ከሁለት ወር በፊት “የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ?” በሚል ርዕስ ላቀረብነው ጽሁፍ የድረገጻችን የዘወትር ተሳታፊ አሥራደው ከፈረንሣይ “የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!” በሚል ርዕስ የመጀመሪያውን ክፍል ጽሁፋቸውን አስነብበውን ነበር፡፡ በዚህ የክፍል ሁለት ጽሁፋቸው ደግሞ ባለፈው ያነሱትን ጉዳይ በመዳሰስ እንደሚከተለው አቅርበውታል፡፡ ወርቁ ካዶላ የሚያጌጥበት ሌላ! በመጀመሪያው ክፍል መጣጥፌ፤ ቡችላው ማነው? ለምንስ ቡችላ ተባለ? በሚል ጥያቄ ነበር የተለየኋችሁ :: የወርቁ ቡችላ በምስሉ የሚያዩትን ይመስላል፤ ቡችላ የተባለበት ምክንያት ተለቅ ያለ የወርቅ ፍንካች በመሆኑ ነው:: እናም: አዶላ ወርቅ ነው፤ አዶላ ማርና ወተት ነው፤ አዶላ የዱር አራዊትና አዕዋፍ በአንድላይ ሆነው የሚዘምሩበት፤ ዛፎች እጅ ለእጅ ተያይዘው … [Read more...] about ወርቁ ካዶላ የሚያጌጥበት ሌላ!
Right Column - Primary Sidebar
የጎልጉል ቅምሻ
ብልቴን ሰረቁት በምስራቅ ቻይና የዢያንግ አውራጃ የኒቂያዖ ፖሊስ የደረሰው ክስ ግራ የሚጋባ ሆኗል፡፡ የ41ዓመቱ ፌ ሊን “ተኝቼ ሳለ ሌቦች ክፍሌ በርግደው በመግባት ብልቴን ሰረቁት” በማለት ነበር ወንጀሉን ያብራራው፡፡ ሲቀጥልም ሌቦቹ ቤቱ እንደገቡ ጭንቅላቱ ላይ የሆነ ነገር አድርገው ሱሪውን ወደታች ካወረዱ በኋላ ሮጠው እንደጠፉ አስረድቷል፡፡ “በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም፤ በኋላ ግን እየደማሁ መሆኔን ሳስተውል ብልቴ ተበጥሶ መሄዱን አስተዋልኩ” ብሏል፡፡ ፖሊስ እንደሚለው ሌቦቹ ሊን በሚያዘወትራቸው በርካታ ሴቶች የቀኑ አፍቃሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምት በመስጠት ፍለጋውን ቀጥሏል፡፡ ሊን ግን ይህንን የፖሊስ መላምት ካለመቀበል በተጨማሪ የትም ሂያጅ ሳይሆን ታማኝ እንደሆነ ለራሱ ይመሰክራል፡፡ በስርቆቱ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም በርካታዎች … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
የጉራ ፈርዳ አማሮች መሬታቸው በሃራጅ ተሸጠ ቪኦኤ ሰለባዎችን በማነጋገር እንደዘገበው የጉራ ፈርዳ ነዋሪ አማሮች መሬታቸውን እንዳያርሱ ከተከለከሉ በኋላ መሬታቸው በሃራጅ እየተሸጠባቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል። መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ የግላቸው እንዳደረጉና ግብር እየከፈሉ የሚኖሩት ተበዳዮች ርምጃው የተወሰደባቸው ቅንጅትን በመምረጣቸውና ለመኢአድ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል እንደሆነ ተናግረዋል። በተደጋጋሚ መታሰራቸውንና በከሰሳቸውን የተናገሩት የጉራ ፈርዳ ነዋሪ ከእስር ከተፈቱ በኋላ “መሬታችሁን የያዛችሁት በህጋዊ መንገድ ነው” በማለት ለመኢአድ መረጃ መስጠታቸው እንደ ጥፋት እንደተወሰደባቸው አመልክተዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት በምስጢር የድምጽ መስጫ ክፍል ውስጥ የጤና ባለሙያዎችን በማስቀመጥ ማንን እንደመረጡ መሰለላቸውንም አመልክተዋል። የሚሸጠውን መሬት የወረዳ፣ የቀበሌ፣ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ውለታ የማታውቅ ሀገር
• ያ የኮሜዲ አውራ “እብድ” ተብሎ ጎዳና ላይ “ቆሼ” ይለቅማል! • እርሱን ያፈራው ኅብረተሰብ የወደቀን ቀና ከማድረግ እንዳይቃና ይተጋል • ስለዚህ ኅብረተሰቡ እንደ ድመት የራሱን ልጆች ይበላል! ይኸውልህ ወዳጄ የተመለከትኩትን፣ የታዘብኩትን እና ያስተዋልኩትን እንደወረደ ላጫውትህ፡፡ ያ ጉምቱ የጥበብ ሰው፣ ያ የኮሜዲ-የጭውውት አውራ፣ ያ ጥበብን የተቀባው ባለትልቅ ተሰጥዖው ሰው፣ ያ ከሥነ-ሠብዕ ጥበብ ተሻግሮ የአዕዋፋትን ዝማሬ ምስጢር፣ የንፋስን ሿሿታ፣ የበር-መስኮት ሲጥሲጥታ ሳይቀር በጥበብ ሥራው ላይ አክሎ የሚከውንልህ ተዋናይ ልመንህ ታደሠ፣ ከፒያሳ ወረድ ብሎ ከሚገኘው ቢስ መብራት አደባባይ ላይ፣ እንደ ማንም ቆሼ ሲለቅም ተመለከትኩት፡፡ ልመንህን ያየ፣ እኔን-አንተን አየ፤ እኔን-አንተን ያየ ኅብረተሰቡን አየ፤ ኅብረተሰቡን ያየ-ተቋማቱን አየ ነው እያልኩህ ያለሁት … [Read more...] about ውለታ የማታውቅ ሀገር
“ዲቪ አልቀረም!! ቀረ ያለው ማን ነው?”
