የዛሬ 30 ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሒሣብ መዝገበ አያያዝ ትምሐርት አስተምር ነበር። ዛሬም በሱው ነው እንጀራዬን በስደት ዓለም ከስቃይ ጋር እንደወጥ እያጣቀስኩ የምበላው። ታዲያ ያኔ፣ የመምሕራን ካፌቴሪያ ለምሳ በየጠረጴዛው ዙሪያ በቡድን በቡድን እየተሰበሰብን አንዳንድ ክፍል ውስጥ ያጋጠሙን ገጠመኞች እያነሳን እንስቅ ነበር። አንድ ዕውቅ የኢኮኖሚክስ መምሕር ነበሩ። እግዚአብሔር ይመስገንና፣ ዛሬም በሕይወት አሉ። ስማቸውን ግን አልጠቅስም። ታዲያ አንድ ቀን ከጎናችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሁነው ምሳ እየበሉ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በዕለቱ ያጋጠማቸውን አስቂኝ ክስተት ሲገልጹ፣ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እንደዋዛ እሰማቸው ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዳንድ ጠጠር ያሉ የኢኮኖሚክስ ጽንሰ-ሀሳቦችን አንስተው ሲያስተምሩ፣ አንድ ወጣት ተማሪ ነገሩ ከብዶት ነው መሰል፣ ሳያስበው … [Read more...] about ውይ! አምባሳደሩ ተናገሩ!
Left Column
የቅሊንጦ አንበሶች
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ቅሊንጦ የሚባል ጫካ አለ እዚያ ጫካ ውስጥ በርካታ ጥቁር አንበሶች አሉ፡፡ ለጥቂት ቀናት እዚያ ጫካ ውስጥ ከትቸ ነበር፡፡ በገባሁ በዐሥረኛ ቀኔ ትቻቸው ወጣሁ፡፡ እዚያ በነበርኩበት ወቅት ካገኘኋቸው አናብስት የሁለቱን ታሪክ ብቻ በአጭር በጭሩ ላጫውታቹህ፡፡ አንደኛው አበበ ካሴ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ጎንደር ነው፡፡ አምና 2006ዓ.ም. ጥር 12 ቀን ነበር የተያዘው፡፡ ወደዚህ ጫካ ከመምጣቱ በፊት በተለያዩ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የማሰቃያ ቦታዎች ሰቆቃ ሲፈጸምበት ቆይቶ በመጨረሻ ነው እዚህ ጫካ ውስጥ የታሰረው፡፡ አበበ ካሴ የግንቦት 7 ቆራጥ ታጋይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ከ1981-1993ዓ.ም. ድረስ የቀድሞው ኢሕዴን የአሁኑ ብአዴን ታጋይ ሆኖ ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ ከዚያ በኋላ እሱና ጓዶቹ ታግለው ለዚህ ያበቋቸው መሪዎቹ ከዚህ በስተቀር የማይባል … [Read more...] about የቅሊንጦ አንበሶች
“አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት
የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸው፡፡ የሚኖሩት ከ10 አመት ልቻቸው ጋር ነው፡፡ ይህን ልጅ እሳቸው ብቻ ነው የሚያሳድጉት፡፡ ትናንት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከታፈሱ ከሰዓታት በኋላ ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በደህንነቶች ታፈኑ፡፡ አቶ ቀኖ የጥበቃ ስራ ከመስራት ውጭ ሰልፉ አስተባባሪም ተሳታፊም አልነበሩም፡፡ ግን ታጥሮ ከሰነበተው የሰማያዊ ቢሮ የወጣ ሁሉ ሲለቀም ነበርና እሳቸውንም አፈኗቸው፡፡ ምን አልባትም ተደብድበው ይሆናል፡፡ ይህ ስርዓት እነ ይልቃልን፣ ብርሃኑን፣ አቤልን፣ በላይን፣ ጣይቱዎቹን . . . ሰማያዊን ብቻ አይደለም የሚፈራው፣ የሚያፍነው፣ የሚያፍሰው፣ የሚደበድበው፡፡ አቶ ቀኖንም የሆነ ነገር ያደርጋሉ ወይንም አድርገዋል በሚል (በራሱ ትርጉም) አፍኖ አስሯቸዋል፡፡ አሁን አቶ ቀኖ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ … [Read more...] about “አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት
