በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ የፖለቲካ አካሄድ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያመጣል የተባለው የሰሞኑ ምርጫ ውጤት ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት የመንፈስ ልዕልና አጎናጽፏቸዋል፡፡ በበርካታ ችግሮች ለተወጠረችው ናይጄሪያ “ብሩህ ጊዜ” ያመጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን በምክትልነት ናይጄሪያን እያገለገሉ በነበሩበት ጊዜ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዑማሩ ሙሳ ሕይወታቸው በማለፉ ወዲያው የፕሬዚዳንትነት መንበሩን ተረከቡ፡፡ ዑማሩ ሙሳን ተክተው ጥቂት እንዳገለገሉ በወቅቱ በተካሄደ ምርጫ ሙሐማዱ ቡሃሪን አሸንፈው ናይጄሪያን ለአምስት ዓመታት መርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የዛሬ አምስት ዓመት ባሸነፏቸው መልሰው ተሸንፈው ሥልጣናቸውን በሰላም አስረክበው በናይጄሪያ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ተግባር በመፈጸም ስማቸውን ከመቃብር በላይ ህያው አድርገዋል - ፕሬዚዳንት ጉድላክ … [Read more...] about መጪው ጊዜ ለናይጄሪያ “ብሩህ” ይሆናል!!
Full Width Top
“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ
“የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል ሲለኝ - ደነገጥኩ” የሚል አስተያየት የሰጠው ኳስ አፍቃሪ ከጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል ጋር የተገናኘው አዲስ አበባ ስታዲየም ነበር። ጉዳዩ ለሚዲያ ግብዓት እንደሚውል ባይረዳም ገጠመኙን ለመናገር የተገደደው ስለ ምርጫ አንስተው ሲወያዩ ነው። ድንገት ተገናኝተው ቆሎ በመገባበዝ የጀመሩት ጨዋታ ዘጋቢውን ወደ 1997 ምርጫ ትዝታ ወረወረው። ተግባብተው አወጉና ተለያዩ። የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል!! ለምን? መርዝ ዘርቶ በጥይት ለማጨድ? የስታዲየሙ ሰው የመኪና ማስጌጫ ለመግዛትና ለማስገጠም ሰባራ ባቡር እንደሄደ ይናገራል። እዛም እንደ ደረሰ የሚፈልገውን ገዝቶ እያስገጠመ ሳለ አንድ ጎረምሳ ቢጤ ይጠጋቸውና ወሬ ይጀምራል። ጎረምሳው የትግራይ ተወላጅ ነው። አንዳንድ ማስጌጫዎች የሚፈልግ ከሆነ እሱ ዘንድ በርካሽ እንደሚያገኝ እየነገረው ቃላት መለዋወጥ ጀመሩ። … [Read more...] about “የትግራይ ተወላጆች ታጥቀናል” ሲለኝ – ደነገጥኩ
“የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት መዋቅር ውስጥ ተመድበው የሚያገለግሉ የሰለላ ሰራተኞች በጽናት መስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ለዓመታት የስለላ ሠራተኛና የአዲስ አበባ ቀጠና ኦፊሰር የነበረች የህወሃት አባል መክዳቷ ታወቀ። የጎልጉል ታማኝ የዜና ምንጮች አንዳሉት ድርጅቷ ህወሃትንና ታላቁን የአፈና ተቋም የስለላ ኦፊሰር የነበረችው የመክዳት ውጥኗ እውን የሆነላት ከስድስት ዓመት በኋላ ነው። በተደጋጋሚ ጊዚያት የዲፕሎማት ቪዛ እንዲሰጣት ፓስፖርቷን ለኢሚግሬሽን ብትልክም ያልተሳካላት ይህቺ የስለላ ኦፊሰር፣ በመጨረሻ የተሳካላት ስፔን አገር ለስለላ ስልጠና በማግኘቷ ነው። አዲስ አበባ የሚገኙ ባልደረቦቿ “እርሷ ዕድለኛ ናት” በማለት ለጎልጉል ዘጋቢ እንዳሳበቁት፣ ኦፊሰሯ ስፔን አገር ከባልደረቦቿ ተለይታ ያመራችው ወደ አሜሪካ ነው። እዚያም እንደ ደረሰች … [Read more...] about “የስለላ ሰራተኞች መሯቸዋል፤ በጽናት የሚሰራ የለም”
ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
ኦነግ ሲከተል የነበረው መንገድ ስህተት እንደነበር በይፋ በመናገር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የተሰኘውን አዲስ ድርጅትና ወኪሎች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት አቶ ሌንጮ ለታ ተቀባይ በማጣታቸው ወደመጡበት የተመለሱት ኦህዴድ ባቀረበው ተቃውሞ መሆኑ ታወቀ። የኢህአዴግ አፈ ቀላጤ የስላቅ መልስ ሰጡ። ኦዴግ (ኦዲኤፍ) በ2012 ምርጫ ሊጋበዝ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታል። የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በመነጠል ከኢትዮጵያ (“አቢሲኒያ አገዛዝ”) መገንጠልን አማራጭ አድርጎ ለግማሽ ምዕተ አመት ሲወድቅ ሲነሳ የኖረውን ኦነግ ሲመሩ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ተቃውሞ ደርሶባቸው ነበር። የቀድሞው የትግል ጉዞ ስህተት እንደነበር በይፋ አስታውቀው ለድርድር ኢህአዴግ ደጅ የዘለቁት አቶ ሌንጮ ከጉዟቸው በፊት የተነሳባቸውን ተቃውሞ … [Read more...] about ኦህዴድ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ላይ ጀገነ
በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል”