የዲቪ ሎተሪ እድለኛ ነው። ባገኘው እድል መሰረት አሜሪካ ለመግባት ማሟላት የሚገባውን ሁሉ እያከናወነ ይገኛል። በአካል አዲስ አበባ፣ በሃሳብ አሜሪካ ያለው ወጣት ስራውን በገዛ ፈቃዱ ተሰናብቷል። እቃውን ለሚወዳቸው ማከፋፈል ጀምሯል። አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ የብስና ውቂያኖስ አልሰነጠቀም እንጂ በምኞት በየቀኑ በረራ ያደርጋል። አሜሪካ!! “ማርና ወተት የምታፈሰው አሜሪካ እንደገባሁ” እያለ ቃል የሚገባላቸው ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ ስንቅ እያዘጋጁለት ነው። ስጦታ ያበረከቱለትና ድንገት ካልተገናኘን በማለት የተሰናበቱት አሉ። እንዳኮበኮበ ያለው ወጣት ላሊበላ ሬስቶራንት ጫማ እያስጠረገ የአጭር የስልክ መልዕክት ይደርሰዋል። መልዕክቱ “ዲቪ ቀረ” የሚል ነበር። ወዲያው “ማን ነው ቀረ ያለው” ሲል መልሶ ጠየቀ። ደነገጠ። ብርክ ያዘው። ህልሙ፣ ውጥኑ ሁሉ ሲተን፣ ከእጁ ሲያመልጠው ታየው፡፡ … [Read more...] about “ዲቪ አልቀረም!! ቀረ ያለው ማን ነው?”
ሉዓላዊነትና መብት
ሶርያ አሮጌ አገር ነው፤ ታሪኩ ረጅም ነው፤ ከሶርያ ጋር ሲወዳደር አሜሪካ ሕጻን ነው፤ ነገር ግን ለብዙ ወራት በሶርያ ውስጥ የሚካሄደውን ጦርነትና በቅርቡ በአሜሪካ የተደረገውን ምርጫ ስንመለከትና ስናነጻጽራቸው፣ የሶርያ ሕዝብ እርስበርሱ ሲጨራረስ አሜሪካኖች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሐዝቡ ድምጹን ሰጥቶ ምርጫው ተጠናቅቆ በሰላም የሥልጣን ርክክብ ተደረገ፤ ዕድሜ የመብሰል ምልክት ላይሆን እንደሚችልና ፍሬ-አልባ እንደሚሆን መረዳት እንችላለን፤ ከርሞ ጥጃ እየሆኑ ዕድሜ መቁጠር፤ በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ግን አንድ ሰው፣ በሺር አላሳድ፣ እስቲሞት ድረስ መጋደሉና አገር መፈራረሱ ይቀጥላል፤ ዓለምም፣ የተባበሩት መንግሥታትም፣ የአረብ ማኅበርም ሁሉም ከንፈሩን እየመጠጠ የሶርያን ሕዝብ ስቃይ ያያል፤ የፍልስጥኤማውያንንም ስቃይ እንዲሁ፡፡ ለምን አንዲህ ይሆናል? ምክንያቱ ሉዓላዊነት የሚባል ነገር … [Read more...] about ሉዓላዊነትና መብት
በሳቅ ፍርስ አሉ
በሳቅ ፍርስ አሉ አገራቸውን በመክዳት ወገናቸውን ለመጉዳት ያልነበረ ሕግ ጥሰው በነስብሐት ነጋ – በነ መለስ ተከሰው ሽብርተኛ ሲባሉ ‘በሳቅ ፍርስ አሉ’ አሉ፡፡ ሽ-ሽ-ት በሚል ርዕስ ላቀረብነው የአብዲ ሰኢድ ግጥም ግሩም የሆነ ምላሽ በመስጠት ጨዋታው ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት dawit፣ ሽማግሌው፣ በለው፣ yeKanadaw kebede እና ዱባለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ በዚህ የግጥም ጨዋታችን የዘወትር ተሳታፊ የሆኑት የካናዳው ከበደ (yeKanadaw kebede) “ለሚቀጥለው የግጥም ጨዋታ አድርጓት” ብለው “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ “አሸባሪ” በመባል ተከስሰው በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን በተመለከተ የላኩልንን ግጥም ነው ላሁኑ ጨዋታችን ያቀረብነው፡፡ እስካሁን ግጥም ስናቀርብ የነበረው ከሌሎች ቦታዎች ነበር አሁን ግን የካናዳው ከበደ የራሳቸውን … [Read more...] about በሳቅ ፍርስ አሉ
የጎልጉል ቅምሻ
