the Ethiopian way.
ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ
መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም "በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም!" አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia's unemployment "በኢትዮጵያ ስራ አጥንትን ለመሸሸ " ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል ። በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ሽህ ዶላር ያበድራል ተብሎ … [Read more...] about ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ
Broken Wings
Ethiopian poetry with integrity and courage Ethiopian poet Yilma Tafere Tasew fled his country in 1991, angryat the constant violation of human rights and fearing for his life. He struggled to survive in refugee camps in Kenya until 1997, when he was invited by the UNHCR (the United Nations refugee agency) to work for the social and community services section in Nairobi. (Please click here to read more and see the poster) … [Read more...] about Broken Wings
ዲሲ 2013
ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። "ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።" ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ በመሆንዋ ታሪኳን ጠለቅ እያልን ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ሊወሳሰብ ስለሚችል እጅግ ብዙ ጥናት ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ጸሃፊው ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር የሚጽፈው ጠፍቶት ሳይሆን ግራ ተጋብቶ መጻፉን ያቆማል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ዲሲ 2013










