መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም ብቻ ይሆንብናልና። በተለምዶ ያ ትውልድ እያልን የምንጠራው ቀዳሚው ትውልድ ኣንድ የሆነ ሼል ሰብሮ የወጣ ነበር። ያ ትውልድ ለዘመናት የነበረውን ዘውዳዊ ኣገዛዝ ደፍሮ የጠየቀ፣ የፍትህና የእኩልነትን ጥያቄዎች ኣንግቦ ግንባሩን ለጥይት የሰጠ በመሆኑ ታሪክ ሁልጊዜም ያ ትውልድ..........እያለ ሲያስታውሰው እንዲሁ ይኖራል። (ሙሉውን … [Read more...] about ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
Uncategorized
ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
የህውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሰላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል ህውሃት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሰራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) … [Read more...] about ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!
ዲሲ 2013
ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። "ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።" ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ በመሆንዋ ታሪኳን ጠለቅ እያልን ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ሊወሳሰብ ስለሚችል እጅግ ብዙ ጥናት ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ጸሃፊው ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር የሚጽፈው ጠፍቶት ሳይሆን ግራ ተጋብቶ መጻፉን ያቆማል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ዲሲ 2013
የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል። በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው። አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ … [Read more...] about የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ
ከ፩፯ አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ፪፪ አመታት የስርአቱን ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ አፓርታይድ ስርአት ተቀይሮዋል። ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት ፪፩ አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ
በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር
አንድ ምራቅ መዋጥ የጀመረ የ28 ዓመት ወጣት የኑሮ አጉራ ቢጠናው ጊዜ ወደ ጠንቋይ ቤተ ይሄዳል፡፡ ለአጋፋሪው ሣንቲም ቢቴ ቦጨቅ ያደርግና ወረፋውን አፋጥኖ በተሎ ይደርሰዋል፡፡ በሁሉም ቦታ መቼም ይቺ ሙስና ተንሰራፍታለችና በዚህ አይግረማችሁ፡፡ ሀገራችን በተለይ በዚህ አንደኛ ሳትሆን የምትቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንቋይ፤ ምን ፈልገህ መጣህ? አውሊያው ምን እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ አንተ ብላቴና? አስጠንቋይ፤ የኑሮ ችር ነው ወደዚህ ያመጣኝ፡፡ ሕይወቴ ልፋት ብቻ ሆነ፤ ቀን ከሌት ብለፋ ድካም እንጂ ውጤት የለም፡፡ ጓደኞቼ የትና የት ሲደርሱ እኔ በድህነት እየማቀቅሁ ቀረሁ፡፡… ጠንቋይ፤ አይዞህ፤ ገና ወጣት እኮ ነህ፡፡ ተስፋ አትቁረጥ… አስጠንቋይ፤ እሺ! በርስዎው መጀን አባቴ፡፡ ያለርስዎ ማን አለኝ፡፡ እስካሁንም ወደርስዎ ያልመጣሁት … [Read more...] about በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር
የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውና ማየት የሚፈልገው!
ባለፉት ዐመታት በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ምርጫዎች ተካሂደዋል። ከአምስት ዐመት በፊት በኬንያ የተካሄደውንና፣ በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ደግሞ በናይጄሪያ የተደረገውን የፕሬዚደንትና የፓርላሜንት ምርጫ ትዝ ሳይለን አይቀርም። ከአንድ ዐመት በፊት ደግሞ በቱኒዚያ የተለኮሰው የሰሜን አፍሪካው የጥቢው አብዮት እየተባለ የሚጠራው ወደ ግብጽና ወደ ሊቢያ፣ ከዚያም ወደ የመን በመሸጋገር የስርዓት ለውጥ ሳይሆን የፕሬዚደንቶችን ለውጥ አስከትሏል። … … ከዚህ ስንነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘው፣ የሚያልመውና የሚጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ነው። የዛሬው የወያኔ አገዛዝ በአንዳች ነገር ቢወድቅ ምኞቴን የሚያሟላልኝ፣ ህልሜን ዕውን የሚያደርግልኝ፣ ነፃነቴን የሚያስከብርልኝና፣ ተከብሬና ተዝናንቼ በአገሬ ውስጥ ለመኖር የሚያስችለኝ የተደራጀ ኃይል አለ ወይ? ካለስ እንዴትና በምንስ ዘዴ ነው ስር የሰደደውን … [Read more...] about የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውና ማየት የሚፈልገው!
የእህቶቻችን ሰቆቃ በአረብ ምድር
ይህ የምትመለከቱትን ፎት ያነሳሁት በጅዳው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች አንድ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህች የምታይዋት እህትም ምን እዚያ አመጣት እንዳትሉ ! ከአንድ ወር ከሳምንት በፊት በኮንትራት ስራ ከሀገር ቤት የመጣች መሆኗን ሳውዲው የእድሜ ባለጸጋ አሰሪዋ ተነገረውኛል፡፡ እኔም ሆንኩ ይህንን ጉድ አብረውኝ የሚመከቱ እህቶቸ ሁላችንም ወደ ሃገር ቤት የሚሸኙ ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን አጅበን ነና የመጣነው የዚህች እህት ወደ አየር መንገዱ ለምን እንዳመጣች መጠየቅ አላስፈለገኝም ፡፡ በሰውነቷ ላይ ባረፈውን እስራትና ድብደባ ከመገለ እጇና ገላዋ ላይ ሰንበር የመሰለ የጉዳት ምልክት ይታያል፡፡ (ሙሉው ታሪክ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የእህቶቻችን ሰቆቃ በአረብ ምድር
Test post
This is a test post for testing links and other things. Donec vestibulum feugiat augue, ac ultricies tellus condimentum luctus. Sed congue dolor eu urna faucibus adipiscing. Morbi malesuada, ligula et tempus tempor, leo justo commodo augue, rhoncus tincidunt sem ligula ut nisl. Duis ornare tortor ut massa pellentesque eu aliquam nisi tincidunt. Vestibulum malesuada vulputate ligula, in rutrum erat ullamcorper vel. Phasellus sem metus, accumsan sed porttitor non, interdum ac massa. In sit amet … [Read more...] about Test post







