ዶ/ር ዳንኤል ተፈራና ዶ/ር ፀሀይ ለኢሳት ጋዜጠኛ ለአቶ ፋሲል የኔ ዓለም ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ለሰጧቸው መልሶች የቀረበ አስተያየት ከፈቃዱ በቀለ መግቢያ በቅርቡ ሁለት በአሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚስቶችን የኢሳት የቴሊቪዝን ጋዜጠኛ የሆነው አቶ ፋሲል የኔ ዓለም ኢትዮጵያ ከውጭ የምትበደረው ብድር መጠን እያደገ ስለመምጣቱና ስለኢኮኖሚው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በመጋበዝ በመሰላቸውና በሚታያቸው፣ እንዲሁም ከተማሩት የኢኮኖሚ ትምህርት አንፃርና ከዕምነታቸው በመነሳት ለተደረገላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል። ፕሮፊሰር ዳንኤል ዕዳንንም ሆነ፣ የሚሰሩትን ፕሮጅክቶች ወደ ፊት ሊገኝ ከሚችለው ውጤትና አትኩሮ ቅድሚያ መስጠት የሚገባውን፣ ነገር ግን የሚታለፈው አንገብጋቤ ጥያቄ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት በንጽጽር … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ ነው ወይስ የኋሊት ጉዞ እያሳየ ነው?
Right Column - Primary Sidebar
ሰይፈ ነበልባል ክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ
መግቢያ በዚህ ርእስ ይህችን ጦማር እንዳዘጋጅ የተገደድኩበት ምክንያት “የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ በመሆኔ ለቤተ ክርስቲያኔ እቆማለሁ፤ ጋዜጠኛ በመሆኔም ለህዝቤ እውነቱን አስጨብጣለሁ” እያሉ፤ ነገር ግን እንደሚሉት ሆነው የማይገኙ እንደ አቶ አዲሱ አበበ የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች በመካከላችን ስለተከሰቱ ነው። አቶ አዲሱ እንደሚሉት የክርስትና ሕይወትና የጋዜጠኝነት ሙያ የተዋሀዳቸው ቢሆኑ ኖሮ እጅግ በታደልን ነበር። እንደነ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋና ርዕዮት ዓለሙን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች ታስረው በመሰቃየት ላይ ሳሉ፤ በቂ ችሎታና ሙያ ሳይኖራቸው አቅጣጫ እየቀያየሩ በሚፈጽሙት ተደጋጋሚ በደል በአካባቢያችን ያሉትን አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ባልወረሩና ወያኔ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ አውታሮች ተሰልፈው የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያፈኑ ጋዜጠኞች ቁጥራቸው ባልበዛ … [Read more...] about ሰይፈ ነበልባል ክርስትና እና ጋዜጠኝነት ሲወሀዱ ወደ ሰይፈ ነበልባልነት ይለወጣሉ
አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ ! * ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን! ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette ነው። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ፣ መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን? እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም! መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ … [Read more...] about አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም?
“እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
ከቂሊንጦ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አብርሃ ደስታና የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ኦኬሎ አኳይ፣ ስለ እስራቸው ሁኔታ እንዲህ ይላሉ:: በቅድሚያ አብርሃ ደስታ:- "እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡ "ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ "እኔ እስር ቤት እንድገኝ … [Read more...] about “እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም” አብርሃ ደስታ
“መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም
ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት መንግስት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ የተከሰተውን ስቃይ እና በደል ተከትሎ ለስራ ወደ አረብ ሀገራት በሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል። በተለይ ያለአንዳች የህይወት ዋስትና ወደ ተጠቀሱት ሃገራት በኮንትራት የሚሄድ ሰራተኞችን ከገጠር እስከ ከተማ በዘለቀ ድለላ ህጋዊ ፈቃድ አግኝተው ዜጎችን እያጋዙ የነበሩ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ቢሮዎች መዘጋታቸው አይዘነጋም። ዘግይቶም ቢሆን መንግስት በወቅቱ ወሰደ በተባለው እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከአስከፊው የአረብ ዓለም ስቃይ መታደግ ቢችልም ከግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቻችንን ህይወት ስላለበት ሁኔታ የተጠቀሱትን የኤጀንሲ ባለቤቶች በህግ ለመሞገት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም የገቡትን ቃል … [Read more...] about “መንግሥት ከደላሎች ጋር አይደራደርም” ኃይለማርያም
