ዓለምነህ በአዋዜ ፐሮግራሙ ላይ ጸጋዬ አራርሳ ‹‹ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም›› ያለውን ይዞ በለዘበ ቋንቋና በለዘበ ድምጽ ደቁሶታል፤ ብዙ ሰዎች የገባቸው አልመሰለኝም፤ በጉዳዩ የተማረውና የተመራመረው ዶር. ጸጋዬ አራርሶም የገባው አይመስለኝም፤ እስቲ እኔ የገባኝን ልንገራችሁ፡፡ በመጀመሪያ በሁለቱ ሰዎች መሀከል ያለውን የትምህርት ደረጃ ልዩነት ዓለምነህ ራሱ እንዳለው እሱ ‹‹በትምህርት እጅግም አልገፋም›› ጸጋዬ ግን የትምህርቱን ደረጃ ጣራው ላይ አድርሶታል ተብሎ በስሙ ላይ ‹‹ዶክተር›› የሚል የትምህርት ማዕርግ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ በትምህርት እጅግም ያልገፋው ሰው በትምህርት ጣራ ላይ በደረሰው ሰው አስተያየት ላይ የሰጠው ትችት የትምህርት ደረጃ የሚባለውንም ሆነ የሁለቱን ሰዎች እውቀትና ብስለት የሚለካ ነው፤ የዓለምነህ ትችት ስለቱ ያረፈው ጸጋዬ የሚልዮኖችን እምነት መካዱ ላይ … [Read more...] about ዓለምነህና ጸጋዬ አራርሳ
Left Column
“ትራምፕ – ቢመረጥስ?! …”
… በበረዶ፣ በዝናም፣ በሐሩር፣ በቁሩ . . . መፈክር አንግበን፣ ላንቃችን እስኪታይ - አምባገነኖችን በጩኸት አውግዘን፣ የድምጽ-አልባውን ሕዝብ - የጭቆና ብሶት፣ ላለም ስናሰማ - ለሩብ ምዕተ-ዓመት፤ ጆሮ ዳባ ብለው - የተሳለቁብን፣ ከጨቋኝ ወግነው፣ በዶላር አፋፍተው… ነጻነታችንን በጅ-አዙር ያስቀሙን. . .፤ ቦ! ጊዜ ለኩሉ!... የተፈጥሮ አዙሪት-ህግ - የወር-ተራው እዚያም ደርሶ፣ በታላቋ አሜሪካ - “አምባገነን” ትራምፕ ነግሶ፣ ‘የባቢሎን ግምቡን‘ አጥሮ . . . ነጻነትን ፊጥኝ አስሮ፣ ህገ-መንግስት ተሰውቶ. . . ፍርድ ቤቱም ለርሱ አድልቶ...፣ የአሜሪካ ሃምሳ ስቴቶች - ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው፣ በመፈክር ተጥለቅልቀው - በራብ-አድማ ጠቁረው ከስተው፤ በላያችን የወረደ ፣ መብረቅ... ዝናም ወርዶባቸው፣ የነጻነት ረሃብ፣ ጥሙ - ዘልቆ ገብቶ … [Read more...] about “ትራምፕ – ቢመረጥስ?! …”
ሰሚ ያጣ ሕዝብ
ሕዝብ ተነሳ። ይህ ከወትሮው የተለየ አነሳስ ይመስላል። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ይህ ሕዝብ ተነስቶ ሲያበቃ እድሉን ለልጆቹ በአደራነት ሰጥቶ ሲቀመጥ፥ መሪዎቻችን የስልጣን ርክክብ አካሄደው ሕዝቡን በዜሮ እየሰደዱት ስልችቶታል። ቁጭ ብድግ ማለቱ በቃኝ ያለ ይመስላል። አሁን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መነሳቱ፥ የስልጣን ርክክብ ለማካሄድ ሳይሆን፥ ዳግም እንደገና መነሳት በማያስፈልገው ሁኔታ ስልጣኑን ራሱ ወስዶ ተረጋግቶ ለመቀመጥ ነው። ቀድሞ ነገር ባለጉዳዩ ሕዝብ ቁጭ ብሎ መሪዎቻችን ሲተራመሱና ሕዝቡን ራሱን ሲያተራምሱት ምንም ያለማድረጉ በውጭ ለተመልካች ሲታይ ምንም እንደማያውቅ ያስመስለው ይሆናል። እውነቱን ብንመረምር ግን የምናስተውለው ሁሉን አዋቂ እንደሆነና፥ ዝም ያሰኘው ትዕግስቱ መሆኑ በገባን ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲታገስ መሬት ነው። ይሸከማል፥ ይችላል። ረዥም ጊዜ ይሰጣል። ፅዋ … [Read more...] about ሰሚ ያጣ ሕዝብ
ሰምሃል መለስ የገባት መተካካት – ተቃዋሚዎች ያልገባቸው መታደስ!