ኢህአዴግ በሥልጣን በቆየባቸው 25 ያህል ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ መቶ ዝሆኖች ውስጥ ከዘጠና በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፣ ወደ ጎረቤት አገር ተሰድደዋል፣ የደረሱበት አይታወቅም፣ . . . ሲሉ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ዛሬ (አርብ) ዘግበዋል፡፡ የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ ኢህአዴግ ከቻይና ጋር ከተፋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የዝሆን ቀንድ ንግድ እየተጧጧፈ እንደሄደ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በዚህም “ጮማ” ንግድ ውስጥ ቢጂንግን፣ ሲንጋፖርን፣ ታይላንድን፣ … መመላለሻቸው ያደረጉ ቱባ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ይጠረጠራሉ፡፡ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል”
“ስሉሱ” ዞረ እንዴ?!
ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ ሁኔታ ኢህአዴግ ላይ ታዋቂ የዓለማችን ጋዜጦች የጀመሩት ተከታታይ ትችት፣ ማሳሰቢያና መፍትሔ ጠቋሚ ዘገባዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነዋል፡፡ ሚዲያዎቹ በዘገባቸው ኢህአዴግን ከቻይና አምባገነናዊና አክራሪ አገዛዝ ጋር አመሳስለዋል፡፡ ኢህአዴግ እከተለዋለሁ የሚለውን የኢኮኖሚ መርህ ከቻይና የተኮረጀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም ሆነ መድረሻው ግራ የሚያጋባና የማይታወቅ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ጋዜጦቹ ኢህአዴግን በሚንከባከቡት መንግሥቶቻቸው እና በራሱ ኢህአዴግ ላይ የሰላ ሒስ መሰዘንዘር መጀመራቸው የፖሊሲ አውጭዎችን አስተሳሰብ የሚያስቀይር ከመሆን አልፎ ኢህአዴግ ላይ “ስሉሱ” ዞሯል የሚያስብል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ “ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” በሚል ርዕስ የሰብዓዊ መብት ተመልካች የሆነው ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) ኢህአዴግ በሚያደርስባቸው ስልታዊ … [Read more...] about “ስሉሱ” ዞረ እንዴ?!
“አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም”
ኢትዮጵያውያን በታሪካችን የታወቅነው በኩራታችንና ራሳችንን በማክበራችን ነበር፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የስዊስ አምባሳደርን ወያኔ አስፈራራውና በኢሰመጉና በሱ መሀከል የነበረውን ልዩነት አደባባይ አወጣው፤ ስለኢሰመጉ የሆነ ያልሆነውን ለመናገር መብት ያገኘህ የመሰለህ አሥር ሺህ ዶላር ስለሰጠኸን ነው፤ ይህንን አሥር ሺህ ዶላር መኪናዬን ሸጬም ቢሆን እመልስልሃለሁ ብዬ በጋዜጣ አወጣሁ፤ ይህንን ያነበበ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ እቤቴ ድረስ መጥቶ የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ሰጠኝና መከናህን አትሸጥም፤ ይኸውልህ አፍንጫው ላይ ወርውርለት ብሎኝ ሄደ፤ እኔም ለስዊስ አምባሳደር የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ላክሁለት፤ እሱም አልተቀበለኝም፤ በመቀስ ቆርጦ መለሰልኝ፤ ልናገር የፈለግሁት ዋናው ነገር ሁለት ነው፤ አንዱ ክብራችንን በገንዘብ የማንሸጥ እንደነበርን ለማስታወስ ሲሆን ሌላው ደግሞ ደጉን ጓደኛዬን … [Read more...] about “አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም”
ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!
ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን … [Read more...] about ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!
ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞ አጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡ ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡ በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራው የደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ … [Read more...] about ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?
የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት
* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!! የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል። የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል። የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና … [Read more...] about የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት










