የትላንቱ እንቅፋት፣ ዛሬም ይመታናል የትላንቱ ገመድ፣ ዛሬም ይጠልፈናል ፤ ሰምተንም - አልሰማን፣ ሳሰማም ሰምተናል አይተንም - አላየን፣ ሳናይም አይተናል ላለመማር - መማር እኛ ተምረናል። አሁን… አሁን ''ከልሂቃኑ እስከ ኢ-ልሂቃኑ'' ድረስ፤ ቀድም ብሎ ሙሰላዊያንና ሂተለራዊያን፤ ካለፉት ሃምሳ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሻአቢያዊያንና ወያኔያዊያን እንዲሁም ኦነጋዊያን ከባንዳ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው የተቀበሉትን የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ ስላወሩትና የስልጣን ኮርቻውን ስለተፈናጠጡት፤ የሚንናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ እንድ ዕውነት ተቆጥሮ ፤ “በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም-በቀል አለ!" መባሉ ነው። ሌላውን ሁሉ ትተን ባለፉት 26 ዓመታት ብቻ ሻአቢያዊያን፣ ወያኔያዊያንና ኦነጋዊያን የሰሩትን ግፍና በደል፣ የዘሩትን ጥላቻና በቀል ብናስብ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ 'ርስ-በርሱ … [Read more...] about በ’ርግጥ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም በቀል አለ?
Right Column - Primary Sidebar
የትግሬ ወያኔ ወደ እውነተኛ ቁመናው ሲመለስ!
የግለስብ ሁለንተናዊ ቁመናው የሚገለጥ ከሚመጣበት መህበረሰብ አኳያ ነው። ግለስቦቹ ተቧድነው የሚፈጥሩትም ማህበርና ድርጂትም ላይ የዚያው ማህበረሰብ አሻራ አብሯቸው ይኖራል። ለምሳሌ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ማህበረሰቦችን በዚህ አኳያ መዳሰስ ይቻላል። ይህን ማህበራዊ እይታ ያፍሪካ ቀንድ ወስጥ የሰፈሩ የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚጋሩት ቢሆንም በሱማሌ፣ በኤርትራና በትግሬ ማህበረሰቦች መሀል ባያሌው የሚታየው በቤተሰባዊ (ክላን) አመለካከት ዙሪያ የሚታይ ማህበረሰባዊ መከፋፈል የላቀ ነው። በዚህ ረገድ ዛሬ ለነጻዪቱ ሱማሌ መበታትን ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ የህዝቧ በክላን ዙሪያ ያጠነጠነ አመለካከት በማደግ ላይ የነበረውን ሀገራዊ አመለካከት ስለደፈጠጠው ነው። ዚያድ ባሬ የኦክቶበር አብዮት ብሎ የሰየመውን የ1962ዓም የመፈንቅ ለመንግስት ሲመሰርት ዋና የአገዛዙ መመሪያ አድርጎ ያስቀመጠው … [Read more...] about የትግሬ ወያኔ ወደ እውነተኛ ቁመናው ሲመለስ!
የዘመናችን ሲኖድ የቱን ይመስላል?
በዚህ ዘመን ያለው ሲኖድ (ሸንጎ)የቱን ይመስላል? የዮቶርን ሸንጎ? የአርዮስፋጎስን ሸንጎ? ወይስ የክርስቲያኖችን የቱን ይመስላል? ይህንን ጥያቄ የፈጠረብኝ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተከሰተው ውዥንብር እንዴት ትመለከቱታላችሁ? በሚል ከህዝብ የቀረበ ጥያቄ ነው። በመጀመሪያ በዚህ ቅዱስ ስብሰባ ላይ ተሳሳቱ የተባሉ ወገኖች የሚታገዱበት የመነጋገሪያ አጀንዳ በሀራ ዘተዋህዶ ድረ ገጽ ተሰራጭቶ ተመለከትን። ቀጠለና አዲስ ተክል አባ ፋኑኤል በገንዘብ በገዙት ጵጵስና ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሰርገው ገብተው በየደረሱበት ህዝብ በማተራመስ ላይ እንዳሉ ከፓትርያርኩ አንደበት ተሰማ። በወቅቱ የቀረበውን ለመረዳት ከፈለጉ በቀይ ቀለም የተጻፈችውን ዓዲስ ተክል የምትለዋን ይጫኑ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) ቀሲስ አስተርአየ ታህሳስ 7 ቀን 2010 ዓ/ … [Read more...] about የዘመናችን ሲኖድ የቱን ይመስላል?