ስኳር ለስኳር በሽታ ያጋልጣል “ጣመኝ ድገመኝ” የምንላቸው ዓይነት ብስኩቶች፣ የቸኮሌት ውጤቶች፣ አይስክሬም፣ ብርታት ሰጪ መጠጦች፣ … በከፍተኛ ሁኔታ ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጡ ሳይንስ ደርሼበታለሁ ይለናል፡፡ በእነዚህ የምግብ ውጤቶች ውስጥ የሚገኘው የበቆሎ ስኳር (fructose corn syrup - HFCS) ምግቦቹን ለማጣፈጥ የሚጨመር በመሆኑ ይህንን ተመጋቢ የሆኑ 20በመቶ ለስኳር በሽታ መጋለጣቸው የማይቀር ነው ይላል ውጤቱ፡፡ ከምዕራባውያን አገራት መካከል አሜሪካ በጣፋጩ አወሳሰድ ቀዳሚውን ስትይዝ በአማካይ አንድ ሰው በዓመት 24.78ኪሎ የበቆሎውን ስኳር በተለያዩ ምግቦች አማካኝነት ወደ ሆዱ ይጭናል፡፡ አንድ ካናዳዊ በዓመት 9.13ኪሎ ሲጭን አንድ ጣሊያናዊ ወይም እንግሊዛዊ ከግማሽ ኪሎ በታች እንደሆነ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ግብጻዊያን 1.6ኪሎ በአማካይ እንደሚጭኑ ያስረዳው … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
ከእሁድ እስከ እሁድ
በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነጋዴ ወይስ ለወገን ደራሽ? በዱባይ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፓስፖርታቸው በአሰሪዎቻቸው አማካይነት ለተመለሰላቸው ወገኖች የፓስፖርት እድሳት በሚል አንድ ሺህ አንድ መቶ ድራም እንደሚያስከፍል ተሰማ። ለጎልጉል በስልክ መረጃ የሰጠች አንድ የዱባይ ነዋሪ ኤምባሲው አገልግሎቱን መጀመሩ እንደሚያስመሰግነው ጠቁማ፣ ክፍያው ግን የተጋነነ ንግድ እንደሚመስል አስታውቃለች። ዘጠና ከመቶ የዱባይ ነዋሪዎች ፓስፖርታቸው ጊዜው ያለፈበትና በአሰሪዎቻቸው በመያዣነት የተያዘ እንደሆነ የጠቀሰችው ይህች ወጣት “በችግር ላይ ካሉ ዜጎች ላይ ከስድሰት ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር መቀበል አግባብ አይደለም። ኤምባሲው ፓስፖርታቸው ለተወሰደባቸውም መላ ይፈልግ” ስትል ጠይቃለች። አሰሪዎቻቸው በሚያደርሱባቸው በደል ተማረው የሚጠፋ ወገኖች ፓስፖርታቸው በመያዣነት አሰሪዎቻቸው ዘንድ ስለሚቀር የጉዞ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው
እንደ መግቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን የካቢኒያቸውን ሽግሽግና አዲስ ተሿሚ ሚኒስትሮቻቸውን ትላንት (ህዳር 20፣ 2005 ዓ.ም) በፓርላማ በመገኘት አሹመዋል:: አዲሱ ካቢኔም ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች ሲኖሩት የአራት ሚኒስቴሮችን ሽግሽግም ያካተት ነው:: የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሚኒሰቴር አቶ ጂነዲ ሳዶ ከሃላፊነት በማንሳት በአቶ ሙክታር ከድር ተተክተዋል:: የጤና ጠብቃ እና የንግድ ሚኒስትር ሚኒሰቴር ዲኤታ የነበሩት ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና አቶ ከበደ ጫኔ እንደየቅደምተከትል ለሚመሯቸው ተቋሞች ሚኒስቴር ሆነዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ማዕረግ የተሾሙት የሚከተሉት ናቸው:: ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል … [Read more...] about አዲሱ የስልጣን ክፍፍልና አመክንዮው










