ከትናንት ጅዳ ውስጥ በጠና ታማ እሷና ልጇ አደጋ ላይ አሉ ስለተባ ለችው እህት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ደርሶኛል። መረጃውን በዝርዝር ያገኘሁት ከሊያ ሾው ነበር፣ ታመመች የተባለችውን እህት በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ እንደደረሰኝ ወደ ጅዳ ቆንስል ደውዬ ለማጣራት ሞክሬ ነበር! በጅዳ ቆንስላ መረጃ ለማግኘት ከባድ እየሆነ መጥቷ ል፣ አንዳንዶች ኃላፊዎች ከዚህ ቀደም በማቀርባቸው ተጨባጭ ሂሶች አኩርፈው መረጃ ላለመስጠት ስልካቸውን ይዘጉብኛል፣ አንዳንዶች ደግሞ መረጃም ሆነ ጥያቄ ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም! እጅ አዙር በሆነ መንገድ የጅዳ ቆንስል መረጃው እንዳልደረሰው ተነግሮኛል! ይህች እህት በሽሜሲ ጊዜያዊ እስር ቤት በር ላይ ተጥለላች መባሉን ሰምቸ ወደ ቦታው የሚያጣራልኝ የስራ ባልደረባዬን ልኬም ነበር፣ ዛሬ ረፋድ ላይ በር ላይ ተዟዙሮ የወደቀ ሰው አለመኖሩን አረጋግጦልኛል! ይህን … [Read more...] about በጅዳ ሽሜሲ በር ላይ ወድቃለች የተባለችው እህት ጉዳይ!
Left Column
የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫ በሚመለከት የተሰጠ መግለጫና የሰላም ጥሪ
የኢትዮጵያን ችግር የመፍትሄ መንገድ በሚመለከት "ኢትዮጵያን ለማዳን እንነጋገር" በሚል ርእስ ቀደም ሲል አንድ የሰላም ጥሪ ማቅረባችንን እናስታውሳለን። መልእክቱም ባጭሩ ይህች ታላቅ ሀገር የገጠማት ችግር ሊፈታ የሚችለው በመሪዎቿና በልዩ ልዩ የተቃውሞ ጎራ በተሰለፉ የራሷ ልጆች ብቻ መሆኑን፤ መፍቻ መንገዱም ውይይትና ንግግር መሆኑን፤ ጊዜውም አሁን መሆኑን የሚያመላክት ነበር። ለዚህም ሁሉም ወገኖች ቢያንስ በችግሩ ላይ ለመነጋገር መስማማት እንዳለባቸው በመጠቆም ለሰላማዊ ውይይት እንዲተባበሩና ሃሳባቸውን እንዲገልፁልን አሳስበንም ነበር። ጥሪውን የተመለከቱ ድርጅቶችና ግለሰቦች የሰጡንን በጎ ምላሽና ማበረታቻ በምስጋናና በአክብሮት ተቀብለናል፤ ደስ ብሎናልም። የሰላም ውይይት ወደሰላም በር የሚወስድ ጠቃሚ ስልት መሆኑን በማመን ድርጅታችን ላቀረበው የውይይት መድረክ ዝግጅት ሃሳብ … [Read more...] about የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫ በሚመለከት የተሰጠ መግለጫና የሰላም ጥሪ
“ነጻነት ሰው ከመሆን የሚገኝ መብት ነው”
ግዛው ለገሰ በጣም መሠረታዊና አንገብጋቢ፣ ጊዜያዊም ጉዳዮችን አንሥቷል፤ በበኩሌ ጉዳዮቹን በማንሣቱ በጣም እያመሰገንሁት አስተያየቴን በአጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ ‹‹ህወሓት የተቋቋመው በአማራ ጥላቻ ነው፡፡ ይህን ሀቅ ሳይቀበሉ ስለነፃነት ማታገል አይቻልም፡፡ ነፃነት ደግሞ የዜግነት መበት እንጂ የወል መብት አይደለም፡፡ ነፃነት በማንነት ትግል አይገኝም፡፡›› ግዛው በጣም መሠረታዊ ነጥብና ሀሳብ አቅርበሃል፤ ነገር ግን ድብልቅልቁ ወጣብኝ! መነሻ፡--‹‹ሕወሀት የተቋቋመው በአማራ ጥላቻ (ላይ?) ነው፤›› ከዚህ ትነሣና፡-- ‹‹ይህንን ሀቅ ሳይቀበሉ ስለነጻነት ማታገል (መታገል?) አይቻልም፤›› ትላለህ፡፡ እንደምረዳው ግልጽ ያልሆነልኝ ግዛው ሁለቱን ዓረፍተ ነገሮች እርስበርሳቸውና እያንዳንዳቸውን ከነጻነት ጋር ያቆራኛቸው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ በእኔ አስተሳሰብ ምንም … [Read more...] about “ነጻነት ሰው ከመሆን የሚገኝ መብት ነው”
“HILLARY WINS” መስፍን በዙ
