ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ በሚመስል ሁኔታ ኢትዮጵያ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ያገኘች አስመስሎ የሚያወራው ህወሃት “ጸጥታ አስከባሪ ነኝ” እያለ በአፍሪካ ሳይጠሩት አለሁ የሚለውን ያህል አሁን ደግሞ በተራው በአገር ውስጥ ህዝብን ጸጥታ በመንሳት ሊገመገም መሆኑ ተነገረ፡፡ “በኢትዮጵያ ሰላም ለማስከበር በሚል የህወሃት ጄኔራሎች የተባበሩት መንግሥታትን ምደባ እየጠየቁ ነው” በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተሳልቀዋል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት ድምጽ የማትሰጥ አባል ሆና መመረጧ የህዳሴው ውጤት ነው፤ የመለስ ራዕይ ተግባራዊነት ነው፤ … በማለት ከፍተኛ ዲስኩር የነፋው፤ ከበሮ የደለቀው ህወሃት “ህዝብን ጸጥታ ነስተሃል” ተብሎ በተባበሩት መንግሥታት የምርመራ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በንጉሡ ዘመን እንዲሁም በደርግ ጊዜ የጸጥታው … [Read more...] about “ጸጥታ አስከባሪው” ህወሃት/ኢህአዴግ ጸጥታው ሊገመገም ነው
Full Width Top
እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባይ ጸሃዬ፤ ሳሞራ የኑስን ጨምረው ሌሎች ከፍተኛ የህወሃት ባልደረቦቻቸውንና በመያዝ አሜሪካ አገር አጭር ቆይታ አድርገው መመለሳቸውን ጎልጉል አረጋግጧል። አሜሪካ በግል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማነጋገር ውሉ ባግባቡ የማይታወቅ የሽግግር ሃሳብ ለመተግበር ማሰቧ ተሰምቷል። የሽግግር ሃሳቡ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የያዘውን ስልጣን በተወሰነ መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ሃሳብ የሚያቀርቡ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አሜሪካ ይህንን መሰሉን አቋም እንድትቀይር እየወተወቱ ነው። ለኦባማ አስተዳደር ፖሊሲ አውጪዎች ዕቅድ ለማቅረብ እነዚሁ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝግጅት አላቸው። ከሁለት ቀን በፊት አሜሪካ አጭር ቆይታ ያደረጉት እነ አባይ ጸሃዬ “እንወድቃለን” ብለው እንደሚሰጉ ለአለቆቻቸው አስታውቀዋል። የጎልጉል የዲፕሎማት … [Read more...] about እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”
ብአዴን እንደ ኦህዴድ ከዳ?!
በጎንደር ከተማ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ አካሄደ፡፡ አገራዊና ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማቅረብ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚካሄደው ትግል ያለውን ድጋፍ ገለጸ፡፡ ስልታዊ ጥርነፋውን አልፎ ትዕይንተ ህዝብ ለማድረግ መቻሉ ብአዴን ህወሃት የሚዘውረውን ኢህአዴግ ለመክዳቱ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ እሁድ ሐምሌ 24፤2008ዓም በጎንደር ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ህወሃት/ኢህአዴግ ገና ከጅምሩ የማምከን ተግባር ለመፈጸም በርካታ የጸጥታ አባላትን በስፍራው መድቦ ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ከቀናት በፊት በተናገረው እና ራሱ ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ሕገመንግሥት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉን አስቀድሞ አሳውቆ፤ በአግባቡ መልዕክቱን አስተላልፎ በክብር ተመልሷል፡፡ ዓላማውን የሚያውቅና ለሚያምንበት የቆመ ህዝብ እስካለ ድረስ ኢህአዴግ ሰልፍ ቢፈቅድም ባይፈቅድም ሕዝብ ያለውን … [Read more...] about ብአዴን እንደ ኦህዴድ ከዳ?!
ምስለ – ብአዴን
ለፖለቲካ ስልጣን ሁለተኛነት ሁሌም የሚጫወተዉ ብአዴን፤ ኢሕኢፓ በገጠመው የመበታተን አደጋ ለኢሕዴን ጥንሰሳ ምክንያት የሆነው የበለሳ ንቅናቄውን በመጀመር ብዙዎች ወደ ደርግ ሲኮበልሉ፣ እልፎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ ‹‹ጥቂቶች ቆራጦች›› ህዳር 11/1973 ዓ.ም በህወሓት አጋፋሪነት ኢሕዴንን እንደመሰረቱ በግነታዊ ቃላት የታጀበው የድርጅቱ ታሪክ ያትታል፡፡ የዘመናዊው አርበኛ (ኢሕአፓ) ኃይል በደርግ፣ ሻዕብያና ወያኔ ታክቲካል ህብረት ውልቅልቁ በወጣበት ሂደት ውስጥ የተፈጠረው ኢህዴን ደርግን ለመጣል ካደረገው ወታደራዊ አበርክቶ ይልቅ የፖለቲካ አበርክቶው እጅግ ላቅ ያለ እንደነበር ይነገርለታል፡፡ በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ ደብረታቦር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሰሜን ሸዋን የመሳሰሉ የደርግ ጠንካራ ወታደራዊ ቤዞች የነበሩትን ቦታዎች ሰብሮ ለመግባት የኢሕዴን ውስን ሰራዊትና አመራሮች የየአካባቢውን … [Read more...] about ምስለ – ብአዴን
“ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
የወልቃይት ጉዳይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ደም እያፋሰሰ ባለበት በሁኑ ወቅት ቴድሮስ አድሃኖም ወልቃይትን የትግራይ ግዛት አድርገው በመቁጠር "የአማራ ብሔር ተወላጆች ወልቃይት መጥተው መኖር ከፈለጉ የትግራይ ሕዝብ በደስታ ይቀበላቸዋል" በማልተ የትግራይ ሕዝብ ወክለው ስለ ወልቃይት የትግራይ ክልልነት በድፍረት በፌስቡክ ላይ ይህንን ብለዋል - ሙሉው ቃል ከዚህ በታች ይገኛል:- በጎንደር የተከሰተውን የማንነት ጥያቄ ሰበብ በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች ብጥብጥ ለማስነሣት ቢሞክሩም መንግሥታችን በሰከነ ዘዴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውሎታል:: የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአማራ ተወላጆች ጋር በመወያየትና በማሳመን የወልቃይትን መሬት የትግራይም ሆኑ የአማራ ተወላጆች በጋራ እንዲኖሩበት በማግባባት ላይ ይገኛል፡፡ ወልቃይት የአማራ ነው በማለት የሚነዛው ፕሮፓጋንዳም የሐሰት መሆኑና … [Read more...] about “ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ
በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!
በጎንደር የሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ ሕዝብ የማያምንባቸውንና ከትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ንብረቶች ላይ ርምጃ መውሰዱ ታውቁዋል። ማክሰኞ ሊነጋጋ አካባቢ ተነሳ የተባለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀላቀል ወደ ጎንደር ያመሩ ወገኖችም መበራከታቸው እየተሰማ ነው። ለዓመጹ ውጤታማነት የዘር ትግል ሳይሆን ኅብረብሔራዊ እንቅስቃሴ እንደሚበጅ ተገለጸ። አመጹ የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ ባነሱና "እኛ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም" በሚል የተነሳውን ጥያቄ ከውጤት ለማድረስ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አራት የሚሆኑትን ከትግራይ የመጡ ነፍጥ አንጋቾች ከያዟቸው በኋላ እንደሆነ ለኢሳት በድምጽ ማብራሪያ የሰጡ አረጋገጠዋል። ከዚያም ኮሎኔል ዘውዱ ደመቀን ለመያዝ ሙከራ ተደረገ። ይህን ጊዜ ኮሎኔሉ "በሬን አልከፍትም ጥዬ እወድቃለሁ" በማለት ሊያስሯቸው ከመጡት ሃይሎች … [Read more...] about በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር “እየቀለለ” ነው!
ጠቅላላ ወጪው 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተነገረለት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በብልሽት ምክንያት ግማሽ ያህል ባቡሮቹ እንደማይሰሩ ተነገረ፡፡ የባቡሩ ፕሮጀክት ከመጠናቀቁ በፊት ሥራው እንዲጀመር ህወሃት/ኢህአዴግ ግፊት አድርጎ ነበር፤ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የፖለቲካ ውሳኔ ነው፤ ቀላል ባቡሩ “እየቀለለ ነው” ተብሏል፡፡ ማክሰኞ ዕለት የተሰማው ሸገር ሬዲዮ ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ መረጃ አቀባዮቼ አደረሱኝ ባለው መሠረት ከተጀመረ ዓመት ያልሞላው የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ሥራ “እየቀለለ” መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአገልግሎት ከተመደቡት 41 ባቡሮች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙት 28ቱ ብቻ መሆናቸውን መረጃ አቀባዮቹን ጠቅሶ ሬዲዮው አስረድቷል፡፡ ሃያ አንዱ ባቡሮች በብልሽት ምክንያት አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚሳልፉት በጥገና እንደሆነ፤ የመለዋወጫ ችግር ደግሞ ይበልጥ … [Read more...] about የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር “እየቀለለ” ነው!
የስቃይ ሰለባዎች
በዞን ዘጠኝ ዓለማቀፍ የማሰቃየት ተግባር ተጠቂዎችን የመደገፍ ቀን (International Day in Support of Victims of Torture) ከጎርጎሮሳዊያኑ 1998 ጀምሮ በየዓመቱ ጁን 26 ቀን ይከበራል፡፡ ቀኑ ጁን 26 ላይ የሚከበርበት ሁለት ምክንያቶች ሲኖሩ፤ አንደኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር በመስራች አባል አገራት ቻርተሩን የፈረሙበት ቀን ጁን 26፣ 1945 ሲሆን በሁለተኝነት የተባበሩት መንግስታት የፀረ ማሰቃየትና የጭካኔ የቅጣት ተግባር ኮንቬንሽን (Convention against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment) ወደ ስራ የገባው ጁን 26፣ 1987 በመሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የቻርተሩም መስራች ፈራሚ ስትሆን ኮንቬንሽኑን ደግሞ በፓርላማ አጽድቃ ተቀብላለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት … [Read more...] about የስቃይ ሰለባዎች
“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡ “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል) “በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላ የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ … [Read more...] about “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”
ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!
በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ በአሜሪካ፤ በአውሮጳ፤ በአውስትራሊያና በኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በቅርቡ ወሳኝ በሆኑ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ መታሰቡን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል፡፡ ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑና የአገራቱም ዝርዝር እንዳላቸው የተናገሩት መረጃ አቀባይ የሹምሽሩ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ህወሃት ከውስጥና ጫና ተጠቃሽ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ በኢህአዴግ ተለጣፊና ድቃይ ድርጅቶች ታቅፈው የሥርዓቱ ሎሌ የሆኑት አምባሳደሮች በመጪዎቹ … [Read more...] about ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!









![“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”](https://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2016/06/Slide4-e1466824461975-300x148.jpg)