ግልጽ ደብዳቤ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
የዱሮ ወዳጄ ሰላምታዬ ይድረሽ። እንደምታውቂው ከተያየን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሆኗል። እኔም ካገሬ ከወጣሁ 21 ዓመት አለፈኝ። በጤናና በምቾት እንደምትኖሪ እሰማለሁ። እግዚአብሄርም መንግስትም ጥሩውን ነገር ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጥሽ ምኞቴ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጓደኝነት ከምቀርባቸውና ከማከብራቸው ስዎች ውስጥ አንቺ አንዷ እንደነበርሽ ራስሽም ብዙ ሰዎችም ያውቃሉ። ከጊዜ ብዛትና በስልጣንም ርቀት ምክንያት ጓደኝነቴን ብትረሽውም አልፈርድብሽም። እኔ ግን ከሀገሬ ባለስልጣኖች አንዷ በመሆንሽ አልፎ አልፎም ቢሆን ስላንቺ የሚባለውን ከፉም ደግም እሰማለሁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስላንቺ ክፉ ሲናግሩ ስሰማ የጓደኝነት ነገር እየሆነብኝ ደስ አይለኝም። ተሳክቶልኝ እንደሆን ባላውቅም ስላንቺ የማውቃቸውን በጎ ነገሮች በማንሳትም ልሟገት የሞከርኩበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ብዙ ሰዎች ያኔ 41 … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
የጣሊያን ፖሊስ ሰዉ አስተላላፊዎችን ያዘ
የጣሊያን ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንግድ ወደ አዉሮጳ ያሸጋግራሉ በማለት የተጠረጠሩ 10 የኤርትራ ተወላጆችን በቁጥጥር ሥር አዋለ። የካታኒያ-ሲሲሊ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ የሚያሸጋግር ሕብረ-ሐገራት መረብ መኖሩን የሚጠቁም መረጃ ከደረሰዉ በኋላ ባደረገዉ አሰሳ ነዉ። በፖሊስ መግለጫ መሠረት ስደተኞቹን የሚያሻግረዉ መረብ ኤርትራ፤ ሊቢያ፤ ሌሎች ሰሜን አፍሪቃ ሐገራት እና ኢጣሊያ ድረስ የተዘረጋ ነዉ። ለአሸገጋሪዎቹ ገንዘብ እየከፈሉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ በርካታ ስደተኞች ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ እየሰመጡ ሞተዋል። ፖሊስ ሰሞኑን የያዛቸዉን ተጠርጣሪ አሸጋጋሪዎች ካለፈዉ ግንቦት እስከ መስከረም ድረስ 23 የባሕር ላይ ጉዞዎችን አቀነባብረዋል በማለት ከሷቸዋል። ከተጓዦቹ ቢያንስ 240 ስደተኞች ሞተዋል። ከአስሩ ተጠርጣሪዎች ዘጠኙ ኅዳር 16 … [Read more...] about የጣሊያን ፖሊስ ሰዉ አስተላላፊዎችን ያዘ
ዘመን ሞቷል – ኃይሉ አትበሉ
ማስታወሻው ጠፍቶ ምስሉ ተገርስሶ ወድቆ አካሉ ተሰርዞ ቃለ ውሉ ዘመን ሞቷል ኃይሉ አትበሉ። ታሪክ የለም አምልጦናል ዘመን ቆመን ሞቶብናል ሁሉም አልቆ ተጠቃሏል ጋሼ ኃይሉ ይዞት ሄዷል ለዘመን ነው እንባ ማፍሰስ ለታሪክ ነው ከል መልበስ ለጊዜ ነው ፊት መከስከስ ለጋሽ ኃይሉ ይብቃን ማልቀስ የዘመንን በሞት ማምለጥ የጊዜውን መገላበጥ ገና በፊት ጋሼ ኃይሉ ተናግሮታል በአፉ ሙሉ መጣ ብለን ሚሊኒየም በክብሩ ላይ ልንታደም ወዲያ ወዲህ ስንሯሯጥ ምድር ስንቀድ ሰማይ ስንፈልጥ ከረምንና አገር ወጥቶ ተበልቶና ተጠጥቶ ጋሼ ኃይሉ ብቻ ቀርቶ ምነው ጠፋህ? በዚህ በዓል አንተ ብቻ ብሎ ሲባል ያልኖርኩትን አላከብርም ይሄ በዓል የኔ አይደለም መች ኖሬ ነው የማከብረው የኔ ዘመን ሞቷል ተወው ብሎ ነበር መልስ የሰጠው ጋሼ ኃይሉ እንዲህ … [Read more...] about ዘመን ሞቷል – ኃይሉ አትበሉ
“ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]