የኢትዮጵያ፤ የውይይትና መፍትሔ መድረክ መግለጫ
የሃገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን በተለይ ላለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይና በመረረ ሁኔታ መንግስታቸውን ሲቃወሙ ይታያል። እንዲህ ያለ በተከታታይና በቆራጥነት የተካሄደ ሕዝባዊ ተቃውሞ በሃገራችን ታሪክ አልታየም። ገበሬዎች ሰልፍ ወጥተው “የህወሓት አገዛዝ በቃን” እያሉ ነው። የትናንሽ ከተማ ነዋሪዎች በነቂስ እየወጡ በመረረ ሁኔታ ሲጮሁ ይሄው ሶስት ዓመት ሆነ። ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አየወጡ ለውጥ እንፈልጋለን ሲሉ ይታያል። ነጋዴው ሱቁን እየዘጋ ተቃውሞውን ያሰማል። ኢትዮጵያውያን ያለ ልክ ለውጥ የፈለጉ መሆናቸውን የሚያሳይ መራራ ተቃውሞ በሃገሪቱ በሰፊው በየቀኑ ይታያል። ይሁን እንጂ ተቃውሞ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የመንግስት ታማኝ ወታደሮች፤ በተለይ አጋዚ፤ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ታጣቂዎች፤ ደህንነት በሚወስዱት ግብታዊ ርምጃ … [Read more...] about የኢትዮጵያ፤ የውይይትና መፍትሔ መድረክ መግለጫ
ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ? የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዝቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ … [Read more...] about ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
ግልፅ ደብዳቤ ለህወሃት
የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about ግልፅ ደብዳቤ ለህወሃት
ለጨለንቆ ሰማዕታት
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ነፍጥ አንጋቢዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት የጨለንቆ ወገኖች በነቀምቴና በአዳማ ተማሪዎች መታሰቢያ አድርገዋል። የቢቢሲ የኦሮሚኛ ዘገባ እንዳስረዳው ከአንድ ቤት አምስት ሞተዋል። (ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ድረገጾች የተገኙ ናቸው) በነቀምቴ ወለጋ አዳማ ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ለጨለንቆ ሰማዕታት
አሁንም ይፈለጋል!
የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው – ኦሞት ኦባንግ !! ኦሞት የዛሬ 14ዓመት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኙዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን … [Read more...] about አሁንም ይፈለጋል!
ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው
አባቶች “ሥራ ለሠሪው እሾህ ለአጣሪው” እንዲሉ ኢትዮጵያውያንን ከፋፍሎ ለመግዛት ዘረኝነትን ፖሊሲው ያደረገው ህወሃት ለሃያሰባት ዓመት ኮትኩቶና ውሃ እያጠታ ያሳደገው ዘረኝነት ወይም የጎሰኝነት ገመድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ መተንፈሻ እያሳጣው ነው። ሰው በሰውነቱ ከዚያም ዝቅ ሲል በዜግነቱ ወይም በኢትዮጵያዊነቱ መከበር ሲኖርበት፣ ህዝቡን በጎጥ አጥር ከትቶ እርስ በርሱ እንዲጋደል ወያኔ ሌት ተቀን ሠርቷል። ለዘመናት የቆየው ኢትዮጵያዊ ትስስርና ባህሉ ህዝቡን በአንድነት ቢያቆየውም ብዙ ዜጎች በማንነታቸው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተዘርፈዋል፣ ተሰደዋል፣ ተንገላትተዋል። ጊዜ ይውሰድ እንጂ ኢትዮጵያውያን የወያኔ ተንኮል ከመረዳት አልፈው በቃህ በሚል ፍጻሜውን ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው። ዓለምን ያስደነገጠው የሩዋንዳ እልቂት ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያላቸውን ሩዋንዳውያን ቅኝ … [Read more...] about ዘረኝነት ፈጣሪዋን ልታጠፋ ነው
“ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?)” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ
"ዋሸሁ እንዴ?" (ነን ሶቤ) ሲል ይጠይቃል፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ። ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም። በአስር ሺዎች የታደሙበት የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ ይመስላል። ከፍ ሲል ደግሞ ኮንሰርቱን በቀጥታ ስርጭት እየተከታተሉ ላሉት የአድዋ ባለ ግዜዎች የቀረበ ጥያቄ ነው። ይህ ድምጸ-መረዋ ወጣት በምርጥ ቅላፄው ያንጎራጎረው ፉከራ እና ዜማ እጅግ ያስደምማል። ማስደመሙ እውነትን በመድረክ ላይ መዘርገፉ አይደለም። ከራሱ ደህንነት ይልቅ የወገኑን ስቃይ እና ሰቆቃ በማስቀደሙ ነው። እንዲህ አይነቱ እውነትን አደባባይ ወጥቶ በድፍረት የመናገር "ገት" የነበረው ቴዲ አፍሮ ነበር። ይህንን በማድረጉም በአንባገነኖቹ ጥርስ ውስጥ ገብቶ ብዙ ቢያስከፍለውም፣ ከህዝብ ልብ ውስጥ ሊወጣ … [Read more...] about “ነን ሶቤ (ዋሸሁ እንዴ?)” ይላል የአምቦው ፈርጥ ሃጫሉ










