• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጎንደር የተነሳው አመጽ እየሰፋ ነው!

July 13, 2016 10:10 am by Editor 2 Comments

በጎንደር የሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ ሕዝብ የማያምንባቸውንና ከትግራይ ተገንጣይ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ንብረቶች ላይ ርምጃ መውሰዱ ታውቁዋል። ማክሰኞ ሊነጋጋ አካባቢ ተነሳ የተባለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመቀላቀል ወደ ጎንደር ያመሩ ወገኖችም መበራከታቸው እየተሰማ ነው። ለዓመጹ ውጤታማነት የዘር ትግል ሳይሆን ኅብረብሔራዊ እንቅስቃሴ እንደሚበጅ ተገለጸ።

አመጹ የተቀሰቀሰው የማንነት ጥያቄ ባነሱና “እኛ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም” በሚል የተነሳውን ጥያቄ ከውጤት ለማድረስ ከተመረጡት የኮሚቴ አባላት መካከል አራት የሚሆኑትን ከትግራይ የመጡ ነፍጥ አንጋቾች ከያዟቸው በኋላ እንደሆነ ለኢሳት በድምጽ ማብራሪያ የሰጡ አረጋገጠዋል። ከዚያም ኮሎኔል ዘውዱ ደመቀን ለመያዝ ሙከራ ተደረገ። ይህን ጊዜ ኮሎኔሉ “በሬን አልከፍትም ጥዬ እወድቃለሁ” በማለት ሊያስሯቸው ከመጡት ሃይሎች መካከል ሁለቱን” ጣሉ። ይህንን የሰሙ የወልቃይት ሚሊሻዎች በስድስት አውቶቡስ ጎንደር ደረሱ። ቀደም ሲል ህዝብ የኮሎኔሉን ቤት ከቦ አላስነካም ብሎ ቆየቶ ነበርና በመደጋገፍ ኮሎኔል ዘውዴ ጥቃት ሳይደርስባቸው ከቤታቸው ማስወጣት እንደተቻለ ለኢሳት ማብራሪያ ከሰጡት ለማወቅ ተችሏል። tmp_29027-image-0-02-01-69d0f7f2ea563ae5a74916cea250d7fd0bc0411a96d357cca5c257fb60b23503-V-1175058064

አክለውም የዞኑ አስተዳደርና የክልሉ ሃላፊዎች እየሆነ ስላለው ሲነገራቸው ያለማቅማማት “የምናውቀው ነገር የለም። የምትችሉትን ርምጃ ውሰዱ። ነገር ግን መሳሪያ አንሰጣችሁም” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ስም ጠቅሰው ተናግረዋል።

ከትግራይ መጡ የተባሉትና የክልሉንም ሆነ የዞኑን ፈቃድ ካላገኙት ታጣቂዎች መካከል 6 የሚሆኑት የተገደሉ ሲሆን ከህዝብ ወገን ቁጥሩ በትክክል ያልተገለጸ ህይወት ማለፉን የማህበራዊ ገጾች እየዘገቡ ነው። የህወሃት ሚዲያም 4 የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ይፋ አድርጓል። ጉዳዩንም ከዘረፋና ከሽብር ጋር አያይዞታል።

ኢሳት በተከታታይ ያነጋገራቸው ሰው እንዳሉት የወረቀት ጥያቄ ላቀረቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን በደል ሰርተው ይህ ሁሉ ስቃይ እንደሚደርስባቸው ግልጽ አይደለም። በዚሁ መነሻ በህወሃት የበረሃ ትግል ወቅት ምግብ፣ መሬት፣ ከለላ በመስጠት፣ ደግሶና አካፍሎ ሲያበላ የነበረ የወልቃይት ህዝብ ውለታው ይህ መሆኑን በማስታውስ “የትግራይን ህዝብ ከወንድሙ የአማራ ህዝብ ጋር የህወሃት ባለስልጣናት ደም እያቃቡት ነው። የትግራይ ህዝብ ይህን ጉዳይ እንዴት ያየዋል?” ሲሉ ጠየቀዋል። አያይዘውም “ለወደፊትስ አስቸጋሪ አይሆንም? አማራ ምን አደረገ?” ሲሉ መልዕት አስተላልፈዋል።

