ዛሬም እንደሳምንቱ መብታችንን እያሉ ኢትዮጵያዊያን በየመስጊዱ ተሰብሰበዋል። በየቀኑ በየቤተክርስትያኑ ጸሎታቸውን ያደርሳሉ። በየትምህርት ቤቱ በራቸው ተንኳኩቶ እንዳይወሰዱ ተደብቀው ያጠናሉ። መምህራን በፍራቻ፤ ለተማሪዎቻቸው ሳይሆን ለካድሬዎቹ ይሽቆጠቆጣሉ። አርሶ አደሮች ለሚያርሱበት መሬት፣ ለማዳበሪያና ለካድሬ ሲሉ አንገታቸውን ደፍተዋል። ላብ አደሮች የሥራ ዋስትና አንገታቸውን አንቆ ወገባቸውን አጉብጦታል። ነጋዴዎች ከኤፈርት ጋር ውድድሩ ራቁታቸውን አስቀርቷቸዋል። ጋዜጠኞች ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እኔ የምላችሁን ካላደረጋችሁ ተብለው እስር ቤቱን ሞልተውታል። ማን ተርፎ? የፖለቲካ ምኅዳሩን ማነቆ የጨበጠው መንግሥት አምልኩኝ ብሏል። ሀገራችን ባለችበት የፖለቲካ ሀቅና እኛ አሁን ባለንበት ድንዘዛ፤ አንድ የሚያነቃ ብራቅ ብልጭ ሊልብን ይገባል። የአንድነት ውይይት የግድ ነው። ይቺ ሀገራችን … [Read more...] about በውጭ ያለነው ኢትዮጵያዊያን ምርጫዎች አሉን
Right Column - Primary Sidebar
ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
አሁን ላይ በሐገራችን የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃዎች የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ጨምሯል፡፡ በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርትን በነባርና አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች በኩል ትምህርታቸውን ተከታትለው እየተመረቁ የሚወጡ ተማሪዎች (ምሩቃን) ቁጥር በዚያው ልክ እያደገ ይገኛል፡፡ በዚህ አመት ብቻ እንኳ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተመራቂዎች ቁጥር ከ60 ሺህ በላይ እንደሆነ ይፋ ሆኗል፡፡ ይህ ቁጥር በግል ኮሌጆችና በተለያዩ መለስተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የተከታተሉትን አይጨምርም፡፡ የትምህርት ተቋማትም ሆነ በእነዚህ ተቋማት ገብተው ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ቁጥር መጨመሩ ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ተማሪዎች በምን ሁኔታ ትምህርታቸውን ተከታትለው እንደሚወጡ ሲታይና ከምረቃ በኋላም ያለውን የሥራ ጊዜ … [Read more...] about ምርቃት ወዲህ ሥራ ወዲያ
ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጥፋት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ!!!
ዛሬ እውነት እውነቱን እንቅጭ እንቅጩን እንነጋገራለን፡፡ እንዴ! ይሄ ሰው ከዚህ ቀደም ሲያወራልን የኖረው ቅጥፈት ነበር እንዴ? እንዳትሉ፤ አለ አይደል ይሄ መፏከቱን መሸራደዱን መበሻሸቁን ትተን እንደ ባለ አእምሮና ኃላፊነት እንደሚሰማው ዜጋ በንጹሕ በቅዱስ ልቡና ልዕልና ያለውን ሐሳብ አንሥተን እንወያያለን ለማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ዐይነ ሕሊናችንን ያብራልን እዝነ ልቡናችንን ይክፈትልን አሜን!! ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘውግ ፖለቲካ (እምነተ-አስተዳደር) ወይም ብሔር ተኮር የሆነ ከፋፋይና አጥፊ የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ በግዳጅ እንድትዘፈቅ ከተደረገች 24ኛ ዓመታችንን ይዘናል፡፡ በዚህ ዘመን ውስጥ አንድነት የነበረው ሕዝብ በግድ ካልተነጣጠልክ፣ በጎሪጥ ካልተያየህ፣ እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ሁሉ ለእኛ ለእኛ ሳይሆን ለእኔ ለእኔ (ለብሔረሰቡ ብቻ) ካላልክ ተብሎ እየተወተወተ ወዶ … [Read more...] about ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጥፋት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ!!!
Center for the Rights of Ethiopian Women (CREW) Fundraising Event
አራዊታዊ መንግሥታት
አራዊታዊው ኢሀደግ እና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ዶክተር ቀሲስ አማረ ካሣየ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አባ ኃ/ሚካኤል የሰጡት መግለጫ፦ በአገራችን ላይ ክፉ ዘመን የወለደው አራዊታዊው መንግሥትና የየመን መንግሥት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸሙት አራዊታዊ ተግባር በፈጣሪና በፍጡሩ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው፤ የሰው ጥንተ ጠላት የሆነው የሰይጣን ተግባር ስለሆነ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን የሚወገዝ ነው። ሕዝባችንም የዜግነት ከለላ ከሰጣቸው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋራ በመተባበር አቶ አንዳርጋቸውንና በተመሳሳይ አራዊታዊ አደና የተያዙትን ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለማስለቀቅ የጀመረውን ጥረት አስፈላጊ በሆነው ሁሉ መንገድ እንዲቀጥል እግዚአብሔር የሚቀበለውና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም … [Read more...] about አራዊታዊ መንግሥታት
የጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደም እንባ!
