በበርካታዎች ዘንድ የተለያዩ ስሞች አሏቸው፤ የአደባባይ ምሁር፣ አንጋፋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ፣ ጋሼ መስፍን፣ ወዘተ፡፡ በእኛ ግምት ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ የሚለው ገጣሚ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በተለይ በቅርብ ዓመታት ያሳተሟቸው መጻህፍት፣ የጻፏቸው ጦማሮች፣ ወዘተ ይህንን ማዕረግ ሊያሰጥዋቸው ይችላሉ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ፕ/ር መስፍን በህይወት ዘመናቸው ካስተማሩትና ካስተላለፉት ዕውቀት በተጨማሪ እጅግ በርካታ መጻህፍትን በማሳተም ይህንን ለዘመናት የዳበረውን ዕውቀታቸውን ለመጪው ትውልድ እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ አራት መጻህፍትን አሳትመዋል፡፡ በመጪው ሚያዚያ ወር 83 ዓመታቸውን ከማክበራቸው በፊት ባለቅኔው መስፍን በሰማኒያዎቹ ዕድሜያቸው ይህንን ሁሉ ለማድረግ መብቃታቸው ከጻፉት መጻህፍትና አርቆ … [Read more...] about “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
Right Column - Primary Sidebar
“የጠቆሩ ልቦች”
“የጠቆሩ ልቦች” ይቺ አጉል ዘመናይ፣ የወንዜ ልጅ እቱ አፍሪካዊ መልኳ፤ “ደብሯት” ጥቁረቱ ፊቷን በ“ሜክ አፕ” እጇን በእንሶስላ ፀጉሯን ባንዳች ቀለም፣ ቀባችው ልትቀላ፡፡ ግን ባይገባት እንጂ፣ እንዲህ የምትደክም እንዲህ የምትለፋ … የቆዳችን ሳይሆን፣ የልባችን መጥቆር ነው አገር ያጠፋ፡፡ ሰለሞን ሽፈራው “ተወራራሽ ሕልሞች” መጽሐፍ ባለፈው “ሕልም እንኳ የታለ?” በሚል ርዕስ ላወጣነው ጨዋታ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት ዱባለ፣ በለው፣ inkopa እና Yekanadaw kebede ምስጋናችን እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ በዚህኛው አስደናቂ ቅኔዎችም ተዘርፈዋል፤ ወላድ በድባብ ተሂድና አገራችን አሁንም ባለቅኔዎችንና ጥበበኞችን እንዳላጣች እናንተ ምስክር ናችሁ፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ ለዚህኛው ጨዋታ ደግሞ እስቲ ተቀኙልን! (ፎቶውን ያገኘነው … [Read more...] about “የጠቆሩ ልቦች”
የጎልጉል ቅምሻ
ጋብቻ በጠብመንጃ ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የ“ጠብመንጃ ጋብቻ” አሁን በከፍተኛ ቁጥር ቀጥሎ እንዳለ ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡ በላስቬጋስ የሚካሄደው ይኸው የጋብቻ ሥነስርዓት በቅርቡ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት በተተከፈተ ተኩስ ህጻናት ከሞቱ በኋላ ይቋረጣል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከተለያየ የዓለማችን ክፍል በመምጣት 500ዶላር አካባቢ በሚከፈልበትና በጠብመንጃ ሱቅ ውስጥ በሚካሄደው በዚህ ሥነስርዓት ሙሽሮች የተለያዩ ጠብመንጃዎች፣ ዑዚ መትረየስ፣ ኤኬ47፣ ወዘተ (ታንክ ሲቀር) የጦር መሣሪያዎችን በመያዝ ቃለመሃላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ለእነርሱ ብቻ በተዘጋጀ ቦታ ላይ የዒላማ ተኩስ በማድረግ ጋብቻቸውን በተኩስ ያደምቁታል፡፡ ወ/ሮ የመከላከያ ሚ/ር ከተመሠረተ ጀምሮ ከወንዶች በስተቀር እንስት ሚኒስትር ያላየው የአሜሪካው የመከላከያ ሚ/ር (ፔንታጎን) … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢሳያስ “ተላላኪ” ሲሉ ህወሃትን ዘለፉ በፈረንጅ የዘመን አቆጣጠር አዲስ ዓመት የተቀበለችውን ኤርትራን የሚመሩት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን ባገራቸው ቴሌቪዥን በትግርኛና በአረብኛ ተሳድበዋል። የአዲስ አበባው መንግስት የሚሉትን ህወሃት፣ “ተላላኪ” ሲሉ ዘልፈውታል። ስርዓቱ በአሜሪካ ጠንካራ እንክብካቤ እድሜውን ቢያራዝምም ተቃውሞ የሚመሰረተው ውስጥ ባለው ሁኔታ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኢሳያስ፣ “የራሱን ጥቅም ብቻ በሚያስቀድመውና አገሪቱን በሚያስተዳድረው ጠባብ ቡድን፣ እንዲሁም በተቀጥላነት በሚያገለግላቸው የውጪ ሃይሎች…” አማካይነት ማዕቀብ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል። ጠ/ሚ ቢቀያየር ትርጉም እንደሌለው ያመለከቱት ኢሳያስ፣ በሃይል የተያዘባቸው መሬት እስካልተለቀቀ ድረስ እንደማይደራደሩ አስታውቀዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላስተላለፉት የእንደራደር ጥያቄ “የጉዳዩን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
አዲሱ የሃይማኖት ህግና የሃገሪቱ ህገመንግስት
አዲሱ የሃይማኖት ህግና የሃገሪቱ ህገመንግስት (በሰለሞን) መንግሥት ሕገ-መንግስቱን ሊያከበር ይገባል! (ከእምነት ቤቶች) በጉዳዩ ላይ እንድንወያይ ስንጠየቅ ይህ የሃገረቱን ህገመንግስት ይቃረናል እኛም እዚህ ተወክለን የመጣነው ለሌላ ጉዳይ እንጂ በህግ ላይ ህግ ለማውጣት አይደለም ብለን አጀንዳው እንዲመለስ አድርገናል ፡፡(ከተስብሳቢዎች አንዱ) በስራ ላይ የዋለውን እንደ አዲስ ለማጸደቅ በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ ውይይት እንዲደረግ የእምነት ተቌማት የጋራ ጉባኤ ላይ ቀርቦ ነበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አይመለከተኝም ብላ ወጥታ ነበር ቀጥሎም የኢትዮጵያ እስልምና ጽህፈት ቤትም አይመለከተኝም ብሎ ነበር፡፡ በመጨረሻምወንጌላዊያን ይህ ህግ እነርሱ ላይ ተፈጻሚ ሆኖ የቆየ ቢሆንም በህግ መልክ እንደገና ሲቀርብ ግን ተገርመውበታል፡፡ “ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መርጠው በላኳቸው … [Read more...] about አዲሱ የሃይማኖት ህግና የሃገሪቱ ህገመንግስት
የጎልጉል ቅምሻ
ፍቅር ቁመት አይወስነውም የዓለማችን ረጅም ወጣት የከንፈር ወዳጅ የሆነው የ22ዓመቱ ብራዚላዊ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ አስደሳች እንደሆነ ገለጸ፡፡ ዕድሜዋ 17ዓመትና ቁመትዋ 6ጫማ ከ8ኢንች (2.1ሜትር) የምትረዝመው ኤሊሳኒ ሲልቫ ዕድገቷን የሚቆጣጠረው ዕጢ ላይ ባጋጠማት ችግር ምክንያት እንደዚህ ቁመቷ ሊረዝም እንደቻለና በሽታዋ ከታወቀ በኋላ ሐኪሞች ዕብጠቱን እንዳስወገዱት ተገልጾዋል፡፡ ወደፊት ሞዴሊስት ለመሆን የምታስበው የከንፈው ወዳጅዋ መልካም ስብዕና ያለውና ለእርሷም ድንቅ አመለካከት እንዳለው ገልጻለች፡፡ ሆኖም ችግሯን ከመግለጽ አልተቆጠበችም፤ “ያለኝ ዋና ችግር እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንሄድ ትንሹን ወንድሜን ወይም ልጄን ይዤ የምሄድ ይመስለኛል” ብላለች፡፡ የዓመቱ ሰው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ታህሳስ 4፤ 1928ዓም (ጃኑዋሪ 6፤1936 አውሮጳውያኑ ቆጣጠር) … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ጁነዲንና ኢህአዴግ ፊርማቸውን ቀደዱ ከሚኒስትርነታቸውና ከኦህዴድ ስራ አስፈጻሚነታቸው በግምገማ እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል። ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው ለማንሳት ፓርላማው በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ የምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡ ሪፖርተር እንዳለው “የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን በቀጣይ ስብሰባ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
ኅዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሥራ ጉዳይ ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ለሁለት ቀን ተኩል የሚበቃኝን ሸክፌ ከመሥሪያ ቤቴ በተመደበልኝ መኪና ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ለሚነሳው በረራ ለመድረስ ወደቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ላይ የተደረደሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት አቀባበል ወይንም ሽኝት የሚደረግለት ባለሥልጣን/እንግዳ እንዳለ ስለጠቆመኝ መንገዱ ሳይዘጋ ቦሌ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርግ ለሹፌሩ ጠቆምኩት፡፡ ብዙም ሳንጓዝ አትላስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ላይ ስንደርስ በስፍራው የነበሩት የትራፊክ ፖሊሶች ወደ ቺቺንያ ወይንም ወደ ቦሌ ሩዋንዳ የሚወስደውን መንገድ እንድንጠቀም አስገደዱን፡፡ ወዲያውኑ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ ለሰባት … [Read more...] about አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!
ሕልም እንኳ የታለ?
ሕልም እንኳ የታለ? በሕልሜ ተኝቼ፣ ሸጋ ሕልም አይቼ በአገሬ በአፍሪካ ዲሞክራሲ በቅሎ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መብቱ ተደላድሎ ወገኔ ሲያጣጥም የሰላምን ፍሬ ሽብር ተወግዶ በመላው አገሬ . . . ይህን እያለምኩኝ አልጋ ውስጥ አርፌ . . . ጥይት ቀሰቀሰኝ ከሞቀው እንቅልፌ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ከፀሐይ በታች መድብል 2004ዓ.ም “መሰላል” በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ ድንቅ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት በለው፣ ዱባለ፣ አሥራደው (ከፈረንሳይ) እና yeKanadaw kebede ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁ የቋጠራችሁት ግጥም በራሱ የግጥም ጨዋታ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለጨዋታ ያቀረብነው ግጥም ከዚህ በፊት “ሕልመኛው” በሚል ካወጣነው ጨዋታ ጋር በ“ሕልም” እንኳን የማይገናኝ መሆኑን ለመግለጽ … [Read more...] about ሕልም እንኳ የታለ?
በአረቢያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ሽያጭ ተጠያቂው ማነው?
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት … [Read more...] about በአረቢያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ሽያጭ ተጠያቂው ማነው?