ሕዝባዊ ቁጣው መጠኑን እየጨመረ ሲሆን በዳባት ተመሳሳይ ተቃውሞ መጀመሩም ተጠቁሟል። እንደ ማብራሪያ ሰጪዎቹ ከሆነ አሁን የተነሳው ህዝባዊ አመጽ “አማራውን ሊያጠፉት ነው ሳትጠፋ የቻልከውን አጥፋ” ወደሚል ምሬትና አልሞት ባይ ተጋዳይነት ተሸጋግሯል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አማራውን ገፍተው ገፍተው እዚህ አደረሱት” ሲሉ አሁንም ህወሃት ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባው፣ በሃይል እገፋበታለሁ ካለ ነገሮች መስመራቸውን ሊስቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ስለሆነም ዓመጹ ውጤታማ እንዲሆን በዘር ወይም በወገን ወይም በብሄር ላይ ያተኮረ ከመሆኑ ይልቅ ሁሉንም ያካተተ ህብረብሄራዊ ሊሆን እንደሚገባ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ  በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በህወሃት ጥቃት ያልደረሰበት፥ ያልተጎዳ፥ ስቃይ ያላየ አለመኖሩ ሁሉንም የጥቃት ሰለባ በአንድነት ሊያስተባብር የሚችል ችግር መኖሩ ግልጽ ነው የሚሉት ወገኖች መፍትሔውንም በጋራ መቀመም ብልሃት የሚጠይቅ ለሁሉም ወገን የሚጠቅም አማራጭ ነው በማለት ተደማጭነት ያላቸው፥ በሁሉም ሰው ዘንድ መሰማት የሚችሉ ግለሰቦች መሪውን መጨበጥ የሚገባቸው ሰዓት አሁን ነው ይላሉ። ከዚህ በታች ያለውን የፎቶ መረጃ ያገኘነው በተለያዩ ግለሰቦች ከተሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎችና ገጾች መሆኑንን እንገልጻለን።

tmp_15399-13710715_1148946795144607_2017281093280564382_o1685727325

tmp_15399-13707789_1148946778477942_5492643436133731161_n1133332102

tmp_15399-image-0-02-01-a572473c5f641bb9c088bffa0ec9465f701552bd58cb1ab86268e062f5fe18c4-V1971705821

 

tmp_15399-image-0-02-01-192a9dfe6bfff5d1bbd8b8b45b7dee506627e8c650f3c9ac6700b63c3aebd185-V-2001290385

tmp_15399-image-0-02-01-217e92e8d567ef5197bad2cc41ee07318670e2389390764fddc5cb213001bcdc-V-700063890

tmp_15399-image-0-02-01-96ff643f388aedca3a1c22a1890a46afc5212539577470929da8ee23541083d8-V1771574122

tmp_15399-image-0-02-01-e2b4a6beeda20c7bb79e07a810ec11845b76f82d1ce9398e551b9eef24b8f356-V-1123621149

tmp_15399-image-0-02-01-583bd9387c71fef30efd1277e624b14a10b32aa36188424c264b19885e17afba-V-1576589714

tmp_15399-image-0-02-01-faa277e39bd106e02fc549d93327c7ac1d7f8734b33c97ef035a84f15d05131f-V1666556473

tmp_15399-image-0-02-01-e1f0b35e678abf0e5053381d1bf46724ce5787a104e5e2fb23a690072c44c068-V-163156207

tmp_15399-image-0-02-01-7c0f8afa0205c40e7248f09bc94493431a3c9b7adf0613f71b82fe84512d6887-V1152039146

tmp_15399-image-0-02-01-2bf417e10269578b47350508804ee9da8f3a4bf3342fd0c8b561628ed3509250-V1318858571

tmp_15399-image-0-02-01-b751af1f29aabede0f48a26913c0788c7754e1111872b2cbaae01fe1ace66904-V521799796

tmp_15399-image-0-02-01-22f4f68275868ccd7108f6c5307805a6c70944df005ed6bb11da0416dab59196-V1197009622

tmp_15399-image-0-02-01-f6a5c95cac38eabc84d1a160a0ab4f46fa8e5ed63c6c5b98b14a6361690cf075-V-873836785

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    July 16, 2016 07:10 pm at 7:10 pm

    Aye Gura

    Gonder has never truly ruled itself in its history

    Bekafa (Oromo ) ,Michael Shehul (tigrai ) Tewodros ( Wello Oromo ) ruled it for centuries

    Melaku Tefera under Mengistu ( Gimira )order ( Gondere) ruled it for years

    Reply
  2. gud says

    July 16, 2016 07:12 pm at 7:12 pm

    Fukera

    These people r In 18th century . Need proper education .

    Hwala kernet at its best !

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule