በህወሓት ትዕዛዝና አርቃቂነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነውን "ሕገ መንግሥት" "አርቃቂ" ኮሚሲዮን በሊቀመንበርነት የመሩት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ "ከዚህ በፊት ህገ መንግስቱን ስናፀድቅ ህዝቡ በቀጥታ አልወሰነበትም፡፡ በተወካዮች በኩል ነው የወሰነው" በማለት ከሌሎች አዲስ አድማስ ቃለ meጠይቅ ካደረገላቸው ግለሰቦች ጋር በመሆን "የማይገሠሠው ሕገ መንግሥት" "ክብሩ"ን አውርደውታል፡፡ ዘገባው እንዲህ ቀርቧል:- በፓርቲዎች ድርድር ኢህአዴግ፤ “ልደራደርባቸውም አልችልም” በሚል ውድቅ ካደረጋቸው አጀንዳዎች አንዱ የህገ መንግስቱ መሻሻል ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ህገ መንግስቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር መቅረብ የሚችል አይደለም? ኢህአዴግ ለምን ለድርድርና ለውይይት እንዳይቀርብ ፈለገ? ህገ መንግስቱ ሲጸድቅ ተሳትፎ የነበራቸው አንጋፋ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ምሁራን አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡ … [Read more...] about ሕገመንግሥቱ የፀደቀው በቀጥታ ሕዝቡ ወስኖበት ሳይሆን በተወካዮች ነው – ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ
Left Column
የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
ራዕይ ለኢትዮጵያ - Vision Ethiopia Vision Ethiopia and ESAT Fourth Conference Second call for papers, July 3, 2017 Conference Theme: Building Democratic Institutions in Ethiopia የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት Vision Ethiopia, an independent network of Ethiopian scholars and professionals, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT), is pleased to announce that the Fourth Conference will be held in Washington D.C. on September 16 and 17, 2017. We thank those who … [Read more...] about የዲሞክራሲ ተቋማትን በኢትዮጵያ ስለመግንባት
“ደግ ሰዉ አለፈ ..”
አባት ያቆየዉን ልጅ እዲጠብቀዉ የተከበሩ ኮ/ል አስናቀ እንግዳ፤ ኢትዮጵያን ለሚረከበዉ ወጣት ትዉልድ አዘዉትረዉ እንዲህ ይሉ ነበር። "አንተ የዛሬ ትዉልድ ሆይ! አንድ ጊዜ ቆም ብለህ አዳምጠኝ። ከተቻለ አባቶችህ ከሠሩት ላቅ ያለ፤ በስተቀር የእነሱን ያህል ካልሠራህ ሐገር አይኖርህም። የእኔ ትዉልድ በስልጣኔ ኋላ ቀር ቢሆንም፤አባቶቹ ከሠሩት በላይ አከናዉኖ አደራዉን ተወጥቶ፤ሀገሪቱን አስረክቦሃል።አንተም ለልጆችህ ይህችን ጥንታዊ ሐገር በክብር ለማስረከብ እንድትችል፤ ወኔ ይኑርህ። ወኔ እንዲኖርህ ለሆድህ አትገዛ። ኩራት ራት ነዉ ብለህ፤ ለራስህ ኀሊና ተገዛ " ይሉ ነበር። እንግዲህ ይህን የመሰለ ቁምነገር ሲያስተምሩ የኖሩ አባት፤ የወጣትነት ጊዚአቸዉ ምን እንደሚመስል ከአርበኝነትና ከጠቅላላ የትግል ታሪካቸዉ የቀነጨብኩትን ከዚህ በታች በግጥም እያቀረብኩ፤ኮ/ል አስናቀ እንግዳ በርግጥ … [Read more...] about “ደግ ሰዉ አለፈ ..”