* የጅብ ችኩል … መቸም ይህ የአሜሪካ ምርጫ ከቅስቀሳው እስከ ትራምፕ ምርጫ ትዝታው ብዙ ነው፣ በመጨረሻው ቀንና በምርጫው ውጤት ቀን የሆንነው ግን በጣም ያጓጓና ልዩ ትዝታ ይዞ ያለፈ አጋጣሚ ነው፣ ለብዙዎቻችን ... የማልረሳውን የእኔን ትዝታ ከትዝብት ጋር ላጋራችሁ ... "እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!" የሚል መርህን ይዘው ከሚንቀሳቀሱት የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ "HILLARY WINS" "ሄለሪ አሸነፈች!" የሚል አንድ አስገራሚ ሰበር መረጃ ከሌሊት 3:34 Am ተሰራጭቶ ደረሰኝ። HILLARY WINS ከሚለው መረጃ ስር "ቲጂ ቴሌቪዥን ጠዋት ላይ የምርጫ ጣቢያዎቹን ጎብኝቶ ባገኘው መረጃ መሰረት ሄለሪ የአሜሪካ 45ኛ ፕሬዚደንት ሆነው ተመርጠዋል" በሚል የሚያትተው መረጃ አስገራሚ ነበር፣ መረጃው ለሄለሪ ደጋፊ ደስታ፣ ለትራምፕ ደጋፊ ሀዘንም ነበር ... … [Read more...] about “HILLARY WINS” መስፍን በዙ
“ለኦሮሞ ሰላም ኢትዮጵያን እናፍርስ” ያለው ሊበን ዋቆ ፍላቴ ማነው?
ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል በመደረግ ላይ ባለው ማንኛዉም አይነት ትግል ውስጥ ተሰማርቶ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ!!! አንዳንድ ግዜ እራሴንም ሆነ የሀገሬን ልጆች ክፉኛ እታዘባለሁ፣ ያለንበትም ዝብርቅርቅ ህይወት እራሳችን የፈጠርነው በመሆኑ በጣም አፍራለሁ። ለዚህም ነበር የስው ልጅ ማንነት መለኪያ ስለሆኑት ሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች እውቀት፣ እምነትና ብልህነት ለመፃፍ የተነሳሳሁት። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ የሆንን ኢትዮጵያውያኖች እምነትና ብልህነት እንደ ቁምጣ ያጥረናል ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ምክንያቱም ማንነቱንና የሚሰራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ትውልድ ሁሉ በቀላሉ ወደ ነፈሰበት አብሮ አይነፍስምና። ሰሞኑን ለንደን ላይ የኦሮሞ ልጆች ተሰባስበው ወጥና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲመክሩ እንደ ሰነበቱ ሁላችንም የምናውቀው ነው። በዚሁ ስብሰባ … [Read more...] about “ለኦሮሞ ሰላም ኢትዮጵያን እናፍርስ” ያለው ሊበን ዋቆ ፍላቴ ማነው?
ያለም ገዥ
ኮሳሳ አገዝፎ፣ ግዙፍ አኮስሶ የሾመውን ሽሮ፣ያሻውን አንግሶ በለወጠው አዲስ ክስተተ ሁኔታ ሀዘንና ደስታ፤ ደስታና ሀዘንን አቀያይሮ ቦታ በራሱ ህግጋት ዘመኑን ዳኝቶ ጊዜ ነው የሚኖር ዓለማችን ገዝቶ። ጥቅምት 2009 አብርሃም በየነ … [Read more...] about ያለም ገዥ
መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
ለኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው እርቅና መግባባት መሆኑን ከሚጠቁሙና ከዚያ አልፈው የሽምግልናና የማግባባት ስራ ከሚሰሩ ስብስቦች አንዱ "መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ነው። ዛሬ ከመድረኩ ሁለት አባላት በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን የ"መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ እና የመድረኩ አባል ዶ/ር ገበየሁ እጂጉ ናቸው። ያዬ አበበ ፎረም 65 አስተባባሪ … [Read more...] about መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያ መድረክ
የ“ጥልቅ ተሃድሶ” ድራማ ተጀምሯል!