እንዴት ሰነበታችሁሳ! ሀሳብ አለን … ስብስባዎች ሁሉ … አለ አይደል… “እንዴት ሰነበታችሁ…” በሚል ብቻ ይከፈትና ወደ ጉዳዩ ይገባ! አሀ … “ክቡር እከሌ እከሌ፣” “ክብርት እከሊት እከሌ፣” “የተከበሩ እከሌ እከሌ” … ምናምን ሲባል የስብሰባው ሲሦ እያለቀ ነዋ! ለነገሩ … (“ለምን ይዋሻል!” የሚሉት ነገር ነበረ አይደል!) ብዙ ስብሰባዎች ላይ “እንትንህን እንደ ዳናኪል እንፋሎት እንዳላቦንልህ!” አይነት “የጉልበት ግማሹ ምላስ ነው…” ነገር በዝቷላ! (እኔ የምለው … አንዳንዱ መድረክ ላይ ወጥቶ እንዴት ነው እንዲህ ‘ልክ ልክ ማጠጣት’ የሚዋጣለት!) አንድ ወዳጃችን ሲነግረን አለቅየው ‘መጠመቁን’ ለበላዮቹ ለማስመስከር የማይሞክረው ነገር የለም፡፡ በተለይ ስብሰባዎች ላይ የሚናገረው ‘ቦተሊካ’ ነክ ንግግር ካርል ማርክስን ጢሙንና ጸጉሩን አርግፎለት ‘አይ ሮቦት’ ነገር … [Read more...] about “ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]
የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ - በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል። "እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል... ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።" እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም... ይመስላል። የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ … [Read more...] about የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
የድል ፍሬ ፀሐይ
የሕይዎት ዋስትና ፤ የፍጥረቱ ሲሳይ ሃሌታዊ ጀምበር ፤ ለዚህች ማሕሌታይ የተስፋ ብርሃን ፤ የማለዳ ፀሐይ የድል በረከቱ ፤ መከራን ገላጋይ እፎይታን አስኮምኳኝ ፤ ሁሉንም አማላይ ኧረ ምን ነው ቀረሽ ፤ እባክሽ ቶሎ ነይ፡፡ አዝርቱን ውርጭ መታው ፤ ቀረ እንደ ጫጨ አውድማው ነጠፈ ፤ ዘር መክለፍት ተፈጨ ሁሉም በቁር ጠፋ ፤ ውሽንፍሩ አፋጨ ሕይዎት ያለው ፍጥረት ፤ በአጭሩ ተቀጨ የማለዳ ፀሐይ ፤ ሕይዎት መታደያ ምን ነው በአፍሪካ ፤ ምን ነው በኢትዮጵያ ሌሊቱ ረዘመ ፤ ምንድነው ምክንያቱ አትወጭም እንዴ! ፤ ገደለን ምኞቱ የድል ፍሬ ፀሐይ ፤ የፍጥረት ሕይዎቱ በነፍስ ድረሽልን ፤ ይንጋልን ሌሊቱ፡፡ ቁር የቀፈደደው ፤ ያስቀመጠው አስሮ ልሳኑ የተያዘ ፤ የደረቀው ከሮ በሙቀትሽ ይንቃ ፤ ይፈታ ሞት … [Read more...] about የድል ፍሬ ፀሐይ
የባለቅኔው ዝምታ
የታዋቂው ባለቅኔና የሥነ ጽሑፍ ሰው የጋሼ ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) አስከሬን ኖቬምበር 30፤2014 በእስቶክሆልም ከተማ በብዙ መቶዎች በሚቆጠሩ ያገር ልጆች፣ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ጓደኞቹ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት በአቡነ ኤልያስ የሚመራ ፍትሃት የተደረለት ሲሆን፣ ቤተሰቦቹና ተጋባዥ እንግዶች የመሸኛ ንግግርና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥሞችን (Lament) ለለቀስተኞች አቅርበዋል፡፡ በዕለቱ የተገኙት ደራሲ አበራ ለማ ከተጋባዥ ተናጋሪዎችና የሐዘን እንጉርጉሮ ግጥም አቅራቢዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን “የባለቅኔው ዝምታ” በተሰኝ ግጥም ስንብታቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህንኑ በማስመልከት አበራ ለማ የላኩልንን ግጥም እንዲሁም ፎቶ አቅርበናል፡፡ የባለቅኔው ዝምታ መጣልሽ እምዬ፣ ገሞራው ልጅሽ ቅኔ ባኩፋዳ፣ ስንቁን ይዞልሽ፤ መጣልሽ … [Read more...] about የባለቅኔው ዝምታ







![“ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2014/12/Birds-300x277.gif)


