ከውጪ ሀገር የመጡ ሰዎች ለአፄ ምኒልክ ስለ ፎቶግራፍ እንዲህ ብለው አስረዷቸው "በአውሮጳ አንድ ትንሽ ሳጥን አለች ሰውን፣ ፈረሱን፣ ቤተመንግስቱን ሁሉ ወደ ሳጥኗ ታስገባና ሁሉን ትንሽ አርጋ ታሳያለች" አሏቸው። ምኒልክም በሰሙት ነገር ተገርመው እንዴት ይሆናል ይሄን ነገር ማየት አለብኝ ብለው የፎቶ ማንሻ እንዲመጣ አዘዙ። የፎቶ ማንሻውም (ካሜራ) ከእነ አንሺው በ1875 ዓም ወደ ሀገራችን ገባ። ሆኖም ግን አጼ ምኒልክ ፎቶውን ሊነሱ ሲሉ ቀሳውስቱ መኳንንቱ ከለከሏቸው፣ ርኩስ ነገር ነውና አጥፉልን አሏቸው። ምኒልክም "እግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር አታርጉ፣ አትንኩ፣ ነውር ነው ማለት አምላክን መቃውም ነው እንዲህ ያለ ሀሳብ አታስቡ ዞር በሉ ከፊቴ" ብለው ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ም አጼ ምኒልክ የምትመለከቱትን የመጀመሪያ ፎቶ ተነሱ። መልካቸውንም በማየታቸው … [Read more...] about ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
Left Column
ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫሎች ላይ የቦይኮት (እቀባ) ዘመቻዎች ተነስተው ነበር። የዘመቻዎቹን ውጤቶችም አይተናቸዋል። በዚች አጭር ጽሁፌ የማተኩረው በውጤቶቹ ላይ አይደለም። በሲያትሉም ሆነ በሮም ዝግጅቶች ላይ ስለነበርኩ፣ የቦይኮት ዘመቻዎቹ ከጅምሩ ጥቅም እና ጉዳቶችን አመዛዝነው ነበር ወይ የሚለውን በጥቂቱ ለመፈተሽ እሞክራለሁ። በዚህ ርዕስ ላይ ስጽፍ አዋራ እንደሚነሳ አምናለሁ። በጉዳዩ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲወያዩ ብታዘብም በፍርሃት ይሁን በሌላ ምክንያት ሃሳባቸውን በአደባባይ ለመናገር ግን ሲደፍሩ አይታይም። ሃሳባቸውን በድፍረት የሚሰነዝሩ ወገኖችም ቦይኮት ስለሚደረጉ ብዙዎች ዝምታን ቢመርጡ አይደንቅም። "አህያ የለኝ ከጅበ አልጣላ" ብሎ ሃሳቡን በነጻ ለመግለጽ የሚሞክር ደግሞ ይሰደባል። በሳይበሩ አለም፣ ወቅትን እየጠበቀች በምትነደው … [Read more...] about ኳስ እና የ“ቦይኮት” ፖለቲካ
መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በዲሴምበር 5, 1989 ዓ.ም. በምስራቅ ጀርመኗ የድሬዝደን ከተማ ነዋሪው በነቂስ ወደ ጎዳና ወጥቶ ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያሰማ ነበር። የተቃውሞው ኃይል እየበረታ ሲመጣ ህዝቡ ወደ አንድ ህንፃ መትመም ጀመረ። ላለፉት 40 ዓመታት የራሱን ህዝብ መተንፈሻ በማሳጣት ከፍተኛ አፈና ያደርግ ወደነበረው የደህንነቱ መስሪያ ቤት፥ወደ ''ሽታዚ'' ተብሎ ወደሚጠራው መስሪያ ቤት። ጥቂት ወጣቶች ግን የሽታዚን ቢሮ ሰብሮ ከገባው ህዝብ በመነጠል በጥቂት ሜትሮች ርቀት ወደሚገኝ አንድ ህንጻ አመሩ።የወጣቶቹ ወደ ህንፃው እየተጠጉ መምጣት ያሳሰበው የጥበቃ ሰራተኛ በፍጥነት ወደ ውስጥ ዘልቆ በመግባት አንድ ቀጭን እና አጭር የሆነን የ37 ዓመት ሰው አስከትሎ ወደተሰበሰቡት ሰዎች አመራ። ያም ቀጭኑ ሰው ጥርት ባለ ጀርመንኛ ''ይህ ህንፃ የሶቭየት ህብረት … [Read more...] about መንግስት እንደ ሞስኮ ጣና እንደ ፑቲን!
የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት
የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት - ያኔ ነው ያበቃለት! ከቶውን "የአለምን ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር" የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ አይሆንም። ይነፋ የነበረው የእድገት ቀረርቶ እና ይነገር የነበር ሁለት ዲጅት እድገት ቁጥር ሁሉ ውሸት ነበር፣ ወይንም ደግሞ የሃገሪቱ ሃብት በጥቂቶች እየተዘረፈ ነው። ጆሮን ያሰለቸው የ"እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ" ዘፈን ቀዝቀዝ ማለት ሲጀምር የ "ደብል ድጅቱ" የፈጠራ ተረት እንደ በረዶ እየነጻ መሄዱ አልቀረም። እድገቱ የህዝቡን ህይወት አልለወጠም። ተጀምሮ ከሚቋረጥ ህንጻ … [Read more...] about የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት
ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ቅኝት - መስፍን ማሞ ተሰማ የቃኚው ማስታወሻ፤ ጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ጁላይ 2 / 2017 “ራስ እምሩን በተመለከተ” በሚል ርዕስ አንድ ፅህፍ ለንባብ አብቅቷል። ይህ የጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣን አቋም ያንፀባረቀው ፅሁፍ ሙያዊ ሥነምግባርን (ፕሮፌሽናል ኤቲክስ) ከብቃትና ከሃላፊነት ጋር ያዋደደ ስህተቱንም በግልፅና ያለማወላወል የተቀበለና ለእርማቱም መፍትሄን ያመላከተ መሆኑ የድረገፁን ዝግጅት ክፍል የሚያስወድሰውና በአርአያነትም ከመጀመሪያው ረድፍ የሚያቆመው ይሆናል። የሚዲያ ተልዕኮ መሰረቱ እንዲህ ሲሆን ተዓማኒነቱንና ሚዛናዊነቱን ያረጋግጣልና። በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በተፃፈው ‘አዳፍኔ’ መፅሀፍ ላይ ክቡራ ልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ በአርበኝነታቸው ሳይሆን ‘ከጣሊያን ደሞዝ ተቆራጭ የሆነላቸው ባንዳ’ ተደርገው ከባንዶች የስም ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው ለዚህ ቃኚ … [Read more...] about ትዝታ – ሀዲስ አለማየሁ
ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
ስምህን ሳላነሳ፣ ምኑን ሆንከው ፀጋ ለአብሮነት መኖር፣ እየሆንክ አደጋ፣ አድርገህ ከያዝከው፣ የሙሉቀን ሥራ ለማቃባት ደም፣ ኦሮሞን ካማራ። ‘ጀሃዳዊ ሃረካት’፣ እና ‘አኬል ዳማ’ በለምለሟ አርሲ፣ በአኖሊ ከተማ ወያኔ ያቆመው፣ የጥላቻ ሃውልት የተሸከመው እጅ፣ የተቆረጠ ጡት ሆነ ውጤት አልባ፣ አነሰ አሉህ እንዴ አሽከርካሪዎችህ፣ ፍጠር ሌላ ዘዴ? ጦርና ጎራዴ ሕዝቡን ለማማዘዝ ድንገት ቱግ ብለህ፣ የምትረጨው መርዝ። ዕውቀት ነበርኮ፣ ወገንን ለመጥቀም ተከባብሮ እንዲኖር፣ ተዋዶ በሰላም አየ ያንተስ መማር፣ “በረከተ መርገም”!! ተስፋ ለቆረጠ፣ ቀን ለጨለመበት ለጭቁን ወገኑ፣ መላ ለጠፋበት ታጭዶ ለሚወቃው፣ በአግዓዚ ጥይት በአላሚ እሩምታ፣ በቅሊንጦ ታጥሮ ዶጋመድ ለሆነው፣ በሳት ተንጨርጭሮ ፍዳውን ለሚያየው፣ እሥር ቤት ታጉሮ እርቃኑን ለቀረው፣ … [Read more...] about ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
The story of Nigist Yirga: one brave girl among thousands in TPLF terror House
Nigist Yirga Tefera is a twenty-four-year-old girl and a resident of kebele18 in Gonder City. As most of the youth in Ethiopia she is craving for fair governance, equality, democratic rights and an end to extremely corrupt and ethnocentric rule.Standing up for her basic rights took her to Kaliti prison cell since June 2008. Nigist is accused by the TPLF court with terrorism, helping terrorist organizations and participating in and organizing demonstrations against the regime.Her case was heard … [Read more...] about The story of Nigist Yirga: one brave girl among thousands in TPLF terror House