ይድረስ ለአርበኛው ጸሐፊ ዕዝራ ዘለቀ (ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ)
በተከታታይ የጻፍካቸውን ሁለት ግሩም መጣጥፎች በፍቅር አነበብኳቸው፡፡ በነዚህ ጽሑፎች እንደተረዳሁት ጥሩ አንባቢ ነህ፤ የብዕር አጣጣልህም ውብ ነው፡፡ ሀገርህንም እንደምትወድ በጽሑፍህ ብቻ ሣይሆን በረሃ መውረድህ ራሱም በቂ ምሥክር ነው፡፡ ማቄን ጨርቄን ሳትል ለአንዲት እናትህ ኢትዮጵያ ስትል እያሳለፍከው ያለኸውን መከራና ስቃይ መረዳት እችላለሁና የእምዬ አምላክ ይከተልህ፡፡ አንተን ብቻም ሣይሆን ለተመሳሳይ በጎ ዓላማ የተሰለፋችሁትን ጓዶችህንም ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ፤ ያሰባችሁትንም ያሳካላችሁ፡፡ በረከቱ የሁላችንም ነውና፡፡ እኛም በጸሎት ከጎናችሁ አለን፡፡ ይሁንና በግልጽ መነጋገር ለሁሉም ወገን የሚበጅ እንደመሆኑ ከጽሑፍህ ለመረዳት የሞከርኩትን በግልጽ የተነገሩና ያልተነገሩ አንዳንድ ነጥቦችን ማንሳት ወደድኩ፡፡ ከብረት ዝገት ከሰው ስህተት እንደመገኘቱ ተሳስቼ የተረዳሁብህ ነገር … [Read more...] about ይድረስ ለአርበኛው ጸሐፊ ዕዝራ ዘለቀ (ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ)
…ቅምሻ…
በቀረችው ትንፋሽ ... አገሩን አስታሞ ... እሱም እንደ ሌሎች ... ሊያሸልብ ነው ደግሞ! .......................................................... እንደ ሸረሪት ድር ... ነገር ተወሳስቦ... እውነትን ማን ያውጣት ... ከመሃከል ስቦ...? ......................................................... አገር ተሰቃየች...ጣሯ ብቻ በዛ.. ግማሹ እየሸጣት...ግማሹ እየገዛ...! ......................................................... የሰው ዘር መገኛ ... ብለው ሲጎበኙን... በብሄር ተጠምደን ... ተከፋፍለን አዩን:: ......................................................... ማን እንደዘረፈኝ ... ልቤ እያስተዋለ የለመደው … [Read more...] about …ቅምሻ…
አንድነት ከማን ጋር? አንድነት ለምን? አንድነት መቼ?
ዐማራው በባህሉ፣ በሥነ-ልቦናውና በፖለቲካ ታሪኩ እንዲሁም በሚጋራቸው የወል ዕሴቶቹ፣ በእሱነቱና በኢትዮጵያዊነቱ መካከል የተሰመረ ልዩነት ባለመኖሩ፣በዘር ጠላትነት ተፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምበት ፣ወንጀሉ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚፈጸም ነው በማለት፣ለምን? እንዴት? ብሎ ለመጠየቅ ከሁለት ዓሥርተ ዓመታት በላይ እንደፈጀበት በግልጽ ይታወቃል። ይህም ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድንና አጋሮቹ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፉ ሠፊ ዕድልና አጋጣሚ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። ይህን ያህል ቁጥር ያለው ከትግሬ፣ ከሶማሌ፣ ከጉራጌ፣ ከሲዳማ፣ ከወላይታ ቢጠፋ ሁሉም የነገዱ አባሎች ጠፉ ማለት ነበር። ዐማራው ይኸን ያህል ቁጥር የሰው ኃይል ጠፍቶበት፣ ምንም ያልመሰለው ከጣና ሐይቅ በጭልፋ ውኃ የመቀነስ ያህል ሆኖ በመታየቱ፣ የሁሉንም የዐማራውን ነገድ ጆሮ … [Read more...] about አንድነት ከማን ጋር? አንድነት ለምን? አንድነት መቼ?