የእስራኤል የ10 ቀናት የአየር ድብደባ ከ220 በላይ ፍልስጥኤማውያን የጋዛ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በሚወሰደው ዘመቻ ነገን ላያዩ መቀጠፋቸውን እየሰማን ነው: (ከአንድ ሽህ በላይ የዘለቁ በጠና የቆሰሉትን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉት ዜጎችን መከራ እያየንም ነው። እኒህኞቹን በራሳቸው ሀገር ስደተኛ የሆኑትንማ ፍዳ ማየቱ ከሞቱት በላይ ያማል። ሰቆቃው በዚህ ቢያቆም መልካም ነበር ፣ ግን አልሆነም ። በሳምንቱ መጀመሪያ የፍልስጥኤማውያን ሃማስ የጦር ክንፍ ሰው አልባ ሚጢጢ አውሮፕላን Drone ...በእስራኤል ሰማይ መስፈንጠሩን አስታወቀ። ይህም የሃማስን የሚሳኤል ሮኬት ውንጨፋ ለወረራው ምክንያት ላደረጉት እስራኤሎች ከስጋት ባለፈ ጥሩ የመልሶ ማጥቂያ ምክንያት ሆነና ነገሮችን ሁሉ በፍጥነት መቀያየር ይዘዋል። ብቻ ...ዛሬ ሃሙስ ለአርብ በደረቁ ሌሊት የደረሰን ሰበር ዜና አስራኤል … [Read more...] about የጋዛ ፍልስጥኤማውያን የደም እንባ!
ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍ/ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑ ተገለጸ
በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡ ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 … [Read more...] about ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍ/ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑ ተገለጸ
አኖሌ ሃውልት ፖለቲከኞችና የታሪክ ምሁራንን እያወዛገበ ነው
በምኒልክ ዘመን በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ተፈፅሟል የተባለውን የጡትና እጅ መቁረጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና ጭፍጨፋ ለማስታወስ በሚል በአርሲ አኖሌ አካባቢ በ20 ሚሊዮን ብር የተሰራው ሃውልት፣ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ጨምሮ በርካታ የኦህዴድ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል፡፡ ሃውልቱን ያሰራው አካል ያለፈን ታሪክ መዞ ቂም በቀልን ለማውረስ ሳይሆን ቀጣዩ ትውልድ ከአስከፊው ድርጊት እንዲማርና ወደፊት ድርጊቱ እንዳይደገም ነው ሃውልቱ የተገነባው ብሏል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ምሁራን በበኩላቸው ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ አንደኛው ወገን ሃውልቱ በህዝቦች መካከል ቅራኔና ቂም በቀል የሚፈጥር ነው በማለት ሲቃወም ሌላው ወገን በበኩሉ ድርጊቱ ዳግመኛ እንዳይከሰት መማርያ እንጂ የበቀል አይደለም ሲሉ የሃውልቱን መቆም ይደግፋሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ … [Read more...] about አኖሌ ሃውልት ፖለቲከኞችና የታሪክ ምሁራንን እያወዛገበ ነው
ወግ ቀማሪው ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም አረፉ
ከአቶ ሀብተማሪያም ሞገስና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም በ 71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ። ደራሲ መስፍን በልጅነታቸው ባህላዊ የቤተ ክህነት ትምህርት የተማሩ ሲሆን ፣ በሞጆና በአንቦ የአንደኛና የሁለተኛ ደራጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ተብሎ በሚጠራው የትምህርት ተቋምም በመግባት በቋንቋዎችና ሥነ-ፅሁፍ ክፍል በማዕረግ በቢኤ ዲግሪ ተመርቀዋል።በመቀጠልም ካናዳ በሚገኘው ቫንኩበር ከተማ በመሄድ ዪኒቨርስቲ ብሪቲሽ ኮሎምብያ ገብተው የፈጠራ ሥነ- ፅሁፍ የማስተር ድግሪ አግኝተዋል። ደራሲ መስፍን ሀብተማሪያም አገራቸው ከተመለሱ በኋላ በአማርኛ ቋንቋ በኢልብወለድ አጻጻፍ የትምህርት መስክ በተለያዩ ቦታዎች አስተምረዋል በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲም በቋንቋዎች ጥናት ተቋም የስነጽሁፍ ኮርሶችን … [Read more...] about ወግ ቀማሪው ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም አረፉ
የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!
ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች” በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ … [Read more...] about የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!