በቤተ ሙስና፣ የ"ጥልቅ ተሃድሶ"ው ድራማ ተጀምሯል! የእርስ በርስ እና ራስን በራስ መተካካት ቧልት እና ፌዝ። ከመጋረጃው ጀርባ ስብሃት ነጋ፣ አቦይ ጸሃይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ደብረጽዮን እና በረከት ስምኦን የሚቆምሩትን ካርታ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደቬጋስ አጫዋች ፊት እያመጣ ይዘረጋዋል። በዲዮጋን ያደረጉት አብዮታዊ እና ልማታዊ "ምሁራን" ፍለጋ ውጤት ነበረው። "የዶክተር ያለህ" ፍለጋ ጥቂት ታማኝ አገልጋዮችና፣ በርካታ ሮቦቶችን አስገኝቷል። "በዲሞክራሲ" በተመረጠው "የህዝብ ምክር ቤት" የሚኒስትሮቹ ስም ይፋ በሆነ ግዜ፤ ለይስሙላ እንኳን ተቃውሞ፣ አልያም ድምጸ-ተአቅቦ ቢያደርግበት ድራማውን ያሳምረው ነበር። በሙሉ ድምጽ ጸደቀ ተባለ። የነዚህ ሮቦቶች ምርጫ የፍልፍሉን ቀልድ ያስታውሷል። የድሃው ልጅ ለሃብታሙ ልጅ፣ "ምን ያንጠባርርሃል? አንተም የምትበላው አንድ እንጀራ፣ እኔም … [Read more...] about የ“ጥልቅ ተሃድሶ” ድራማ ተጀምሯል!
የተባበረችውን ኢትዮጵያ በጋራ እንገነባለን
በቅርቡ በአንድ የኦሮሞ ወገኖች ስብሰባ ላይ አንድ ሰው ኦሮምያ ሰላም የምታገኘው ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ነው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት አለ ተብሎ ሲራገብ እያየን ነው። እኔ በግሌ የዚህን ሰው ተልእኮ ለመረዳት ቅንጣት ጊዜ አልወሰደብኝም። ከራሱ ከወያኔ በቀጥታ መልእክት እየተቀበለ የሚሰራ የወያኔ ተቀጣሪ ነው ወይም እያጃጃሉ በስልት የሚጠቀሙበት ሰው ነው። አለቀ። ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ነገር እንደሚታወቀው ይህ መንግስት ገና ሲመሰረት ጀምሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለው መሳሪያ ህዝባዊ ድጋፍ አይደለም። በዚህ ጎጠኛ የፓለቲካ አስተሳሰቡና በሙስና ድር በተፈጠረ ሥርዓት ምን ጊዜም ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ አያስብም። ይህንን መንግስት በሚገባ ያውቃል። ይህን ስርዓት እድሜ ይቀጥልለታል ተብሎ የሚታሰበው ስልት ቅራኔ ነው። ለዚህም ነው መንግስት ከህገ መንግስቱም በላይ … [Read more...] about የተባበረችውን ኢትዮጵያ በጋራ እንገነባለን
ይረገም!!
በክፉ ያነሳ ወርቃማውን ስምሽን፣ በሃሜት ያጎደፈ ፀዐዳ ክብርሽን፣ በክፋት ፈረሱ ወዳንቺ የጋለበ፣ በእሾኸም ምላሱ ሊወጋሽ ያሰበ፤ ሰላምሽን የነሳ፣ ባንቺ ላይ ሊሳለቅ፣ ሊቀልድ የቃጣ መልካም ህይወት ትክዳው! ነፍሱ ሰላም ትጣ!! ብርሃንሽን ሊያጠፋ ውበትሽን ሊያከስም፣ መዐዛሽን ሊበክል ህይወትሽን ሊያጨልም፣ በክፋት ያቀደ በሻገተ ህሊናው፣ ብርሃኑ ይደፈን ! ጨለማ ይውረሰው! ስትለመልሚ ስትፈኪ አይቶ፣ በአርኪ ፈገግታሽ በቅናት ተውጦ፣ የቆሸሸ እጁን ባንቺ የዘረጋ፣ ሽባ ይሁን ይስለል! አንደበቱ ይዘጋ! የዘመናት ስምሽን ዝናሽን ሊያጎድፍ፣ ከባዕድ አብሮ ወዲያ ሲያነፈንፍ፣ ህይወቱን በሙሉ ሳይሰራ ቁም-ነገር፣ ገብቶ ሲሽሎኮሎክ ከጢሻ ከቆንጥር...፤ ሊነክስ ያደባ የጠባውን ጡትሽን፣ ሊያጠፋ የቃጣ ሃቀኛውን ልጅሽን፣ የታሪክ መጠሪያ ቅርሳ-ቅርስ … [Read more...] about ይረገም!!