አውቀን እንታረም
ደራሲ፤ አቢይ አበበ (ሌ/ጄኔራል) ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ ዓለም ገና ልጅ ናት አውራጃዋም ደግሞ አርጅቶ የሚሞተው ሰው ብቻ ነው ቀድሞ ብዙ አሳልፋለች ብዙዎች ተክታ የሁሉንም ምግባር በየተራው አይታ። ሌ/ጄ አቢይ አበበ እንዲህ ሆነ፤ ርዕሱን አነበብኩና ደራሲውን ስመለከት ሌተናንት ጄኔራል ይላል። የህትመት ዘመኑ ደግሞ 1955 ዓ/ም። ባለሁበት ዘመን ውስጥ ሆኜ ሳሰላው እንግዲህ መፅሀፉ ከታተመ ግማሽ ምዕተ ዓመት አልፎታል። ህትመቱስ? አስቀድሞ አሥመራ በ”ኢል ፖሊግራፊኮ ሶ. አ” ማተሚያ ቤት የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር ኤርትራ ዋና ከተማ ሲሆን እርግጥ ከ12 ዓመት በሁዋላ በ1967 ዓ/ም (ዘመነ ፅልመት) አዲስ አበባ በቼምበር ማተሚያ ቤት በድጋሚ ታትሟል። ስለምን ዘመነ ፅልመት አልነው 1967 ዓመተ ምህረትን? አንባቢ ቅኝቱን አስጀምሮ ካስጨረሰህ ምላሹን … [Read more...] about አውቀን እንታረም
Many into one Africa, one into many Africans
“I know no national boundary where the African is concerned. The whole world is my province until Africa is free.” - Marcus. M. Garvey. The expression of many identities is seen as the celebration of diversity and a legitimate vehicle for claims to political and other forms of rights. The resolution of diverse identities into compound /combined identities and unities is often suspect bearing the implication that rights and diversity might be sacrificed in the process of bringing about a new … [Read more...] about Many into one Africa, one into many Africans
የጋራ የሆነች ኢትዮጵያ እንዴት እንመሠርታለን?
እስካሁን ለምን በተደጋጋሚ ከሸፍን? እንደምን አላችሁ፣ አሰላሙ አሌይኩም፣ አካም ጂርቱ፣ እንደምን አረፈዳችሁ (good afternoon everyone)። የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ በዚህ ስብሰባ ላይ እንድናገር ስለ ጋበዘኝ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ። ከእናንተ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በመሆን ስለምትወዷት አገራችን የወደፊት ሁኔታ ለመወያየት መብቃት ታላቅ ዕድል ነው። በአሁኑ ወቅት አገራችን በከባድ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፤ ይህም ቀውስ በአንድ ጊዜ የተከሰተ ሳይሆን ለዓመታት ሲጠራቀምና ሲከማች የቆየ ነው። የአገራችን የወደፊት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስበን በመሆኑ እናንተም ይህንኑ ሃሳብ እንዳቀርብ በጠየቃችሁኝ መሠረት እኛ ኢትዮጵያውያን በኅብረት በመሥራት ለአገራችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ማምጣት እንዴት እንደምንችል ሃሳቤን … [Read more...] about የጋራ የሆነች ኢትዮጵያ እንዴት እንመሠርታለን?
መቼ ነው እውነተኛው የትግል ማዕከል የሚፈጠረው?
መክሸፍ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፤ መገለባበጥ እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ዛሬም እንዳምናና ታቻምናው፤ ታጋዩን ክፍል ወደ አንድ ለማስባሰብ የሚሯሯጡ ሞልተዋል። ዛሬም የሃሳብ እና የተግባር አንድነት ብቻ ሕዝቡን ለድል እንደሚያበቃ መሰበኩ አላቋረጠም። የነበረው ተመክሮ ሳይፈተሽ፤ በፍላጎትና በምኞት ላይ ብቻ በመመርኮዝ፤ አዲስ ተዋንያን አዲስ ቅኝት ይዘው ወደ መድረኩ ብቅ ይላሉ። አሁንም ከመልሱ ይልቅ ብዙ ጥያቄዎችን ያነገበ ሂደት ቦታውን ወርሷል። ነበርኩበት። አልፌበታለሁ። እስካሁን ቦታውን ይዞ የነበረው፡ “ምንም ይሁን ምንም፤ ኢትዮጵያን እናድን!” በሚልና፤ “ሁላችሁም የያዛችሁትን እርግፍ አድርጋችሁ በመተው፤ እኛ በምንላችሁ ተሰባሰቡ!” የሚል ነበር ጥሪው። የዛሬው ግን ለየት ያለ ነው። የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል ሆነና፤ በሥልጣን ላይ ባለው የትግሬዎች ገዥ ቡድን … [Read more...] about መቼ ነው እውነተኛው የትግል ማዕከል የሚፈጠረው?