በ5 ዓመቱ ሕፃን ላይ የግብረ-ሰዶም ጥቃት የፈፀመው በ20 ዓመት እሥራት ተቀጣ
አስራ ሦስት ዓመት ባልሞላው ሕፃን ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ፈፅሟል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተበት የ23 ዓመቱ ወጣት ሳሙኤል መርዕድ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ20 ዓመት እሥራት እንዲቀጣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ ታህሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈበት። ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎት በየካቲት 06 ቀን 2006 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ላይ እንደዘረዘረው፤ የ23 ዓመቱ ወጣት ከእርሱ ጋር አንድ አይነት ፆታ ባለውና ዕድሜው ከ13 ዓመት በታች በሆነው ታዳጊ ልጅ ላይ የግብረ-ሰዶም ጥቃት ለማድረስ አስቦ ተንቀሳቅሷል ይላል። በዚህም መሠረት በጥቅምት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02/03 ክልል ልዩ ቦታው ጌሾ ተራ ተብሎ … [Read more...] about በ5 ዓመቱ ሕፃን ላይ የግብረ-ሰዶም ጥቃት የፈፀመው በ20 ዓመት እሥራት ተቀጣ
“የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ
". . . ፖለቲካ ለሀገር ማሰብ ነው፡፡ ፖለቲካ መታደል ከተጨመረበት ለአገርና ውስጥዋ ለሚኖረው ለሕዝብ መልካም ለመስራት መጣር ነው፡፡ ከራስ በላይ ነፋስ በሚባለው ነገር አላምንም፡፡ ከራስ በላይ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ሰፈር፣ ወረዳ፣ አውራጃ ክፍለሀገርና አገር አሉ፡፡ የቻለበትም አህጉርና አለምን በልቦናው ይከታል፡፡ "የአገራችን አንድ የሚታይ ማንም የሚያወራበት ፀባይዋ በደሃና በተራራ የተሞላች መሆኗ ነው፡፡ አንድ ሰው በሀገሩ ደሃ መሆን የለበትም:: ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቹና መብቶቹ መጠበቅ አለባቸው፡፡ የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም፡፡ የለፉበት ውጤት በጥቂት ማንአለብኝ ባዮች ስለሚዘረፍ ነው፡፡ "እነዚህም ዘራፊዎች ዝርፊያቸውን ያለሀሳብ ለማካሄድ ማስፈራራትንና ራሳቸው ያወጡትን ህግ ይጠቀማሉ፡፡ ድሆች ወይም ጭቁኖች መብታቸውን ለማስከበር የሚነሱት ከወደቁበት … [Read more...] about “የድሆች መናጢነት የሚመጣው ሰነፍ ስለሆኑ አይደለም” አዳም ረታ
ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
ብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው! ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው። “መሬት ለአራሹ … [Read more...] about ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
ሱስ ትውልድና ሀገር!
በእኅታችን በሐና ላላንጎ ላይ ያ አደጋ በደረሰ ጊዜ ይሄንን ከባድ ዜና በለጠፉ ዋና ዋና ድረ ገጾች ላይ አንድ አስተያየት ሰጥቸ ነበር “ሆን ተብሎ በሱስ ትብትብ እንዲተበተብ ከተደረገ የዚህ አገዛዝ ትውልድ ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቃል? እንደ ማኅበረሰብ ወንድም እኅቶቻችንን እናም ልጆቻችንን ከዚህ የሱስ ማጥ ውስጥ ካልታደግን በስተቀር ገና ከዚህ የከፋ ብዙ ነገርም ያሰማናል ያሳየናል” የሚል፡፡ አንዳንዶቹ የአገዛዙ ደጋፊዎች አጋጣሚውን ሆን ብየ ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም የፈለኩ መስሏቸው አስተያየቴ ትክክል እንዳልሆነ ሲናገሩ አንዳንዶችም በመሳደብ ከአስተያየቴ ስር ምላሽ ሰጥተው ነበር፡፡ እኔ ግን ስም ለማጥፋትም አጋጣሚውን ለመጠቀምም አልነበረም፡፡ ያልኩት ነገር ለመሆኑ መረጃው ስለነበረኝ እንጅ፡፡ ወያኔ ፍጹም በደነቆረ አመክንዮና በጠላትነት ሰብእና ትውልዱን ሆን ብሎ በሱስ ማጥ … [Read more...] about ሱስ ትውልድና ሀገር!
STARTING THE CONVERSATION BETWEEN DIVERSE ETHIOPIANS IN MINNESOTA
SMNE FORUM SERIES II: MINNESOTA STARTING THE CONVERSATION BETWEEN DIVERSE ETHIOPIANS IN MINNESOTA CAN WE COLLECTIVELY OWN BOTH THE GOOD AND THE UGLY PARTS OF OUR PAST SO WE CAN BE FREE AT LAST FROM THE SHACKLES OF OPPRESSION? First of all, I would like to thanks Ato Girma Biru, all members and supporters of the SMNE in Minnesota for taking your time to organize this wonderful forum. Thank you for inviting me to speak to you on the topic of Starting the Conversation between Diverse … [Read more...] about STARTING THE CONVERSATION BETWEEN DIVERSE ETHIOPIANS IN MINNESOTA