የአፈና ግዜ አዋጁን ተከትሎ፤ የሕወሃቱ ፋና ብሮድካስቲንግ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያስተናገደው "የውይይት መድረክ" አዳዲስ ኩምክናዎችን ይዟል። ልደቱ አያሌውን በመሪ ተዋናይነት ያሳተፈውን ይህን አዲስ የበረከት ስምኦን ድራማ ብዙም ሰው አላየውም። ሕዝቡ ፋና ሚባል ነገር እንደሬት መርሮታል። ገሚሶች ደግሞ በ"ቃና"ው "ጥቁር ፍቅር" ድራማ ተጠምደዋል። በዚህ ድራማ ልደቱ አያሌው መሪ ገጸ-ባህሪይ ተላብሶ ይተውን እንጂ እንደወትሮው ቀልብ ሊስብ አልቻለም። በኢትዮጵያ ታሪክ ወያኔ መድብለ ፖርቲን የፈቀደ ድርጅት እንደሆነ በሙሉ አፉ ሲናገር እሱ አላፈረም። ከሱ ይልቅ የተሸማቀቁት እነ በረከት እና ስብሃት ናቸው። በልባቸው አበስኩ ገበርኩ እያሉ ... ጌታዎቹ ሃዘን ሲሰማቸው እሱ ያለቅሳል። በዚህ አቋሙ ከሶስተኛው መንገድ ወደ አንደኛው የተሸጋገረ ይመስላል ልደቱ። ለነገሩ እንጂ ለሱ … [Read more...] about ሰምሃል መለስ የገባት መተካካት – ተቃዋሚዎች ያልገባቸው መታደስ!
Ethiopia on the transition from total dictatorship: the role of individuals and organisations
“Individuals can be penalised made suffer …even killed but democracy is a destiny of humanity which cannot be averted, it can be delayed but not defeated. (Prominent Ethiopian Journalist Eskinder Nega sent letter from Kality) Source: Pen America. We have been witnessing for the last 25 years, Tigray People’s Liberation's Front (TPLF) domination of the political, economic and social sphere in the country. Power is in the hands of the few and dominated by the secretive police force, and … [Read more...] about Ethiopia on the transition from total dictatorship: the role of individuals and organisations
“ባንዶች ሀገራችሁን እንደጎዳችሁ ዛሬ ደግሞ የምትክሱበት ጊዜ ነው” ጄኔራል ለማ ገ/ማርያም
ጄኔራል ለማ ገብረማርያም የኢጣልያ ፋሺሽቶች ኢትዮጵያን በወረሩበት ዘመን በጽንዓት ተዋግተው ከነበሩት የኢትዮጵያ አርበኞች አንደኛው ነበሩ። በፈጸሙት አኩሪ ትግል ኢጣልያዊ ስለ መማረካቸውና አሁን ደግሞ ሕይወተ ሕልፈት ያጋጠማቸው መሆኑን፤ Ethiopian Media Forum የዘገበውን ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል። ጄኔራል ለማ ለሐገር ነጻነትና ክብር ካከናወኑት እጅግ የሚያኮራ ተግባር ውስጥ አብሮ ሊደነቅ የሚገባው አንዱ አስተዋጽኦዋቸው ቫቲካን በፋሺሽቱ ወረራ ዘመን ለፋሺሽት ኢጣልያ ላከናወነችው ያልተቆጠበ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ በማመልከት ከዚህ ጋር የተያያዘውን ግልጽ ደብዳቤ ማስተላለፋቸው ነው። (ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) በልጅነታቸው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሽምግልናቸው፤ በ97 እድሜያቸው ጭምር ጀኔራል ለማ ለሐገራቸው ያልተቆጠበ ጥረት ያበረክቱ … [Read more...] about “ባንዶች ሀገራችሁን እንደጎዳችሁ ዛሬ ደግሞ የምትክሱበት ጊዜ ነው” ጄኔራል ለማ ገ/ማርያም
“ምጽአተ ዐማራ” አዲስ መጽሐፍ
ይህ መጽሐፍ ባለ 657 ገፆች ነው። በዘጠኝ ምዕራፎች ተከፋፍሏል። እነርሱም፦ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መከፋፈል፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩና ዐማራው የከፈሉት ዋጋ የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ፣ የዐማራው የአንድነትና የፀረ-አንድነት ትግል ውጤት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ የፍፁማዊ ዘውዳዊ አገዛዝ የአንድነት ግንባታ ሂደት ድምድም እና የኢትዮጵያ ዳግም ብተና ጽንስ የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የኃይል አሰላለፍ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ከ1972 እስከ 2007 ዓም ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ስለ ዐማራና ስለ ኢትዮጵያዊነት ምሑራን ምን ይላሉ? የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፦ ዐማራው ላይ የደረሰው ሰቆቃ የወለደው ነፍስ አድን ድርጅት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦ የአሥራት ዘር ፍሬ … [Read more...] about “ምጽአተ ዐማራ” አዲስ መጽሐፍ
ግልፅ ደብዳቤ ለፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ
ለፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ዋይት ሐውስ 1600 ፔንሲልቫንያ አቬኑ ሰሜን ምዕራብ ዋሽንግቶን ዲሲ 20500 የተከበሩ ፕሬዚደንት ኦባማ፤ ይህንን ደብዳቤ የምጽፍሎት በኢትዮጵያ ውስጥያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ላሳውቆት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ተጎዳን፣በደል ተፈጸመብን በማለት የሚያሰማውን አቤቱታ፣ ህጋዊ ጥያቄዎችንና ሠላማዊ ሰልፎችን ሁሉ መንግሥት ከማዳመጥ ይልቅ ጉልበትንና ኃይሉን ሁሉ እንደሚጠቀም ያውቃሉ ብዬ አምናለሁ። ይህ ሁኔታ ባግባቡ ካልተያዘ በሀገሪቷና በአካባቢው ሁሉ ያልተጠበቀና አስከፊ ሁኔታ ሊከሠት ይችላል።የኢትዮጵያና የዩናትድ እስቴት አሜሪካ ግንኙነት ከ1903 ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህ የንግድና የወዳጅነት ውል ተፈራርመው ኢትዮጵያም ጥብቅ ወዳጅ ተብላ ትታወቅ ነበር። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አብላጫውን የአሜሪካን ረድኤት እንድታገኝምሆኗል። በአጸፋው … [Read more...] about ግልፅ ደብዳቤ ለፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ
My two cents to break the deadlock between the Oromos and Unity Camps
Researches recognized that many change agendas fail not because of resistance to change. It is due to wrong responses to resistances. Many people tend to think that all resistances are one and the same. And hence, they use the same response to all resistances. To give you a quick background, experts in the field agree that there are three major levels of resistances to change. People resist at Level 1 since they don’t understand the change at all. Those who resist at Level 2, they capture the … [Read more...] about My two cents to break the deadlock between the Oromos and Unity Camps
“ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”
ኢትዮጵያ ድንቅ አገር ናት። ይህ ማስደነቋ ደግሞ ከሕዝቧ መደበላለቅ ጋር ውበቷን እጅግ አጉልቶታል። ከዛሬ 40ዓመት በፊት የተጀመረው ጎሣ፣ ዘር፣ … ላይ ትኩረት ያደረገው ገዳዳ የግራ ፖለቲካ ኢትዮጵያ አላት የተባለውን የፖለቲካ ችግር ሲፈታ ሳይሆን ይበልጡኑ ሲያወሳስበውና ሕዝብን ግራ ሲጋባ እዚህ ደርሰናል። በዚያ ርዕዮት የተጠመቁ ሕዝብን ሲያስፈጁ እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ሲያመጡ አልታዩም፤ በዚያ የጎሣ ፖለቲካ ጥርሳቸውን የነቀሉም እስካሁን የማይሠራ ነገር በመሞከር በሽታውን ለአዲሱ ትውልድ እንደ ስጦታ አስረክበውታል። ለነጻነት በሚደረገው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያ ወገኖች በአንድነት ብሶታቸው፣ ምሬታቸው፣ … ሊሰማ ይገባል እንጂ በተናጠል “ፍትህ ለኦሮሞ፣ ፍትህ ለአማራ፣ ፍትህ ለኦጋዴን፣ …” የሚለው አካሄድ የትም የሚያደርስ አይመስለንም፡፡ የተጨቆንነው ሁላችንም ነን፤ የትግራይ … [Read more...] about “ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም!”