New book unveils 12 soft skills that make or break one’s success
FOR IMMEDIATE RELEASE Press Release Soft Skills That Make or Break Your Success: 12 soft skills to master self, get along with, and lead others successfully by Assegid Habtewold- a leadership expert and soft skills workshop facilitator, is now available. The book is based on a story and shares great insights, approaches, and tools essential to develop the 12 vital soft skills that make or break one’s success. Silver Spring, MD, July 13 … [Read more...] about New book unveils 12 soft skills that make or break one’s success
ያለ ውክልና ግብር እየሰበሰበ ያለው ህወሓት ባዲስ የጀመረው የገቢ ግብር ሕይወት አጠፋ
አንዳች የሕዝብ ውክልና ሳይኖረው በተገንጣይ ነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ህወሓት ሰሞኑን በአዲስ አበባ አነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እየጣለ ያለው የግምት ገቢ ግብር ሕዝቡን አማርሯል ለሞትም ዳርጓል፡፡ አዲስ አድማስ ያተመው ዘገባ እንዲህ ይነበባል:- የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ሰሞኑን በአነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እየጣለ ያለው አዲሱ የግምት የገቢ ግብር ተመን ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ ከዚሁ የቀን ገቢ ግምት ጋር በተያያዘ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የተጣለባቸውን የቀን ገቢ ግምት ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮባቸው በድንገት ወድቀው ህይወታቸው ያለፈው አቶ አጎናፍር፤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሰፈር ውስጥ በከፈቷት የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ነበር … [Read more...] about ያለ ውክልና ግብር እየሰበሰበ ያለው ህወሓት ባዲስ የጀመረው የገቢ ግብር ሕይወት አጠፋ
ካየሁት ከማስታውሰው
ማስታወሻ ከቃኚው፤ ይህ የልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ መፅሀፍ ቅኝት በቅድሚያ ጥቅምት 2004 ዓ/ም - ኖቬምበር 2011- በሌሎች ድረገፆች ላይ ለንባብ ቀርቧል። በዚህ ወቅት በጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ላይ መቅረብ ያስፈለገበት ምክንያትም በቅርቡ ጎልጉል 'የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ' በሚል በግንቦት ወር ላይ አርበኞቻችንን ለመዘከር ባወጣው ፅሁፍ ራስ እምሩ ከ'ባንዳዎች' የስም ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ባስነሳው ውዝግብ ነው። ይህ ፅሁፍ/ቅኝት እዛ ውዝግብ ውስጥ አይገባም። ሆኖም ክቡር ልዑል ራስ እምሩ ሀገራችን ከነበረቻቸው ታላላቅና ስመጥር ኢትዮጵያውያን አርበኞቻችን አንዱ መሆናቸውን ቃኚው የሚያምንና እጅግም ከበሬታ ያለው በመሆኑ በህይወት ዘመናቸው ፅፈው የተዉልንን ማስታወሻ መመርመሩ መቃኘቱ ተገቢ መሆኑን ስላመነበት እነሆ የተከበረው የጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ፈቃዱ … [Read more...] about ካየሁት ከማስታውሰው










